Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
Yes, if you exclude Woyane from the parameters!
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
ወይን is ወይን it becomes more sweeter with time!
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
That must be a fake wine. An authentic wine’s flavor becomes enhanced as it ages, not sweeter. The latter is a typical characteristic of an evaporated or expired wine, which is bad for your health.
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
ከጥቂቶቹ ጥንታዊት ቅድስት ስፍራዎች እና ቤተ-መቅደስ መካከል አክሱም ጽዮን ትጠቀሳለች። ይህ ቅዱስ ቦታ ታሪካዊ ምግባሩን በጠበቀ መልኩ መቀጠል ተገቢ ነው። የመጀመሪያው ተግባር መሆን ያለበት ሐዋርያት የሰበሰቧትን ቀዳማዊት ኦርቶዶክስ መጠበቅ ነው። ከዚህ አንጻር አክሱም ከተማ ከጴንጤ ቆስጤ፤ ጆቫ፤ ብልጥግና ጎስፕል፤ ወዘተ ወፍ-አራሽ ባዕድ እምነት መንጻት አለባት። ምዕምኑን እና ቤተ-መቅደሱን ከሚያረክሱ፤የእመንቱን መሰረት ከሚንዱ ነጣቂ ተኩላዎች መጠበቅ አለባት። ከዚያ መለስ ደግሞ ኢ-ክርስቲያናዊ የሆኑ የሶዶም ምግባር፤ አደንዛዥ ዕጽ፤ ዝሙት፤ ወዘተ መከልከል ያስፈልጋል። ይህ እርምጃ በሌሎች ቀደምት የኢትዮጵያ ሃይማኖት መሰረት በሆኑት እንደ ተድባባ ጽዮን (አምሃራ ሳይንት) -ቅድመ እክሱም በብሉይ ዘመን ስለነበርችው፤ የጣና ሃይቅ ቅዱሳን ቦታዎች (ያለ አግባቡ እየረከሱ ያሉት) ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስዱ ይገባቸዋል።
በመቀጠል በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውስጥ የተሰገሰጉ የጴንጤ እና የተሃዲሶ አላማ የሚያራምዱ የቅስና ካባ ከለበሱ ትህነግ እና ቄሮ "ጳጳሳት፤ቄሳውስት" መጠበቅ አለባት። አክሱም ጽዮን ይህን እራሷን ቤተ-መቅደስ ቀሳውስት እና ጳጳሳት መገምገም አለባት።
በመቀጠል በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውስጥ የተሰገሰጉ የጴንጤ እና የተሃዲሶ አላማ የሚያራምዱ የቅስና ካባ ከለበሱ ትህነግ እና ቄሮ "ጳጳሳት፤ቄሳውስት" መጠበቅ አለባት። አክሱም ጽዮን ይህን እራሷን ቤተ-መቅደስ ቀሳውስት እና ጳጳሳት መገምገም አለባት።
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
ሰዎች ሁሉ የፈለጉትን የማመን መብት አላቸው፥ እያአንዳንዱ ሰው የየተፈጠረው ሉኣላዊ ሆኖ ነው። አክሱም የታቦተ ፅዮን መንበርና፥ታሪካዊ የክርስትና ማእከል ከመሆንዋ አንፃር ክልክል የሆኑ ፥ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፥ ከአክሱም የሚጠበቀው ዋናው ግን የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መስበክያና፥ ክርስትያናዊ ስነምግባር ማሳያ ከተማ መሆን አለባት! ላሊበላም ቅድስት ከተማ ብትሆን መልካም ነው። ክርስትያኖች የተጠራ ነው ያአለም ብርሃንና ጨው እንድንሆን እንጂ ሰዎችን በእምነት ምክንያት እንድናሳድድ አይደለም!
