Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 25 May 2026, 20:40

ሰዎች አብረው ለረጅም ጊዜ ሲኖሩ የጋራ መገለጫ ይመሰርታሉ፣ ቋንቋቸውና አመጣጣቸው እንኳን የተለያየ ቢሆንም። ለዚህ ነው ሰላማዊ የተባሉ ሃገሮች ሁሉ የጋራ መለያ ወይንም መታወቂያ ያላቸው። የትህነግ ካድሬዎች ስሟን እየጠቀሱ የሚያጭበረብሩባት ስዊዘርላንድ እንኳን ህዝቧቿን የሚያስተሳስር ናሽናል አይዴንቲቲ አላት፥ የብሄራዊ መዝሙራቸው፣ መስቀለኛው ሰንደቅ ዓላማቸው፣ ገለልተኝነታቸውና አብሮ ለመኖር ፈቃደኝነታቸው።

ወያኔ በኢትዮጵያ የተከለችውና ፒፒ ያስቀጠለችው የክልል አስተሳሰብ ግን ምንም አይነት የጋራ እሴት እንዳይኖር፣ ህዝቦች ከጎጣቸው ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ ቀፍድዶ የሚይዝ፣ ፖለቲከኞችን ብቻ የሚጠቅምና በተለይ አናሳ ብሄረሰቦችን አቅም የሚያሳጣ አሰራር ነው።

ዛሬ በየክልሉ እየሄድክ የኢትዮጵያ የጋራ መለያ ምንድነው ብለህ ብትጠይቅ የተለያየ መልስ ነው የምታገኘው። ህዝቦች የጋራ መገለጫቸውን እስካላዳበሩ ድረስ ተነቃንቆ የሚወልቅ እንጂ ጠንካራና ዘለቄታዊ ሃገር ሊመሰርቱ አይችሉም።
Last edited by Selam/ on 26 May 2026, 00:47, edited 1 time in total.

Odie
Member+
Posts: 8335
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Odie » 25 May 2026, 20:58

ነገሩ የተበላሽው አገሪቱ በአንድ ጉልበተኛና አጭበርባሪ መልክ ተጠፍጥፋ ተስርታ የስለሞን ዝርያዎች መንገሻ የተደረገች እለት ነው!

ከዚያን ጊዜ ጀንምሮ ነው በተለይም የሶስት ጎሳዎች እኔ እበልጥ እኔ ልግዛህ እኔ የተጧጧፈው!

አሁንም ጫካ ያለውና አኩርፎ የተደበቀው የኔ ንፅሁ ደም ዘር ነው አገሪቱ ላይ ብርሃን የሚፈነጥቀው:: በታሪኬ ይህች አገር የኔነች እያለ ሌላውን እየስደበ የአገር ልጆችን አንጡራ ደም እያፈስስ ያለው!

The only solution is to admit past wrong doings apologize where necessary, forgive and reconcile pluse REIMGINE and creat a forward looking country proud of its diverse cultural and ethnics identity with unity than bringing back the dead ልሙጥ country.

Of course this is a talk only and who ever owns the tank and the bank will have to agree to the direction the country should be going and stoping all animosity!

Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 25 May 2026, 22:33

ሃገር በጎጥ ቡድን በተሸነሸነ ህዝብ አይገነባም፣ በተለይ በትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ በሆነ ህብረተሰብ መካከል። ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው የግለሰብ መለያ ቢኖረውም፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በዘር ግንድ ታጥሮ እንዲኖር ስለሚገደድ።

የውሃ ጎርፍ ሊወስደው ሲል ነፍሱን ያዳናትን የሌላ ጎሳ ሰውን እንኳን በሰብአዊነት ደረጃ ቢያከብረውም፣ በህብረተሰብ ጫና ምክንያት ወዳጁ እንዳያደርገው ይገደዳል። “በርበሬና ሽሮ ከእነሱ አትግዙ” ማለት፣ ዋጋቸው የራስህ ጎጥ ከሚሸጥበት ዋጋ ያነሰ ቢሆንም የነፃ ገበያ አስተሳሰብ አያስፈልግህም ብሎ የግለሰብ መብትን መንፈግ ማለት ነው። “ከእነሱ ወገን ሚስት አታግቡ” ማለት፣ በምግባሯና በአስተሳሰቧ ብትጣጣሙም፣ እርምጥምጥም ያለችውን የራስህን ወገን ብቻ አግባና ተጠናቀቅ ማለት ነው።

