Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 18081
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

ብርጫው በሰላም ልዑካን

Post by Selam/ » 08 Jun 2026, 08:17

ካድሬዎችና ጎጠኞች ER ላይ እንደ ትንኝ ሲርመሰመሱ የሰላም ልዑካን ከግንቦት ፳ ማግስት የተደረገውን ብርጫ በቦታው ተገኝቶ ሲከታተል ቆይቶ በሰላም ተመልሷል። ልዑካኑ በዋነኛነት ወለንጪቲን፣ አዲስ አበባንና ደብረ ሲናን በንቃት ታዝቧል። ግን ካልጠፋ ጊዜ፣ የኢትዮጵያ ብርጫ ቦረንትቻ በሚጣልበት ቀፋፊ ወር ውስጥ መሆኑ አይገርማችሁም? እግዜር ይፍረድብሽ ወያኔ!


በሸኔ፣ በወያኔና በመሬት መንቀጥቀጥ የምትናጠው ደብረ ሲና እንደተፈራው ሳትረበሽ ብርጫውን በስነ ስርዓት አጠናቃለች። በየብርጫ
ጣቢያዎች ዳስ ተጥሎ ማለትም ድንኳኖች ተደኩነው ህዝቡ ከጠዋት ጀምሮ በመገኘት በካሜራ እየተቀረጸና ጎመን በጤናን እያማተበ ድምፁን ሰጥቶ ወደየቤቱ ተመልሷል።

አዲስ አበቤዎችም የዕረፍት ቀናቸውን በመጠቀም፣ ቱታቸውን ለብሰው ብርጫውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዋል። ደርግ ስኳር በመከልከል፣ ወያኔ ኮንዶሚኒየም እንቁልልጮ በማድረግ፣ ፒፒ ደግሞ በወፍ በረር ስለላ ልቦናን በመስረቅ የበራጮችን ድምፅ በገፍ አግኝተዋል።

ፀዴዋ ወለንጪቲም በኦነግና በባለ ኮከቡ ባንዲራ ደምቃ በነፋሻ አየሯ ዛፎቿን እያወዛወዘች በራጮችንና ተበራጮችን አንድ አድርጋለች። ልማቱ ይቆምብሃል፣ ነፍጠኛ ይሰለቅጥሃል የተባለው ሙሉ ኦሮሞ ፣ ግልብጡ ኦሮሞ እንዲሁም ሌላውም ህብረተሰብ ውጤቱ ቀድሞ የታወቀውን ብርጫ በነቂስ ወጥቶ ተሳትፏል።

ስለሆነም ወንድም ወይንም እህት ሳይኖረው ብቻውን ያደገው አቶ ዓብዮት ከጎፍጫላው ሽመልስ ጋ አብሮ ሮጦ ብቻውን አሸንፏል።