Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11805
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የፓትርያርኩ ጥሪ "አቁሙ! .... በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ !"

Post by MINILIK SALSAWI » 07 May 2026, 01:32

" በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ ! " - ቅዱስነታቸው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ የረክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ ዛሬ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ተጀምሯል ይህን አመስልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።






Naga Tuma
Member+
Posts: 7512
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የፓትርያርኩ ጥሪ "አቁሙ! .... በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ !"

Post by Naga Tuma » 07 May 2026, 22:59

እንደ ኣንድ ግለሰብ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ከርቀት ሆኖ አስተያየት መስጠት የማያምርብኝ ሊመስል ይችላል።

ከርቀት ሆኜ ሃይማኖትን የሚመለከት አስተያየት ኣንብቤ የቻልኩትን ያህል ምክር ሳስተላልፍ የሰነበትኩ ስለሆነ እጅግ ገንቢ የሆነ አስተያየት ያለኝ ይመስለኛል።

ማርያም በእግዝኣብሔር ፍቃድ ኣዳኝ ወለደች ተብሎ ለሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ የተሰበከ ሃገር ኢትዮጵያ ዉስጥ በዚህ የስምንተኛዉ ሺህ ዘመን የተባለ ግዜ እግዝኣብሔር ኣለ ብሎ ማሰብ የኣዕምሮ መቃወስ ነዉ የሚል ኢትዮጵያዊ መኖሩ ዕዉነትም ስምንተኛዊ ሺህ የተባለዉ ዘመን ይመስላል።

እንደ መጀመርያም ሳይሆን፣ እንደመጨረሻም ሳይሆን፣ እንደመካከለኛዉ ብላኝ ኣለች ኣሉ የባቄላ እሸት።

እኔ ይህን የኣዕምሮ መቃወስ ነዉ የተባለዉን አስተያየት ሳላነብ በፊት ሰዎች መለኮትን ፍሩ ብዬ እዚህ መድረክ ላይ መክሬኣለሁ።

እኔ የህዳሴ ወይም ሬይነሳንስ የሚባለዉ ሰዉ ነኝ።

ህዳሴ ሲባል ከምን ተነስቶ፣ ምን ተይዞ ነዉ ህዳሴ የሚባል ጥያቄን ያመጣል።

አምስት መቶ ዓመታት በፊት የኣዉሮፓ ህዳሴ ወይም ሬይነሳንስ የተባለዉ የጎደስ አቴና ዘመን የጥንት ግሪክ ስልጣኔ ስንቶች ዘመናትን በጨለማ ዉስጥ ኖሮ ከተገኘ በኋላ ነዉ።

እኔ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ህዳሴ እና ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የምለዉ የፈረዖ አክናተን ዘመን የጥንት ኢትዮጵያ ስልጣኔ ስንቶች ዘመናትን በጨለማ ዉስጥ ኖሮ ከተስተዋለ በኋላ ነዉ።

የፈረዖ አክናተን ዘመን የጥንት ኢትዮጵያ ስልጣኔ ስንቶች ዘመናትን በጨለማ ዉስጥ መኖር ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ቅርስ አስርቱ ትዕዛዛት እራሱ ሃጥኣተኛ ፈረዖ የተባለዉ ነበረ የሚል ታሪክ መገኘቱ ነዉ።

ይህ ማለት እስራኤላዊ ሙሴ የተባለዉ የጥንት ኢትዮጵያ ፈረዖ ነበር ማለት ይሆናል።

ይህንን ታሪክ እኔ ከሃያ ዓመታት በፊት ኣንብቤ የደረስኩበት ሲሆን የኢትዮጵያዊ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ከሃምሳ ዓመታት በፊት የደረሰበት መሆኑን በቅርብ ዓመታት ሰምቻለሁ።

የሃይማኖት መሪዎች ከሃይማኖት መጽሓፍ ዉጪ ወጥተዉ የሚመራመሩ ኣይመስለኝም። ካልተሳሳትኩኝ ምክራቸዉ ኣትመራመሩ ነዉ።

የህዳሴ ወይም ሬይነሳንስ ሰዎች ከሃይማኖት መጽሓፍ ኣፈንግጠዉ የሚመራመሩ ናቸዉ።

ተመራምረዉም ኣዳዲስ ግኝቶችን ኣግኝተዉ መምከር የሚጀምሩ ናቸዉ።

ግኝቶቻቸዉ የሃይማኖቱን መሠረት የሚነቀንቁ ናቸዉ።

ለምሳሌ የአስርቱ ትዕዛዛት አባት የጥንት ኢትዮጵያ ታላቅ ፈረዖን ግፈኛ ብሎ ማስተማር፣ የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ የነበረን እስራኤላዊ ነበር ማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን መሠረት የሚነቀንቅ ነዉ።

ይህን ያህል ኣዲስ ነገር ሲሰማ የጥሞና ግዜ ያስፈልገናል ማለት ጥልቅ የሆነ አመራር ይመስለኛል።

ይህም ብቻ ሳይሆን በዚህ ዘመን እግዝኣብሔር ኣለ ብሎ ማሰብ የኣዕምሮ መቃወስ ነዉ የሚሉ ኢትዮጵያዊያን መኖራቸዉ የጥሞና ግዜ ያስፈልገናል የምያስብል ይመስለኛል።