ይኸ በጣም የታመመ ህብረተሰብ መገለጫ ነው። አስተዋይና በዕውቀት ከሰለጠነው እጩ ይልቅ፣ ደደብና የምትጠላውም ቢሆን የራስህ ጎጥ የሆነውን ሰው ብቻ እንድትመርጥ ያስገድድሃል። በተለያዩ ዘሮች ለደመቀው የአርሰናል ቡድን ድጋፍህን ቀንና ለሊቱን ሙሉ እየሰጠህ፣ ከጎጥህ አጥር ውስጥ መውጣት ካልቻልክ፣ ተፈጥሮ የበደለችህ ድፍን ነህ።
Last edited by Selam/ on 26 May 2026, 00:54, edited 3 times in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 25 May 2026, 22:52

ለጎጠኞች መጥፎ ዜና:

Right
Member+
Posts: 5043
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Right » 25 May 2026, 23:37

ነገሩ የተበላሽው አገሪቱ በአንድ ጉልበተኛና አጭበርባሪ መልክ ተጠፍጥፋ ተስርታ የስለሞን ዝርያዎች መንገሻ የተደረገች እለት ነው!
Grievances of the past. How is that going to deal with the present unbelievably complicated ethnic division? And it shows how society is deeply affected by ethnic politics when the very people who are going to be hurt by the policies namely the ethnic minority groups focused on the wrong agenda.

The three main ethnic groups will be irrelevant if ethnic politics and federalism is removed. Individual freedom a.k.a. Charter of human rights will equalize every citizen of the nation regardless of gender, race, origin and unnecessary labels legally. Those who violates the right of citizens using gender, race, origin, ethnic group etc will be accountable in the courts of law.
How about agreeing on that & putting our attention in achieving it?

This is by far a very educative and helpful thread that good intentions people should join.

Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 26 May 2026, 01:15

የዓለምን የማህበራዊ፣ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራና የስፖርት እንቅስቃሴ የሚከታተል ሰው በጎጥ ፖለቲካ ውስጥ ሲጨማለቅ ሳይ አዝናለሁኝ።

ምሳሌ ልጥቀስ፣ የሊቨርፑልን የእግር ኳስ ቡድን ቲፎዞዎች ተከታትላችሁ ከሆነ፣ ሞ ሳላ ጎል ባስቆጠረ ቁጥር ስሙን ከፍ እያደረጉ ይጠራሉ። ወደ መካ አቅጣጫ አጎንብሶ መሬት ሲስምም፣ እዳንተ ሙስሊም እንሁን እያሉ ይዘምራሉ። እንደሚታወቀው ሊቨርፑል በቀኝ አክራሪዎችና ሙስሊም ጠሎች የተወጠረ ከተማ ነው። ስፖርት ግን ሃይማኖትና ዘርን ሳይቆጥር ሰዎችን በሌላ ደረጃ ያስተሳሰረ የጋራ መታወቂያቸው ሆነ፤ በዚያም የተነሳ በከተማው ውስጥ የነበረው ጥላቻ በከፍተኛ ደረጃ ቀነሰ።

ሰዎችን ከቋንቋቸው፣ ከሃይማኖታቸውና ከጎጣቸው ውጪ የሚያስተሳስሩዋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፣ ይኸን ለመረዳት ሁሉም ራሱን መፈተሽና ፈጣሪ የሰጠውን ልቦና መመርመር ይገባዋል።

Odie
Member+
Posts: 8335
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Odie » 26 May 2026, 04:53

Right wrote:
25 May 2026, 23:37
ነገሩ የተበላሽው አገሪቱ በአንድ ጉልበተኛና አጭበርባሪ መልክ ተጠፍጥፋ ተስርታ የስለሞን ዝርያዎች መንገሻ የተደረገች እለት ነው!
Grievances of the past. How is that going to deal with the present unbelievably complicated ethnic division? And it shows how society is deeply affected by ethnic politics when the very people who are going to be hurt by the policies namely the ethnic minority groups focused on the wrong agenda.

The three main ethnic groups will be irrelevant if ethnic politics and federalism is removed. Individual freedom a.k.a. Charter of human rights will equalize every citizen of the nation regardless of gender, race, origin and unnecessary labels legally. Those who violates the right of citizens using gender, race, origin, ethnic group etc will be accountable in the courts of law.
How about agreeing on that & putting our attention in achieving it?

