Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15545
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ክርስትና እምነት የአዲስ ኪዳን ሳይታተም በፊት ነበር። ክርስቶስ መጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅስ ነበር።ጀርመናዊ ፕሮቴስታንትን ማርቲን ሉተር በ1534 ዓም 66 መጻህፍት የያዘ ጎደሎ አተመ።

Post by Abere » 15 May 2026, 12:29

ክርስትና እምነት የአዲስ ኪዳን መጻህፍታት ተሰብሰብው ሳይታተሙ በፊት ነበር። የቤተክርስቲያን የሆነው ጌታ እየሱስ መጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅስ ነበር፤ ነብያት ይጠቅሱ ነበር። ጀርመናዊ የማርቲን ሉተር በ1534 ዓም 66 መጻህፍት ብቻ ፕሮቴስታንት/ጴንጤ መጽሀፍ አተመ።

ይህ ጎደሎ መጻህፍት ተመሳስሎ ሙሉ መጻህፍታት አሟልተው ከሚገኙት ጥንታዊ ክርስትና እምነት ማለት ኦርቶዶክስ ክርስትና ጋር በገባየ በመረጨቱ ሃሰታዊ ውይም ጎደሎ ትምህርት እንድስፋፋ አድርጓል። በርካታ የኦርቶዶክስ ምዕምን ከዕውቀት ማነስ የተነሳ ገባያ ላይ መጽሀፍ ቅዱስ ካዩ ዝም ብለው ይገዛሉ። ይህ ስህተት ነው። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይህን ማለፍ የለባትም - ምዕምኑ ጎደሎ መጻህፍት እንዳይ ገዛ እና እንዳይማር መስገንዘብ አለባት። ተኩላ እና በግ በአንድ ቦታ ሊሰማሩ አይገባም።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7512
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ክርስትና እምነት የአዲስ ኪዳን ሳይታተም በፊት ነበር። ክርስቶስ መጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅስ ነበር።ጀርመናዊ ፕሮቴስታንትን ማርቲን ሉተር በ1534 ዓም 66 መጻህፍት የያዘ ጎደሎ አተመ።

Post by Naga Tuma » 15 May 2026, 15:17

አበረ፥

ፀልይ፣ በደንብ ፀልይ፣ የእግዜር ተዓምራዊ አሰራሮች እንዲገለጡልህ።

እኔ የተገለጡልኝን እያሰብኩ እጄን በኣፌ ላይ ስጭን እዉላለሁ። ወደፊት የሚገለጡልኝን ዛሬ ልነገርህ ኣልችልም።

ይህ የአደባባይ ወሬም ኣይዴለም።

በደንብ ከፀለይክ በኋላ ለሌላ ሰዉ ብለህ ሳይሆን ለራስህ ታሪክ ብለህ ለኣንድ ጥያቄ ብቻ መልስ ኣግኝ።

ጥያቄዉ እግዜር ኣለ ወይስ ዬለም?

በደንብ ፀልየህ ያገኘሀዉ መልስ ዬለም ከሆነ የእኔን ምክር እዚሁ ላይ ኣቁም። ምንም ኣይጠቅምህም።

በደንብ ፀልየህ ያገኘሀዉ መልስ ኣለ ከሆነ የኣንተን ኣዉቃለሁ ትምህርት ይዋል ይደር ብለህ የእግዜር ተዓምራዊ አሰራር እንዴት እንደሆነ ለማጤን ጣር።

ለእኔ ተገለጠልኝ ብዬ የማስበዉ የምያመለክተዉ ኣንዱ በታሪክ ተጽፎ አስርቱ ትዕዛዛት ተብሎ የተቀመጠ ነዉ።

የጥንት ዘመኑ መገለጥ ለቀዳማዊ ነብይ ለካ ኣንተ ነህ! የተባለ የጥንት ኢትዮጵያ ቃሉ ከስደት በኋላ ፕሮፌት ሙሴ የተባለ ነዉ።

በዚህ የፍርድ ዘመን የተባለዉ ግዜ ለመገለጡ ምልክቶች ኣሉ ብዬ ስለማስብ ነዉ ለመምከር የምለፋዉ።

ለዚህ ቁልፍ ምልክት እግዜር ለመኖሩ ከበቂ በላይ ተዓምራዊ ክስተቶች ኣሉ ማለት እና እግዜር ዬለም ማለትን መስማትህ ወይም ማንበብህ ብቻ በቂ ነዉ።

የእግዜር ኣለ እና ዬለም ክርክር የእግዜር እና የተንኮለኛዉ ዳያብሎስ ግብግብ ነዉ።

የኣንተ ኣዉቃለሁ ብሎ ትምህርት እዚህ ግብግብ ዉስጥ ነዉ።

ክርስትና ማለት ጥንት ዘመን ለኢትዮጵያ ነብይ የተገለጠ እና በዚህ ዘመን እየተገለጠ ያለ መሃል ያኖረ ማለት ነዉ።

ይህ ዕዉነታ ብቻ ክርስትና ዉስጥ ያሉ ዘበቶች ሳይታሙ ክርስትና ከዚህ ዘመን በኋላ ሃያ ዓመታትን የሚሰነብት ነዉ ወይስ የስደት ንስሃ ከሃያ ዓመታት ወዲህ የሚሰማ ይሆናል የሚል ጥያቄን ያመጣል።

