Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Misraq
Senior Member
Posts: 18099
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Misraq » 28 May 2026, 22:50

ሶዶው ወንድማችን

እኖር ጴንጤው ሊስትሮ (Odie) እና ምስቃን ወሃብያው ሊስትሮ (Dama) ይህን በመለጠፍህ ጓ እንዳይሉብህ :mrgreen:

Horus
Senior Member+
Posts: 43456
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Horus » 28 May 2026, 23:13

Misraq wrote:
28 May 2026, 22:50
ሶዶው ወንድማችን

እኖር ጴንጤው ሊስትሮ (Odie) እና ምስቃን ወሃብያው ሊስትሮ (Dama) ይህን በመለጠፍህ ጓ እንዳይሉብህ :mrgreen:
አንተ ጠንቋይ በምን ቋንቋ ልንገርህ!

ክስታኔ ማን እንደ ሆነ ለማወቅ ካንጎልህ በላይ ነው

ይህ ካቴድራል ሰርተን ስንጨርሰው ካፍሪካ 1ኛ ነው የሚሆነው ገቢሽ !


Naga Tuma
Member+
Posts: 7623
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Naga Tuma » 29 May 2026, 20:29

ትላንትና ይህን ርዕስ ሳለይ በፊት ስለ ኢትዮጵያ የጥንት እና የዘመኑ ሃይማኖት ኣዲስ ርዕስ ለመጀመር ኣቅጄ ነበረ።

ስለዛ እያሰብኩ ይህን ርዕስ በኣጋጣሚ ማየቴ ገርሞኛል።

እኔ ያሰብኩኝ በዚህ የፍርድ ዘመን የተባለ ግዜ የአደዋ ማግስት እንግዶች እና በትለር፣ እና ብሩስ ኢትዮጵያ ሄደዉ ያስተማሩዋቸዉ ልጆች የተማሩትን ኢትዮጵያ ዉስጥ እናስፋፋለን ሲሉ ሌላ ኢትዮጵያዊ አሜሪካ ዉስጥ ስለ ቅድመ ክርስትና የኢትዮጵያ ስልጣኔ እና ሃይማኖት ለማስተማር ለብቻዉ ይለፋል ነዉ።

ለዚህ ኣንዱ ዋነኛ ማስረጃዬ አሜሪካ God የምትለዉ ቃል መሠረቱ ኢትዮጵያ መሆኑ ነዉ።

Gofta/Goita/Gheta/God/god/Gott/goth/guth.

የዚህ ገዳም ነገር መለኮታዊ የሆነ ተዛማጅ ሀሳብ ያለዉ ይመስላል።

በመጀመርያ ዝነኞች የተባሉት የቫቲካን እና የአሜሪካ ኮንግረስ ላይብረሪዎችን ኣስታወሰኝ።

በምድር ላይ እጅግ ታዋቂ ነበር የተባለዉ የአሌክሳንድርያ ላይብረሪንም ኣስታወሰኝ።

ፕሮፌሰሮች ሰባቲካል የተባለ ዕረፍት ግዜ ስያገኙ ቫቲካን ላይብረሪ ሄደዉ ምርምር ያደርጋሉ ኣሉ።

ለዚህም ነዉ ይህ ገዳምም ስለመንፈሳዊ ነገሮች ዋነኛ የምርምር ላይብረሪ ያደራጅ ይሆን ያስባለኝ።

ስለ ቅድመ ክርስትና የኢትዮጵያ ስልጣኔን መጀመር ቁልጭ ኣድርጎ የምያሳይ ፎቶ ነዉ ያልኩኝን ያየሁኝ ከሃያ ዓመታት በፊት ሎስ ኣንጀለስ ዉስጥ ነዉ።

ፎቶዉ የተገለጹበት ቃላት ሴረ ቱማ ገዳ ነዉ።

ያ ፎቶ የጥንት ኢትዮጵያ ስልጣኔ መጀመርን ገዳ ብሎ የምያሳይ ከሆነ ይህ ድርጅት ደግሞ ስለ ጥንት ኢትዮጵያ ሃይማኖት ገዳም ብሎ የምያሳይ ይሆናል ማለት ነዉ፣ በእኔ አስተሳሰብ ማለት ነዉ።

ዞሮ መጀመርያ ማለትም የሚሆን ነዉ።

ቫቲካን የአዉሮፓ ህዳሴ ዉስጥ ያለፈች ናት። አሜሪካ የዛ ህዳሴ የበኩር ልጅ ናት።

ኢትዮጵያ የራሷን ህዳሴ ገና ሀ ሁ ማለት ያልጀመረች ናት።

የሙሴ ሃዉልቶች ቫቲካን እና የኣሜሪካ ጎንግረስ ህንጻ ዉስጥ ግዙፎች ሆነዉ የሚደነቁ ሲሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ የጥንት ኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪ ታላቅ ፈረዖ የነበረ መሆኑ ገና በሰፊዉ ያልታወቀ ነዉ።

በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት በጣም ግዙፍ ህዳሴ ማድረግ እግዝኣብሔር በአሰራሩ ፊቷ ላይ ጋርጦት ይገኛል።

ሌላ ገንቢ ሀሳብ የሚመስለኝ ገዳም ሙያዋ መንፈሳዊ ነገር ላይ ማተኮር ከሆነ አሜሪካ ዉስጥ ስለ ሪሃብልቴሽን የጤንነት ሙያ ያላቸዉ ብያስተናግዱት ይሻላል ባይ ነኝ።

የአሜሪካ ትምህርት ቤቶች ስለ ግሪክ ቅድመ ክርስትና ጎድስ እና ጎደስስ የምያስተምሯቸዉ ልጆችን የኢትዮጵያ ገዳም በክርስትና ትምህርታችን እንፈዉሳለን ማለት ለሁለቱም ቡድኖች ገንቢ የሚሆን ኣይመስለኝም።

የእኛ የኢትዮጵያዊያን ትልቁ ጥንካሬያችን ቀዳሚ ስልጣኔ ያለን እንጂ የበታች ኣይዴለንም ማለታችን ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ትልቁ ዉድቀታችን የምጀምረዉ የበታች ነን ብለን ያሰብን ዕለት ነዉ።

እኔ ህዳሴ ወይም እዴሳ የምለዉ የኢትዮጵያ ቀዳሚ ስልጣኔ ገዳን እና ቀዳሚ መንፈሳዊ ኣገልግሎት ገዳምን በምርምር መልሶ ማስተዋወቅም ነዉ።

ለዚህ ደግሞ ቫቲካን ዉስጥ እና የአሜሪካ ኮንግረስ ህንጻ ዉስጥ ሃዉልቱ ግዙፍ ሆኖ የሚደንቅ ሙሴን ትክክለኛ ማንነት ማጣራት እና ማሳየት ትልቅ ጅምር ሊሆን ይችላል።

Odie
Member+
Posts: 8010
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Odie » 29 May 2026, 21:19

Misraq wrote:
28 May 2026, 22:50
ሶዶው ወንድማችን

እኖር ጴንጤው ሊስትሮ (Odie) እና ምስቃን ወሃብያው ሊስትሮ (Dama) ይህን በመለጠፍህ ጓ እንዳይሉብህ :mrgreen:
ቅምምምምምምምምምምምቡርስ :lol:

Lifeless :lol:
በተዘረፈ የድሃ ገንዘብ የተስራ!


Horus
Senior Member+
Posts: 43456
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Horus » 29 May 2026, 21:50

በምሁር አክሊል ጉራጌ ያለው ታላቁ ምሁር ኢየሱስ ገዳም!




Digital Weyane
Senior Member
Posts: 10235
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Digital Weyane » 29 May 2026, 21:57

እንኳን ሰው ቤተ መቅደሶቻችንን ሳይቀሩ ሃገር ጥለው ተሰደዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት ናት ማለት ይቻላል። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ :cry: :cry: :cry: :cry:

Horus
Senior Member+
Posts: 43456
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Horus » 29 May 2026, 23:43

Digital Weyane wrote:
29 May 2026, 21:57
እንኳን ሰው ቤተ መቅደሶቻችንን ሳይቀሩ ሃገር ጥለው ተሰደዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት ናት ማለት ይቻላል። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ :cry: :cry: :cry: :cry:
ምቀኛና ቅንድብ አያድጉም አሉ አምሆይ ጻዲቄ!

ቫቲካን እንኳ አንድ ከተማ የሚያክል ገዳም ባሜሪካ የለውም !

Naga Tuma
Member+
Posts: 7623
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Naga Tuma » 31 May 2026, 18:18

ታሪካዊ ሐቆች

1) እ ኢ አ በ1888 ዓም ገደማ መንግስቱ ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ዉስጥ ያቋቋመዉ ኣዲስ ኮሌጅ ዉስጥ ስለ ኣንዱ የእንግሊዝ ሳይንቲስት ኒዉተን ቀመር ወይም ሎዉ ተማርኩኝ።

2) ኮርሱን ያስተማረዉ በወቅቱ ሌክቸረር የነበረ ዶክተር ስለሺ በቀለ ነዉ።

3) አሜሪካ የትምህርት ዕድል ኣግኝቼ ተምሬ ስራ ኣግኝቼ በጥቂት ወራት ዉስጥ ኢትዮጵያ የተማርኩኝ የስራ አሰራር ይኖራል ብዬ ስለገመትኩ እንድያሳየኝ ኣንድ የስራ ባለሙያ ጠየኩኝ።