This is by far a very educative and helpful thread that good intentions people should join.
Good you have expressed yourself in a civil way.
That should have been the way people should be communicating without slurs!
I in fact am not an ethnic politics supporter at all. I am merely responding in kind to verbal abuse of my ethnic origin and culture. As simple as that. No one should be harassed with ethnic slurs for expressing owen idea. No one should be harassed for sticking to a different idea or even for supporting the government. That is the right of self expression on this forum as far as free speech is concerned and legal limit is exercised.
My best wish for Ethiopia would be to abandon ethnic politics. Move to some sort of geographical federation based on factors such as history etc. Federartion could be best for better adminstration and grassroots development as the country is huge and centralized government may be inefficient for running the country. I don’t like regional militias which should be changed to capable regional police and national defence force only.
I don’t support Fano now because of ideology and only “ pure amhara “ mantra. If it has ethiopian solution, it should be inclusive. Also it should distance itself from feudal sentiments, naming itself after past oppressive regimens and using such a rhetoric. Obviously there are segments of society that don’t like that specially those who believe past systems were oppressive e.g Oromo and Sidama nationalists, Tigre nationalists etc. If Fano were ideologically strong, by now it should have known the political fault lines of the nation and stretch out hand to everyone and come with healing solution than falling back to past history of kings and feudal system.
I am amazed by PP development initiatives despite hiccups. The prime minster deserves credit for handling the complex political issues of the country ethnically fractured by EPRDF and working under the shadow of the then TPLF dragon. I appreciate the transformation of Addis, other cities, mega projects and technology initiatives privatization which all showed Ethiopia can really be modernized.
However PP has to go a long way much in improving political space building institutions and promoting citizen right as well as securing peace and willing to talk to rebels plus working with opposition.
Also some ethiopian intellectuals believe ethnic politics in itself may not be bad but the way it is executed in ethiopia including article 39 and not implementing the right to significant other ethnics is a major flaw. The ethnic right is given to some but denied to others. Remember, banning ethnic politics in Ethiopia will erase ethnic sentiments overnight in Ethiopia. Finding a peaceful solution to the sentiments will result in a better outcome than instituting a unitary gov that squashes the ethnic question. Legitimate Ethnic questions may remain and need to be handled amicably arms the country unfortunately had ethnic fault lines and grievances in the past as a result of hammering the nation into one identity.

Whether Ethiopia follows unitary, regional federated or ethnic federated country the right to expression of ethnic and cultural identity may have to be preserved in a way that does not compromise unity. Ethnic spoken languages, multilingual national language, school at least primary with mother tongue should be allowed.
The problem is we are not in a stage to be able to pick a menus how to improve governance and politics in Ethiopia. I believe Dr Abiy is keen in preserving Ethiopian unity he is strongly Ethiopian who is surrounded by may be some Oromo Nationalist old guards dictating his way. Don’t forget the Oromo Nationalists have a grieviance saying Amhara based rule ran the country for long and Tigre for 30 years and Oromo should get chance for a while. I have no problem with that as far as they did the right thing. But any Amhara or Tigre opposition hoping to lead the country should reach out to all progressive elements of other ethnics specially Oromo and try to hammer out a more inclusive political ideology and strategy.

Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 26 May 2026, 06:33

የሰው ልጅ ማህበራዊ እንሰሳ ነው የሚባለው እውነት ነው። በሆነ ነገር ዙሪያ እስከተሰባሰበ ድረስ፣ ሁልጊዜም የራሱን ቡድን አብልጦ ይደግፋል። ይኸም ማለት፣ በሃይማኖት መለያ ካሰባሰብከው፣ የላላ ወይንም የተንሻፈፈ እምነት እንኳን ቢኖረውም፣ የራሱን ቡድን አባላት ይደግፍና ሌሎች ሃይማኖቶችን ያለ ምንም ምክንያት ይጠላል፣ ይጠየፋል። በቋንቋ ወይንም በጎሳ ስታሰባስበውም ውጤቱ ተመሳሳይ ነው።

በስፖርት ደግሞ ከዘርና ከሃይማኖት በላይ የዘለለ የቡድን ፍትጊያ አለ። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ስታድየም ሁልጊዜ ፀብ ይፈጥሩ ነበር። ቡድናቸው ቢሰንፍም የሌላውን ቡድን ከመጥላት ወደ ኋላ አይሉም። የአውሮፓና ደቡብ አሜሪካ ደጋፊዎች እስከ በጩቤ መዘናጠል ደርሰዋል። ዌስት ሃምና ቼልሲ ሲጋጠሙ ሁልጊዜም ቀውጢ ነው የሚሆነው። ጋላታሰራይና ሊቨርፑል ሲጋጠሙ የተፈጠረውን አይተናል፣ ጀርመንና ኔዘርላንድም እንደዚሁ። በቦሰተኑ ሬድ ሶክስና በኒው ዮርኩ ያንኪ ደጋፊዎች መካከል ያለው የከረረ ጥላቻ እስከ አሁን አልተቋጨም።

