ኢትዮጵያ እጅግ በትንሹም ቢሆን የመፍትሄ መንገድ በመሻትና ጥቂት መፍትሄዎችን በመፍጠር ላይ ያለች አገር ነች ።
ኢትዮጵያ የሚሊዮኖች ድሃ ሕዝብ አገር ነች ።
ኢትዮጵያ የጥቂት ሃብታም ሕዝብ አገር ነች ።
ኢትዮጵያ የዚህ ሁለት ተቃራኒ እውነታዎች ውሁድ (ውህደት) አገር ነው ።
ቴዶ አፍሮ ድሃዋ ኢትዮጵያን ገልጿል ።
ዲለን ፔጅ (ወይም አዶናይ) ሃብታሟን ኢትዮጵያ ገልጿል።
ሁለቱም ፣ ቴዲ አፍሮም ዲለን ፔጅም የኢትዮጵያ ሪያሊቲ ፣ የኢትዮጵያ ገጽታ ናቸው ።
ትልቁ ነገር ፣ እጅግ ትልቁ ነገር የነዚህ ሁለት ተጻራሪ እውነታዎች ሙግትና ፍጭት ሳይታፈኑ መካሄዳቸው ነው !
ድህነት እስካልጠፋ ድረስ ሃብታምነት ብቸኛው እውነታ ሊሆን አይችልም!
ሃብታምነት እስካልተደገፈና እስካልገነነ ድረስ ድህነት ሊጠፋ አይችልም!
እነዚህ 2 የኢትዮጵያ እውነታዎችን መካድ አላዋቂ ሰጎን መሆን ነው።
መፍትሄው ሃብታምነትን ማበረታታት እና ድህነትን ለማጥፋት አንድ ሕዝብ ፣ አንድ ሃስብ ፣ አንድ ሰራተኛ መሆን ነው!
ቴዲ አፍሮ የችግራችን ገላጭ ብርሃን ነው!
ዲለን ፔጅ የስኬታች ገላጭ ተስፋ ነው!
ስለዚህ 2ቱም አንድ ናቸው! ሁለቱም የኢትዮጵያ ውስጥና ውጭ ፣ ፊትና ኋላ ናቸው!