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
ቅድስናውን ለኣዅሱም ብቻ የሰጠው ማን ነው? “ቅድስት ኢትዮጵያ” ሲባል ያልሰሙ አካላት መሆን አለባቸው።
"አዅሱም ቅድስት ስለሆነች የምግባረ ብልሹዎች መገለጫ የሆኑ ተግባራት በውስጧ እንድታስተናግድ አይፈቀድም፤" ሌሎቹስ ቦታዎች? ቅዱሳን አይደሉምን? ትግራይ ቅድስት አይደለችምን? ጎንደር ቅድስት አይደለችምን? ጐጃም ቅድስት አይደለችምን? ወሎ ቅድስት አይደለችምን? ሸዋ ቅድስት አይደለችምን? ወዘተ ቅድስት አይደለችምን? በደፈናው ኢትዮጵያስ ‘ቅድስት’ አይደለችምን? የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ወዳጃችን ምን ይሆን መልሱ።
"አዅሱም ቅድስት ስለሆነች የምግባረ ብልሹዎች መገለጫ የሆኑ ተግባራት በውስጧ እንድታስተናግድ አይፈቀድም፤" ሌሎቹስ ቦታዎች? ቅዱሳን አይደሉምን? ትግራይ ቅድስት አይደለችምን? ጎንደር ቅድስት አይደለችምን? ጐጃም ቅድስት አይደለችምን? ወሎ ቅድስት አይደለችምን? ሸዋ ቅድስት አይደለችምን? ወዘተ ቅድስት አይደለችምን? በደፈናው ኢትዮጵያስ ‘ቅድስት’ አይደለችምን? የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ወዳጃችን ምን ይሆን መልሱ።
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
ሰዎች ሁሉ የፈለጉትን የማመን መብት አላቸው፥ እያአንዳንዱ ሰው የየተፈጠረው ሉኣላዊ ሆኖ ነው።
እጨጌ
…ትክክል ነው ግን ቦታውን ከወሰንከው፣ የመጀመሪያው ዓርፍተ ነገርህ ፉርሽ ሆነ ማለት ነው።
Axumezana wrote: ↑11 May 2026, 15:00ሰዎች ሁሉ የፈለጉትን የማመን መብት አላቸው፥ እያአንዳንዱ ሰው የየተፈጠረው ሉኣላዊ ሆኖ ነው። አክሱም የታቦተ ፅዮን መንበርና፥ታሪካዊ የክርስትና ማእከል ከመሆንዋ አንፃር ክልክል የሆኑ ፥ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፥ ከአክሱም የሚጠበቀው ዋናው ግን የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መስበክያና፥ ክርስትያናዊ ስነምግባር ማሳያ ከተማ መሆን አለባት! ላሊበላም ቅድስት ከተማ ብትሆን መልካም ነው። ክርስትያኖች የተጠራ ነው ያአለም ብርሃንና ጨው እንድንሆን እንጂ ሰዎችን በእምነት ምክንያት እንድናሳድድ አይደለም!
-
Digital Weyane
- Senior Member
- Posts: 10207
- Joined: 19 Jun 2019, 21:45
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
በአክሱም ከተማ ውስጥ ሴተኛ አዳሪነት፣ ዝሙት፣ የራቁት ዳንስ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የተፈቀዱ ናቸው።
በአክሱም ከተማ ሙስሊም መሆን ብቻ ነው እንደ ወንጀል የሚቆጠረው።

በአክሱም ከተማ ሙስሊም መሆን ብቻ ነው እንደ ወንጀል የሚቆጠረው።
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
እንደሰማነው ከሆነ ኣዅሱም ከተማ ውስጥ ሙስሊም መሆን ሳይሆን የሚከለከለው፡ መስጅድ መስራት ነው የሚከለከለው። ይህንን ካላመንክ አወል ስዒድን መጠየቅ ትችላለህ፡ ከሆነ ግዜ በፊት እዚያ ሓወልቱ ፊት ቆሞ ደስኩሮ ስለነበረ፡ ጉዳዩን ሳያጣራው አይቀርም!