በንግዱም ሰዎች ተቧድነው በህዝብ መካከል ልዩነት ይፈጥራሉ። ለምሳሌ የጀርመኑ ትሬደር ጆ እና አልዲ በወንድማማቾች አለመስማማት ምክንያት የተከፈለና በኋላም አንተ ከእነዚህ ከተማዎች ውጪ እንዳትንቀሳቀስ፣ እኔም ወደዚያ አልደርስም ተባብለው የተከፋፈሉ ድርጅቶች ናቸው። አዲዳስና ፑማም እንደዚሁ። እንዲያውም የከተማው ህዝብ በሁለት ተከፍሎ፣ አንዱ አዲዳስ ሌላው ደግሞ ፑማ ጫማ ብቻ ነበር የሚያደርገው። አንዱ ከሌላው ጋር የፍቅር ወዳጅነት መመስረትም በፍፁም አይችልም ነበር። በተመሳሳይ ዛሬም በፖለቲካ ቡድን ላይ የተመሰረተ ዴቲንግ አፕ dating app ተፈጥሯል።

ይኸንን ሁሉ ምሳሌ ያመጣሁት ሁለት ነገሮችን ለማሳየት ነው:
1 - ሰዎችን በሆነ የቡድን አጥር ውስጥ ከልሎ፣ ከዚያ ውጪ ያሉት ሌሎቹ ሁሉ ከሰውነት ደረጃ ያነሱ ዕርጉም እንደሆኑ አድርጎ ማሳመንና ራዲካላይዝ ማድረግ ይቻላል።

2 - የሰዎችን በቡድን የማሰብ ዝንባሌ ከጎጥና ሃይማኖት ውጪም ማርካት እንዲሁም ለጥሩም ለመጥፎም አላማ መጠቀም ይቻላል።

በእኔ አመለካከት ኢትዮጵያውያኖችን ሊያስተሳስሩ የሚችሉ ብዙ የጋራ መልካም ነገሮች አሉ ፈቃደኛነቱ ካለ።
Last edited by Selam/ on 26 May 2026, 06:56, edited 2 times in total.

Odie
Member+
Posts: 8335
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Odie » 26 May 2026, 06:55

Selam/ wrote:
26 May 2026, 06:33
የሰው ልጅ ማህበራዊ እንሰሳ ነው የሚባለው እውነት ነው። በሆነ ነገር ዙሪያ እስከተሰባሰበ ድረስ፣ ሁልጊዜም የራሱን ቡድን አብልጦ ይደግፋል። ይኸም ማለት፣ በሃይማኖት መለያ ካሰባሰብከው፣ የላላ ወይንም የተንሻፈፈ እምነት እንኳን ቢኖረውም፣ የራሱን ቡድን አባላት ይደግፍና ሌሎች ሃይማኖቶችን ያለ ምንም ምክንያት ይጠላል፣ ይጠየፋል። በቋንቋ ወይንም በጎሳ ስታሰባስበውም ውጤቱ ተመሳሳይ ነው።

በስፖርት ደግሞ ከዘርና ከሃይማኖት በላይ የዘለለ የቡድን ፍትጊያ አለ። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ስታድየም ሁልጊዜ ፀብ ይፈጥሩ ነበር። ቡድናቸው ቢሰንፍም የሌላውን ቡድን ከመጥላት ወደ ኋላ አይሉም። የአውሮፓና ደቡብ አሜሪካ ደጋፊዎች እስከ በጩቤ መዘናጠል ደርሰዋል። ዌስት ሃምና ቼልሲ ሲጋጠሙ ሁልጊዜም ቀውጢ ነው የሚሆነው። ጋላታሰራይና ሊቨርፑል ሲጋጠሙ የተፈጠረውን አይተናል፣ ጀርመንና ኔዘርላንድም እንደዚሁ። በቦሰተኑ ሬድ ሶክስና በኒው ዮርኩ ያንኪ ደጋፊዎች መካከል ያለው የከረረ ጥላቻ እስከ አሁን አልተቋጨም።