4) የጠየኩት የስራ ባለሙያ ስለምን እንደጠየኩት ያላጤነ መሆኑን እና የጠበኩት አሰራር ኣለመኖሩን በኣጭር ግዜ ዉስጥ ግልጽ ሆነልኝ።

5) ለግዜዉ ተሰናብቼዉ የስራዉ አሰራር ባለመኖሩ እጅግ ተገርሜ ራመድ ራመድ እያልኩኝ ለብቻዬ ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮብሌም ኣልኩኝ።

6) የስራዉ አሰራር ኣለመኖሩ ብቻ ሳይሆን አሰራሩ ሳይኖራቸዉ ስራዉን እንዴት መስራት እንደቻሉ በጣም ደነቀኝ።

7) ይኖራል ብዬ የጠበኩኝን አሰራር ሰርቼ ለማሳየት ትልቅ ዕድል ነዉ ብዬ ተያያዝኩት።

8) አሰራሩን ኣብረን እንስራ እያልኩ ስወተዉትም ብዙ ግዜ ኣለፈ።

9) ሰርቼ ለማሳየት እድል ኣገኘሁ ያልኩኝን ስራ ሙጭጭ ብዬ ቁልጭ ኣድርጌ ኣሳይቼ እ ኢ አ በ2004 ዓም ኣንድ የኣሜሪካ የሙያ ጆርናል ዉስጥ ለማሳተም በቅቻለሁ። ይህን ሳይንሳዊ ስራ ስሰራ ተዋከብኩ ብል እንጂ ተደገፍኩ ማለት የምችል ኣይመስለኝም። አለቃ የነበረዉ እንደ ቡድሃዎች እግዝኣብሔር ዬለም ብሎ የምያምን መሆኑን ሆነ ኣለመሆኑን ኣላዉቅም።

10) እ ኢ አ 1996 ዓም ገደማ ተዓምራዊ የሆነ በሚመስል መንገድ ዶክተር ስለሺ በቀለ እኔ የምኖርበት ከተማ ጓደኛዉን ሊጠይቅ መጥቶ እግረመንገዱን ተገናኘን።

11) እኔ መምጣቱን ኣዉቄ እንገናኝ ብዬ ጠይቄ ሳይሆን እሱ በከተማዉ መኖሬን ሰምቶ እንድንገናኝ ጠይቆ ተገናኘን።

12) ከጓደኛዉ ጋር ለእራት ጋብዘናቸዉ መልካም ግዜ ኣብረን ያሳለፍን ይመስለኛል።

13) ግብዣዉ ላይ ዉይይት ተነስቶ ሁለቱ ጓደኞች ስለ ኣንድ ርዕስ ኣንድ ደቂቃ ላልሞላ ግዜ ተነጋገሩ። ኣንዱ ኢትዮጵያ ዉስጥ በዛን ወቅት ከነበሩት መሪዎች ዉስጥ ኣዕምሮ ያለዉ ኤከሌ ብቻ ነዉ ሲል ሌላዉ ኤከሌ እና ኤከሌ ናቸዉ ኣለ። እኔ ስለ ርዕሱ ኣንድም ነገር መናገሬን ኣላስታዉስም።

14) በዉጪ ሃገር ስለ ኢትዮጵያ የፖለትካ ዉይይት ሳነብ እና ኣልፎ ኣልፎ አስተያየት ስሰጥ ኖሬ እ ኢ አ 1996 ዓም መጀመርያ አከባቢ ያለኝን አስተያየት ላጋራ እና ወደ ኣካዳሚ ላተኩር ብዬ ባለ አረት ክፍሎች ትንታኔ ጻፍኩኝ።

15) ከዛ ትንታኔ በኋላ የኦሮምያ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እንዲዛወር መወሳኑን ዜና ሰማሁኝ።

16) ዉሳኔዉ እተዋለሁ ወደኣልኩኝ መልሶኝ ተቃዉሞ ለማስተባበር ጣርኩኝ።

17) የሃገር ዉስጥ ተቃዉሞን ለማስተባበር መረራ ጉድና ቀዳሚ ሚና የነበረዉ መሆኑን ዜና ባነብም የዉጪ ሃገሩን ተቃዉሞ ለማስተባበር የእነማን ጉልህ ሚና እንደሚበልጥ ኣላዉቅም።

18) እ ኢ አ 1997 ዓም ገደማ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተነሳ ፎቶ ሴረ ቱማ ገዳ ተብሎ ሎስ ኣንጀለስ ከተማ የተደረገ የማህበረሰብ ስብሰባ ዉስጥ በኣጋጣሚ ኣየሁኝ። ፎቶዉን ገና እንደኣየሁኝ ደንቆኝ ከዚህ ፎቶ በላይ ስለ ስልጣኔ አጀማመር የምያሳይ ምን ኣለ ዐይነት ጥያቄ መጠየቄንም ኣልረሳም።