በተጨማሪ እኔ ሰዎች መለኮትን ፍሩ ያልኩኝ መለኮታዊ ምልክቶች የሚመስሉትን በመጻፍ ነዉ።

ለዚህም የጥሞና ግዜ ያስፈልገናል የምያስብል ይመስለኛል።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ቃልቻዎች እና ቃሉዎች የእግዝኣብሔር መላዕክታት ነበሩ የሚል አስተያየት ኣንብቤ የጨለማ ዘመን ዉስጥ መኖር ኣንዱ ምሳሌ ይሄ ነዉ ኣስብሎኛል።

ስለዚህ በእኔ አስተያያት የዚህ የጥሞና ግዜ ኣንገብጋቢ ጉዳይ መለኮታዊ ምልክቶች ኣሉ ወይስ ዬሉም የሚለዉ ጥናት የምያስፈልገዉ ሲለሚመስለኝ።

ቤተክርስትያኗ ይህን በቀጥታ ባታደርግም የጥናት ኣካል ካላት ምዕመናን ማሰማራት የምትችል ይመስለኛል። ቃልቻዎች እና ቃሉዎች ጭምር የሚሉት ሳይናቁ ምልክቶችን ማጥናት ይቻላል ብዬ ኣስባለሁ።

ይህ ማለት ይህ ጥንታዊ የሃይማኖት ቤት በህዳሴ ዘመን ቀዳሚ በመሆን መለኮታዊ መስመርን ማሳየት ይችላል ማለት ነዉ።

በተጫማሪም የኣዉሮፓ የሬነሳንስ ዘመን የካቶልክ ቤተክርስትያንን ወደ ሶስት ጎራዎች መሰናጣጠቅን የሚታደግ እና በጋራ መለኮታዊ ምልክቶች የምያሰባስብ ሊሆን ይችላል ማለት ነዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7512
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የፓትርያርኩ ጥሪ "አቁሙ! .... በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ !"

Post by Naga Tuma » 11 May 2026, 13:48

ሰዎች መለኮትን ፍሩ የሚል ርዕስ እዚህ መድረክ ላይ የጻፍኩኝ ከወራት በፊት ነዉ።

ያለ ምክንያት ኣይዴለም።

ለመነሻ ያህል ሁለት መለኮታዊ የሚመስሉ ምልክቶችን ጽፌኣለሁ።

ሁለቱ መለኮታዊ ምልክቶቹ የሚመስሉኝ ሁለት ግለሰቦችን ይመለከታሉ።

ሁለቱም ግለሰቦች ዐይነ ምድር ብለዉ የተመሳደቁ ነበሩ።

ኣሁን ያሉኝ በጣም ቁልፍ ጥያቄዎች ለእኔ ኣንድ ግለሰብ መለኮታዊ ምልክቶች የሚመስሉኝ ለመሆናቸዉ ኣሳማኝ ናቸዉ ወይስ የኣንድ ግለሰብ ቅዠት ስለሆኑ ኣሳማኝ ኣይዴሉም የሚሉ መልሶችን መለየት ነዉ።

እነዚህ ጥያቄዎች ከሁሉም በላይ የሚመለኩት የሃይማኖት መሪዎችን ነዉ።

መልሶቹ ኣሳማኝ ናቸዉ ከተባለ ተከብራ በኖረች ሃገር እግዝኣብሔር ኣለ ብሎ ማሰብ የኣዕምሮ መቃወስ ነዉ ከተባለዉ እንድታገግም ማድረግ የዋል ይደር የሚባል ጉዳይ ኣይመስለኝም።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7512
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የፓትርያርኩ ጥሪ "አቁሙ! .... በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ !"

Post by Naga Tuma » 19 May 2026, 15:29

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ፓትርያርክ፥

የኣንድ ግለሰብ ምክር ቢሆንም ስሙ።

ተዓምራት ተሰምተዉ ተፈጽሟል።

ተዓምራትን የምያሰማ እና የምያሳይ ህያዉ መሆኑ ለዘላለሙ እንዳይሻር ሆኖ ኣሸንፏል።

እግዜር ዬለም ላለዉ የስምንተኛዉ ሺህ ዘመን ዳያብሎስ ኣለመስገድዎ ሆነ መስገዶዎን ልቦናዎ ብቻ ያዉቃል።

ሰግደዉለት ከሆነ በዚህ ዘመን ተዋርደዉ የተከበረች የሃይማኖት ሃገርንም ስም ኣዋርደዋል ማለት ይቻላል።

ይህ ከሆነ የዚህ ግለሰብ ምክር ዉለዉ ሳያድሩ የእግዜርን ተዓምራዊ አሰራር የምያዉቅ ሆነ እግዜር የምያዉቀዉን ፓትርያርክ መፈለግ ያሻል ነዉ።

Post Reply