በንግዱም ሰዎች ተቧድነው በህዝብ መካከል ልዩነት ይፈጥራሉ። ለምሳሌ የጀርመኑ ትሬደር ጆ እና አልዲ በወንድማማቾች አለመስማማት ምክንያት የተከፈለና በኋላም አንተ ከእነዚህ ከተማዎች ውጪ እንዳትንቀሳቀስ፣ እኔም ወደዚያ አልደርስም ተባብለው የተከፋፈሉ ድርጅቶች ናቸው። አዲዳስና ፑማም እንደዚሁ። እንዲያውም የከተማው ህዝብ በሁለት ተከፍሎ፣ አንዱ አዲዳስ ሌላው ደግሞ ፑማ ጫማ ብቻ ነበር የሚያደርገው። አንዱ ከሌላው ጋር የፍቅር ወዳጅነት መመስረትም በፍፁም አይችልም ነበር። በተመሳሳይ ዛሬም በፖለቲካ ቡድን ላይ የተመሰረተ ዴቲንግ አፕ dating app ተፈጥሯል።

ይኸን ሁሉ ምሳሌ ያመጣሁት የሰዎችን በቡድን የማሰብ ዝንባሌ ከጎጥና ሃይማኖት ውጪም ማርካት እንደሚቻልና ለጥሩም ለመጥፎም አላማ መጠቀም እንደሚቻል ለማሳየት ነው።

በእኔ አመለካከት ኢትዮጵያውያኖችን ሊያስተሳስሩ የሚችሉ ብዙ የጋራ መልካም ነገሮች አሉ ፈቃደኛነቱ ካለ።
The problem is no one is willing so far to try this recipe in Ethiopia. Everybody knows the recipe.
As I said, rivalry ethnic nationalist see one being ruled by the other and fighting for meager resources plus power/glory. They don’t trust one another. To get the upper hand each group trusts its own ethnic group and its paid cronies only. This continues the cycle. Each leader assembles its trustworthy power base to assemble the military and other strong positions to strengthen its power. That base comes from its ethnic stronghold and benefiters. That is the history of Ethiopian rulers and gov systems. The country has not transitioned to modern government where the government base is citizens than ethnic base plus cronies. Mengistu may have tried but he was following toxic socialist system with the old unitarian same tools

Right
Member+
Posts: 5043
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Right » 26 May 2026, 07:17

I am amazed by PP development initiatives despite hiccups. The prime minster deserves credit for handling the complex political issues of the country ethnically fractured by EPRDF and working under the shadow of the then TPLF dragon. I appreciate the transformation of Addis, other cities, mega projects and technology initiatives privatization which all showed Ethiopia can really be modernized.
The PP government is the exact replica of the EPDRF government.
Without a proper structure and infrastructure shiny buildings and street decorations are nothing but are tools of image creation and money laundering.
It was the playbook of the EPDRF government and now conman Abiye is using it, just like many other dictators around the world. The EPDRF built the ring road, the first rail road from Addis to Djibouti,city light rail transit, the incomplete Gerd dam etc in the process they have stolen a lot of money while building their images and tried to hide behind it.

In some cases no harm and in some cases beneficial and in some cases hurting. But it avoids one fundamental thing, built outside a properly placed infrastructure based on one man’s or groups desire with no proper accountability. It is a recipe for disaster.

Having said the above, this thread is about common identity and collective responsibility. It is under the political infrastructure. In my view, unless Ethiopia gets rid off the toxic ethnic ideology and ethnic federalism, it will not move an inch forward. It will regress.
The current government is not only embracing and guarding ethnic ideology, but in the words of the PM, it is non negotiable.
I don’t think Ethiopians fully understands the perils of Ethnic ideology. Getting rid off it should be the number one priority. When I hear people who identified themselves with the smaller ethnic groups see it as their saviour from dominance by the larger ethnic groups, it is mind boggling.
Focus on the subject of this thread.

Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 26 May 2026, 07:36

ሰዎች ሊለወጡ አይችሉም ብሎ ብዙ ምክንያት ከመደርደር ይልቅ ከተቻለ ራስን በቅድሚያ መለወጥ ወይንም ካልተቻለ ዝም ማለት ይመረጣል። ከከፋፋይ የቡድን አስተሳሰብ ቀድመው ሊወጡ የሚችሉት ደግሞ፣ በራሳቸው የተሻለ መተማመን ያላቸውና የመኖር ትርጉሙ በትክክል የገባቸው ሰዎች ናቸው።