የስደት ንስሃ ተሰማ ማለት እግዜር ኢትዮጵያን ታረቃት ማለት ይሆናል ብዬ ኣስባለሁ።

የጥንት ኢትዮጵያ ቀዳማዊ ነብይ ከስደት በኋላ ለእስራኤል ፕሮፌት ሆኖ ከእግዜር ጋር በቶራ በኩል አኮርድ ያስቀመጠላት እስራኤልም በዚህ ዘመን እግዜር ዬለም ያለች ከሆነ ንስሃዉ ሲሰማ ከእግዜር ጋር ትታረቃለች ማለት ይሆናል።

ስምሽን ሳታዋርጂ ዕዉነቱን ኣዉጪ የተባለች እስራኤል ፕሮፌት ሙሴ ትክክለኛ ስሙ ፕሮፌት ሙጬ ነበር ማለትም ትጀምር ይሆናል።

ትክክለኛ ስሙ ፕሮፌት ሙጬ ነበር ከተባለ ደግሞ እየሱስ እራሱ በተዓምር ቢመለስ ምስክርነቱ እናንተ እስራኤላዊያን ከኢትዮጵያ ኣላወጣሁዋችሁም ወይ ሳይሆን እኛ እስራኤላዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንይ የሚል ይመስለኛል። ቴዎድሮስ ካሳሁን ዞሮ መጀመርያ ብሎ ነበር።

ፍቃዱን የምያዉቀዉ ተዓምራትን የምያሳየዉ እና የምያሰማዉ እግዜር ነዉ።
“Abere” wrote: ክርስትና እምነት የአዲስ ኪዳን ሳይታተም በፊት ነበር። ክርስቶስ መጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅስ ነበር።ጀርመናዊ ፕሮቴስታንትን ማርቲን ሉተር በ1534 ዓም 66 መጻህፍት የያዘ ጎደሎ አተመ።
Abere wrote:
15 May 2026, 12:29
ክርስትና እምነት የአዲስ ኪዳን መጻህፍታት ተሰብሰብው ሳይታተሙ በፊት ነበር። የቤተክርስቲያን የሆነው ጌታ እየሱስ መጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅስ ነበር፤ ነብያት ይጠቅሱ ነበር። ጀርመናዊ የማርቲን ሉተር በ1534 ዓም 66 መጻህፍት ብቻ ፕሮቴስታንት/ጴንጤ መጽሀፍ አተመ።

ይህ ጎደሎ መጻህፍት ተመሳስሎ ሙሉ መጻህፍታት አሟልተው ከሚገኙት ጥንታዊ ክርስትና እምነት ማለት ኦርቶዶክስ ክርስትና ጋር በገባየ በመረጨቱ ሃሰታዊ ውይም ጎደሎ ትምህርት እንድስፋፋ አድርጓል። በርካታ የኦርቶዶክስ ምዕምን ከዕውቀት ማነስ የተነሳ ገባያ ላይ መጽሀፍ ቅዱስ ካዩ ዝም ብለው ይገዛሉ። ይህ ስህተት ነው። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይህን ማለፍ የለባትም - ምዕምኑ ጎደሎ መጻህፍት እንዳይ ገዛ እና እንዳይማር መስገንዘብ አለባት። ተኩላ እና በግ በአንድ ቦታ ሊሰማሩ አይገባም።

Abere
Senior Member
Posts: 15545
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ክርስትና እምነት የአዲስ ኪዳን ሳይታተም በፊት ነበር። ክርስቶስ መጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅስ ነበር።ጀርመናዊ ፕሮቴስታንትን ማርቲን ሉተር በ1534 ዓም 66 መጻህፍት የያዘ ጎደሎ አተመ።

Post by Abere » 16 May 2026, 19:48

ማንኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምዕምን በቤቱ ውስጥ ትክክለኛው የተሟላው ክርስቲያናዊ 81 መጽሀፍ ቅዱስ ከሌለው ክርስቲያንነኝ ማለት አይችልም። ዝም ብሎ ከመንገድ ላይ እያፈሰ የሚገዛው መጽሀፍ ቅዱስ ሳይሆን ፓምፍሌት ነው። ቄስ ሁኖ ጎደሎ መጽሀፍ ቅዱስ የሚያስተምር ወይም የያዘ ቄስ ሳይሆን ተኩላው ጴንጤ ነው። በመጨረሻው ዘመን ብዙ ሀሰተኛ መምህራን ይነሳሉ እንዳለው ጌታችን፤ ተጠንቀቁ፤ተጠበቁ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7512
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ክርስትና እምነት የአዲስ ኪዳን ሳይታተም በፊት ነበር። ክርስቶስ መጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅስ ነበር።ጀርመናዊ ፕሮቴስታንትን ማርቲን ሉተር በ1534 ዓም 66 መጻህፍት የያዘ ጎደሎ አተመ።

Post by Naga Tuma » 18 May 2026, 15:05

የአሜሪካን አንደር ጎደ ፕለጅ ዛሬ ሰምቼ ለመጀመርያ ግዜ ያጤንኩኝ፥

ጎድ መሠረቱ የኢትዮጵያ ቃል ነዉ።
እየሱስ መሠረቱ የእስራኤል ቃል ነዉ።

ይህ የኢትዮጵያ ኣምላክ ኣሸናፊነትን የምያመለክት ኣንዱ መለኮታዊ ምልክት ኣይዴለም?

በምን ምክንያት ነበር ኢትዮጵያን የነካ ማለት የተጀመረዉ?

Post Reply