Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7632
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኣንድ ደቂቃ ያልወሰደ ቅጽበታዊ ቅጣት እና አስራ አምስት ዓመታት ገደማ የወሰደ ትግል ታሪኮች

Post by Naga Tuma » 04 Jun 2026, 00:08

የሁለቱም ታሪኮች ስለ ጋላ ብሎ ስድብን መቃወም ነዉ።

ኣንዱ ተቃዉሞ ትልቅ የከተማ አደባባይ ገበያ ዉስጥ የተከሰተ ነዉ።

ለፍታ ነዋሪ እናት አታክልት ለመሸጥ ገበያ ሄዳ ኣንድ ከተሜ ከኣታክልቱ ገዝታ በባህል የሚታወቀዉ ምርቃት ጨምሪ ብላ ተጨመረላት።

ኣታክልቱ ያማራት ምርቃቱ ያንሳል፣ ጨምሪ ኣለች። ምርቃት የጨመረች ለፍታ ነዋሪ እናት በቂ ምርቃት ሰጥቻለሁ ኣለች።

በምርቃት ላይ ምርቃት ያልተጨመረላት ኣኩርፋ ይህቺ ብላ ቃሉ ከአፏ ሲወጣ ለፍታ ነዋሪ እናት እንዴት እና በምን ፍጥነት ረጅም ዱላ እንዳየች ኣሁንም ድረስ በማይገባኝ ሁኔታ በቅጽበት ኣንስታ በሃይል ኣሳረፈችባት።

ከዛ በኋላ ወጣቷ ልጅ በምን ፍጥነት ደብዛዋ ከስፍራዉ እንደጠፋ ኣሁንም ድረስ ኣልገባኝም።

ዙርያዉን የነበሩት ገበያተኞች ተደናብረዉ ሹክ ሹክ ብለዉ ግብይቱ በሰላም ቀጠለ።

ይህንን ታሪክ ከለፍታ ነዋሪዋ እናት ጋር ልጅ ሆኜ ስለነበርኩኝ ኣይቻለሁ።

ሌላዉ ታሪክ ከከተማ ሽሽት በኋላ አስራ አምስት ዓመታት ገደማ የወሰደ ያንኑ የስድብ ቃል የመቃወም ትግል ነዉ።

ስለዚህኛዉ አምበሳ በሚል ስም መታገልን ታሪክ የማዉቀዉ ተጽፎ ያነበብኩኝን ነዉ።

የአስራ አምስት ዓመታት ገደማ ትግሉ የአምበሳነት ጀብዱ የተፈጸመበት ዬት ዬት ሜዳ መሆኑን ኣሁንም ድረስ ኣጋጥሞኝ ኣንብቤ ኣላዉቅም።

ሁለቱን ታሪኮች ኣስታዉሼ ማነጻጸሩ እንቆቅልሽ ሆኖብኛል።