ማንነቱን ሌላ ሰው ካልነገረው በስተቀር የህይወቱ ትርጉም የተመሳቀለበትና በራሱ የማይተማመን ሰው ከጎጥ የቡድን ጥላ ስር ለመውጣት ይቸገራል። በተለይ ደግሞ በዕውቀት አነስተኛ የሆነውና ልቡ የብርሃን ፀጋ የተነፈገችበት ህዝብ እራሱን ከቡድን ውጪ ማየት አይችልም። ለጎጠኛ ፖለቱከኞችም ስንቅ ስለሚሆን፣ በአንድ በኩል የራሱን የቡድን እሴቶች እያጋነኑ በሌላ በኩል ደግሞ የሌሎቹን የወል ግድፈቶች እያደመቁ ደፍቀው ይይዙታል እንጂ በግሉ እንዲያስብ አይፈቅዱለትም።

Odie
Member+
Posts: 8335
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Odie » 26 May 2026, 07:48

Selam/ wrote:
26 May 2026, 07:36
ሰዎች ሊለወጡ አይችሉም ብሎ ብዙ ምክንያት ከመደርደር ይልቅ ከተቻለ ራስን በቅድሚያ መለወጥ ወይንም ካልተቻለ ዝም ማለት ይመረጣል። ከከፋፋይ የቡድን አስተሳሰብ ቀድመው ሊወጡ የሚችሉት ደግሞ፣ በራሳቸው የተሻለ መተማመን ያላቸውና የመኖር ትርጉሙ በትክክል የገባቸው ሰዎች ናቸው።

ማንነቱን ሌላ ሰው ካልነገረው በስተቀር የህይወቱ ትርጉም የተመሳቀለበትና በራሱ የማይተማመን ሰው ከጎጥ የቡድን ጥላ ስር ለመውጣት ይቸገራል። በተለይ ደግሞ በዕውቀት አነስተኛ የሆነውና ልቡ የብርሃን ፀጋ የተነፈገችበት ህዝብ እራሱን ከቡድን ውጪ ማየት አይችልም። ለጎጠኛ ፖለቱከኞችም ስንቅ ስለሚሆን፣ በአንድ በኩል የራሱን የቡድን እሴቶች እያጋነኑ በሌላ በኩል ደግሞ የሌሎቹን የወል ግድፈቶች እያደመቁ ደፍቀው ይይዙታል እንጂ በግሉ እንዲያስብ አይፈቅዱለትም።
Rhetoric does not go beyond what it is!
ኢትዮዽያ ባብላጫው የኔ ዘመዶች የባህል ጭማቂ ብትሆን እኔንም ከናንተ የባስ ያደርገኝ ነበር::
The problem is the North south fracture of the country with regard to how Ethiopia is perceived. I said it in other posts. Unless all ethiopians agree on how they perceive Ethiopia means this unintelligible conversation and disagreement will continue. Although most agreed on the continuation of the frame of the country, there always existed a friction on who is Ethiopian, who is more Ethiopian than others and who benefits more in that names in real terms. Many thought and still think they did not equally feel proud of their country or excluded in major issues. Neither did they feel received equal share nor did the country include their culture. That is what took us here in the history of the country and why many rebels go to forest. The rest is a rosey preaching. Politicians have to find a solution to create an inclusive diverse country ethnic based or not where no one feels left behind harassed, looked down or insulted.
I rest my case as I have no appetite to recycle the same idea on and on. What I discussed above is fact.

Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 26 May 2026, 08:42

ይኸንን ሁሉ የምፅፈው ብዙ አንባቢ ስላለ ስለማውቅ እንጂ፣ ለአንድ ወይንም ለሁለት ሰው መልስ ለመስጠት አስቤ አይደለም። እኔ ልቦናዬ የኢትዮጵያ ህዝቦች አስተሳሰብ ግትር ነው በሚል ስንኩል ምክንያት ላይ ብቻ ተጣብቆ እንዲቆዝም አልፈቅድለትም፣ በግሌ ምን ማድረግ አለብኝ ብዬ ራሴን እሞግታለሁ እንጂ።

የዛሬ ዓመት ገደማ አንድ የሚገርም የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት አነብቤ ነበር፣ ምንጩን ተመልሼ ለማግኘት እሞክራለሁ። የማይተዋወቁ ወጣት ተማሪዎችን በሁለት ግሩፕ ከፍለው እያንዳንዳቸው የተወሰነ ስፖርት ቡድን ደጋፊና ፈንድ ሬይዘር እንዲሆኑ አደረጓቸው። እነዚህ ምንም የማይተዋወቁ ልጆች የሌላውን ቡድን ለማሸነፍ ከራሳቸው ኪስ ሳይቀር ገንዘብ አዋጡ፣ ለሌላው ቡድን ያላቸውም ንቀትና ጥላቻ ከረረ።