19) ፎቶዉ ከኢትዮጵያ የተላከለት ሰዉ ኣንድ ግዜ እኔ የምኖርበት አከባቢ ለጉብኝት መጥቶ ተገናኝተን እኔ መኪና እየነዳሁኝ ዙርያዉን ኣይቶ ብይ ኩን ብየ ዋቅን ለፈ ቱቄ ፈካተ ያለዉን ብዙ ግዜ ኣስታዉሳለሁ። ዙርያ ክቡን ስያዩት ሰማይ ምድርን የሚገናኝ ስለሚመስል ነዉ።

20) እዚህ መድረክ ላይ ሰዎች መለኮትን ፍሩ ብዬ ኣንድ ርዕስ ጀምሬ ነበር።

21) ኣንድ ርዕስ ስር የሆረስን ኣንድ አስተያየት ኣንብቤ ኣማኝ ከሆንክ ብዬ መልስ ሰጠሁት።

22) ሆረስ መልስ ሲመልስ ዶክተር ስለሺ በቀለ እግዝኣብሔር ሲል የምያሳይ ቪድዮ ለጠፈ።

23) እኔ ኣማኝ ከሆንክ ማለቴን እና መልሱ ዉስጥ ዶክተር ስለሺ በቀለ እግዝኣብሔር ሲል መሰማቱን በደንብ ልብ ይበሉ።

24) እኔ ቪድዮዉ መኖሩን ሳላዉቅ በፊት ነዉ ኣማኝ ከሆንክ ያልኩኝ። ቪድዮዉን ሳይ በቅጽበት ያስታወስኩኝ ተዓምራዊ በሚመስል ሁኔታ ከዶክተር ስለሺ በቀለ ጋር እግረመንገዱን መገናኘታችን ነዉ።

25) ጻድቆች ኣይቀጣጠሩም የሚባል የሰማሁ ቢሆንም እዚህ የጠቀስኩኝን አስተያየት ልዉዉጥ ሳስታዉስ ኦምኒፕረዘንት ስለ ተባለዉ ጽንሰሀሳብ ያስታዉሰኛል።

ይህን ሁሉ ታሪካዊ ሐቆች እዚህ የምጽፍበት ምክንያት ኣንድ ብቻ ነዉ። ይህን ታሪካዊ ሐቆች ማንበብ የሚችል ኢትዮጵያ ሆነ ኤርትራ ዉስጥ ምሁር ሆነ መንፈሳዊ መሪ ኣለ ወይ ለማለት ነዉ።

ልብ ከተባለ የደርግ ዘመን የተቀሰመ ዕዉቀት እስከዚህ ዘመን ተዓምራትን የምያስቆጥር እግዝኣብሔር ኣለ እና እግዝኣብሔር ዬለም ክርክርን ያካትታል።

የደርግ ሃጥዓት ኣምባገነንነቱ ነበረ። ኢትዮጵያ ትቅደም ማለቱ ጽድቅ ነበረ።

ከኢትዮጵያ ነፃ ኣዉጪዎች ነን ባሉ ተዋከበ።

የደርግ ዘመን የተቀሰመ ዕዉቀት ሃገር ዉጪ ተዋክቧል ማለት ይቻላል።

የዚህ ዘመን ሌላ ማዋከብ ተዓምራትን የሚያሳይ እግዝኣብሔር ኣለ የሚልዉ እግዝኣብሔር ዬለም በሚሉ ኢትዮጵያዊያን ነን የሚሉ መሆኑ ነዉ።

በተያያዥ ገዳ የሚሉ እና ገዳም የሚሉ የጥንት ኢትዮጵያ ማህበረሰቦች መተባበር ሳይሆን ለየጎራ መሆን ያሳዝናል።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7623
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የሳን ሚጌል ካሊፎርኒያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ገዳም

Post by Naga Tuma » 31 May 2026, 18:25

Horus wrote:
29 May 2026, 21:50
በምሁር አክሊል ጉራጌ ያለው ታላቁ ምሁር ኢየሱስ ገዳም!
ይህኛዉን ኣሁን ኣንብቤ እጅግ ተገረምኩኝ።

እየሱስ ገዳን ያዉቅ ነበር ማለት ጀመርክ?

ያታላቁ ፈረዖ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ፕሮፌት ሙሴ ወይም ነብዩ ሙሳ የተባለዉ ገዳም ያለዉ ዬት እንደሆነ ታዉቃለህ?

Post Reply