ይኸም ማለት ጥላቻንም ይሁን ፍቅርን የሚገሩት ዘርና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆኑ የአስተሳሰብ መቃናት ወይንም መንሻፈፍ ናቸው። ሰዎች ደግሞ አስተሳሰብን ወደ በጎ አቅጣጫ የመገራት አቅም አላቸው። ዓብይ አህመድ ብልጭ አድርጎ አጥፍቶታል፤ ጆርጅ ቡሽ መስከረም 11 ላይ ሃገሩን አንድ አድርጎ ነበር፣ ኦባማም እንደዚሁ፣ ማንዴላም ደቡብ አፍሪካን ከእርስ በእርስ ዕልቂት አድኗል፣ ካጋሜም ሩዋንዳን ከመከራ ጉድጓድ ውስጥ አውጥቷል። መድረኩ ከተሰጣቸው ኢትዮጵያንም ሊያክሙ የሚችሉ (ከፖለቲካ ውጪ ያሉ) ሰዎች አሉ ።

Dama
Member+
Posts: 8641
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Dama » 26 May 2026, 09:30

Selam/ wrote:
25 May 2026, 20:40
ሰዎች አብረው ለረጅም ጊዜ ሲኖሩ የጋራ መገለጫ ይመሰርታሉ፣ ቋንቋቸውና አመጣጣቸው እንኳን የተለያየ ቢሆንም። ለዚህ ነው ሰላማዊ የተባሉ ሃገሮች ሁሉ የጋራ መለያ ወይንም መታወቂያ ያላቸው። የትህነግ ካድሬዎች ስሟን እየጠቀሱ የሚያጭበረብሩባት ስዊዘርላንድ እንኳን ህዝቧቿን የሚያስተሳስር ናሽናል አይዴንቲቲ አላት፥ የብሄራዊ መዝሙራቸው፣ መስቀለኛው ሰንደቅ ዓላማቸው፣ ገለልተኝነታቸውና አብሮ ለመኖር ፈቃደኝነታቸው።

ወያኔ በኢትዮጵያ የተከለችውና ፒፒ ያስቀጠለችው የክልል አስተሳሰብ ግን ምንም አይነት የጋራ እሴት እንዳይኖር፣ ህዝቦች ከጎጣቸው ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ ቀፍድዶ የሚይዝ፣ ፖለቲከኞችን ብቻ የሚጠቅምና በተለይ አናሳ ብሄረሰቦችን አቅም የሚያሳጣ አሰራር ነው።

ዛሬ በየክልሉ እየሄድክ የኢትዮጵያ የጋራ መለያ ምንድነው ብለህ ብትጠይቅ የተለያየ መልስ ነው የምታገኘው። ህዝቦች የጋራ መገለጫቸውን እስካላዳበሩ ድረስ ተነቃንቆ የሚወልቅ እንጂ ጠንካራና ዘለቄታዊ ሃገር ሊመሰርቱ አይችሉም።
Resourceless Amara. There would be no reason why a numerous donkey would campaign for unity if it could survive by its own means. Even that in a very self-serving and undemocratic way. Nowhere near the Swiss way.

Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 26 May 2026, 09:54

ይኸ መድረክ ኤርትራውያኖችም እንዲሳተፉ ይጋብዛል፣ ኤርትራዊነታቸውን እስካልደበቁና ልክ ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ አስመስለው የጎሳ ጠብ ለማቀጣጠል የተለመደ ሴራቸውን እስካልሸረቡ ድረስ።

Right
Member+
Posts: 5043
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Right » 26 May 2026, 12:19

an inclusive diverse country ethnic based or not where no one feels left behind harassed, looked down or insulted.
It can’t be diverse and all inclusive if the country is run ethnic based.
If you want an all inclusive country, with freedom and equal rights to all citizens, you have to eliminate ethnic based systems. The whole idea of the introduction of ethnic based politics is to divide and conquer. The European colonizers used the system for centuries to pillage the third world. While banning it in their own countries. South Africa mastered it in the apartheid era.

First, we all have to agree that ethnic politics is toxic and an agenda of the enemy. And we have to educate ourselves and our people accordingly.
That is the starting point.
The next stage to outlaw it and address it through proper governance. Both a political and legal structure decimate it.
That need collective consciousness.
If we don’t act quickly, Africa will set itself for re-colonization. If and when the new colonizers arrive, it will be worst than what Africa has experienced before. Mass extinction is possible.

Dama
Member+
Posts: 8641
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Dama » 26 May 2026, 14:20

Right wrote:
26 May 2026, 12:19

The phrase ethnic politics is the prostitutionalization of the inalienable rights of the conquered and colonized Ethiopian nations to self-determination. They are not ethnics which refers to cultural groups within a larger whole such as Nigerians, Ghaniabs, Ethiopians in US, England or Italy. Ethiopian nations are polities with their own geographic territories, institututiins of self-governance dating back ages. They are polities histories, languages and independent cultures of their own.

Learn facts before you make silly mistakes.

Amara as a numerous herd, doesn't make a lot of sense bullying other Ethiopians for unity. Of course, this has its origin out of the self-realization of resourcelessness of Amara but it should tighten its belt and assume to live by its own resources.

Right
Member+
Posts: 5043
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Right » 26 May 2026, 23:10

rights of the conquered and colonized Ethiopian nations to self-determination.
Doma,
No body will deny the aspirations of the people of Gurage zone for self determination. Just not try to impose it on the rest of us.
You can’t have it both way though. You will be kicked out of Ethiopia and allow to have your own country as long as it is decided by a fair referendum.
You have no idea on what kind of trap you are in.
There will be no baby sitting.

Selam/
Senior Member
Posts: 18309
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by Selam/ » 27 May 2026, 07:10

መለስ ዜናዊ “መርካቶ 1000 ሌቦች አሉ ብለውን፣ 2000 ፖሊሶች አሰለጠንን፣ በስተመጨረሻ 3000 ሌቦች ሆኑ” ብሏል። ያልተረዳው ነገር፣ ፖሊስን በሰፈርና በጎጥ ብቻ ካሰለጠንከው፣ በአካባቢው የተርመጠመጠ ባህል ተውጦ መቅረቱን ነው።

እሱ ዊንጌት በእንግሊዞች ተምሮ ሲያበቃ፣ ሌሎች ኢትዮጵያኖች ግን በሰፈራቸው አዋቂዎች ብቻ እንዲሰለጥኑ ፈረደባቸው። ለዚህ ነው የህዝብ አወቃቀር ፣ ከጎሳ የቡድን አወቃቀር ተሰብሮ መውጣት ያለበት።

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 11070
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: የጋራ መታወቂያ - Common Identity

Post by ethiopianunity » 27 May 2026, 17:52

Right wrote:
26 May 2026, 07:17
I am amazed by PP development initiatives despite hiccups. The prime minster deserves credit for handling the complex political issues of the country ethnically fractured by EPRDF and working under the shadow of the then TPLF dragon. I appreciate the transformation of Addis, other cities, mega projects and technology initiatives privatization which all showed Ethiopia can really be modernized.
The PP government is the exact replica of the EPDRF government.
Without a proper structure and infrastructure shiny buildings and street decorations are nothing but are tools of image creation and money laundering.
It was the playbook of the EPDRF government and now conman Abiye is using it, just like many other dictators around the world. The EPDRF built the ring road, the first rail road from Addis to Djibouti,city light rail transit, the incomplete Gerd dam etc in the process they have stolen a lot of money while building their images and tried to hide behind it.

In some cases no harm and in some cases beneficial and in some cases hurting. But it avoids one fundamental thing, built outside a properly placed infrastructure based on one man’s or groups desire with no proper accountability. It is a recipe for disaster.

Having said the above, this thread is about common identity and collective responsibility. It is under the political infrastructure. In my view, unless Ethiopia gets rid off the toxic ethnic ideology and ethnic federalism, it will not move an inch forward. It will regress.
The current government is not only embracing and guarding ethnic ideology, but in the words of the PM, it is non negotiable.
I don’t think Ethiopians fully understands the perils of Ethnic ideology. Getting rid off it should be the number one priority. When I hear people who identified themselves with the smaller ethnic groups see it as their saviour from dominance by the larger ethnic groups, it is mind boggling.
Focus on the subject of this thread.
Right aka wrong Weyane\ Shabo

Er is owned by Shabo and Weyane no doubt. Is there any doubt that pp is Eprdf#2? Every leadership all of them were part of Tplf Eprdf member! All of them! So you don’t get pigeon egg from snake egg, l am saying it over and over again. Really? In some case Tplf development was beneficial? Which one is beneficial to the population? As for pp, of course the system is tge same and in fact worse, displacing Addis Abebans. It was all revenge against Shewa by foreigners, Tplf, Shabia and Olf. There are no more in a sense of Shewans and Addis Abebans! They have been systematically been uprooted by colonisers supporters, Tplf, Olf and Shabians.

Post Reply