በነገራችን ላይ አዅሱም ውስጥ ሆነ ሌላ ቦታ የሚወለዱ ሕጻናት እኮ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም በወጉ እስኪጠመቁ ድረስ ክርስትያኖች አይደሉም! ታዲያ ምንድን ናቸው እንዳትለን ደግሞ፡ መልሱ “ሕጻናት” ናቸው ነው! ለጨዋታ ያህል ነው፡ ዲጅታልዋ!
ወደ ነጥብህ ስንጓዝ፡ “የተፈቀዱ ናቸው” እና “አልተከለከሉም” የትኛው ይሆን ትክክለኛው አገላለጽ።
መንበረሰላማ እውነተኛ ከሆነ፡ ትግሉ ኣዅሱምን ከነዚህ እኩይና ኢግብረገባዊ ተግባሮች ነጻ ማውጣት ብቻ ሳይሆን መላዋን ትግራይም ነጻ ማውጣት ይገባዋል። በዚህ ጉዳይ ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ የሚስማማ ይመስለናል።
በነገራችን ላይ የትግራይ ሰዎች “አዅሱም ምቕማጡ ሕሱም!” የሚለው ዕድሜ ጠገብ የትግርኛ ተረትና ምሳሌ፡ በምን ምክንያት እንደተባለ እንዲያስረዱን ጠይቀን እስከ አሁን ድረስ ሊነግሩን አልቻሉም። እስቲ ዲጅታሉ ወዳጃችን ምክንያቱን ንገረን እባክህ!

Digital Weyane wrote: ↑12 May 2026, 07:18በአክሱም ከተማ ውስጥ ሴተኛ አዳሪነት፣ ዝሙት፣ የራቁት ዳንስ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የተፈቀዱ ናቸው።
በአክሱም ከተማ ሙስሊም መሆን ብቻ ነው እንደ ወንጀል የሚቆጠረው።![]()
![]()
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
የኤርትራ ክፍለ ሀገር ወዳጆቻችን ለአፍሪካዊቷ ቫቲካን ትልቅ ክብር ስላላቸው የአክሱም የወደፊት ዕጣ ከሌላ ኢትዮጵያኖች በተለየ መልክ እያሳስባቸው ቀን ከለሊት ያለመሰልቸት ለሚያደርጉት ገንቢ አስተያየት ምስጋና አለመስጠት ንፉግነት ነው።
ህንፃውን በመስቀል ከማጠርህና የሃይማኖት ድንበር ከመፍጠርህ በፊት፣ በመጀመሪያ የልብህን ቤተ ክርስቲያን አንፃ።
ህንፃውን በመስቀል ከማጠርህና የሃይማኖት ድንበር ከመፍጠርህ በፊት፣ በመጀመሪያ የልብህን ቤተ ክርስቲያን አንፃ።
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
Meleket አክሱምን ቅድስት የሚያደርጋት ብዙ ምክንያት ቢኖርም ዋናው የታቦተ ጽዮን መንበር መሆንዋ ነው፥ ላሊበላም ቅድስት ብትባል ያምርባታል፤ ችግርህ የትግራይ ይህን ሁሉ ያስቀናሃል፥ የኔም ጭምር ነው ካልክ እኮ የሚያስቀናህ ነገር የለም፤ አክሱም የሁላችን ናት። አአ ወይም አስመራ የሁላችን ሊሆኑ አይችሉም።
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
ሰላም Axumezana የሚያምነው "ሰዎች ሁሉ የፈለጉትን የማመን መብት አላቸው፥ እያአንዳንዱ ሰው የየተፈጠረው ሉኣላዊ ሆኖ ነው።" አክሱም ውስጥ ማንኛውም እምነትያሉው ሰው ሊኖር ይገባል ህግዋን አክብሮ፤ አክሱም ውስጥ የሚከለከለው መስጊድ መስራት ነው። እስላሞች በሰላም ነው የሚኖሩት፥ ከአክሱም ወጣ ብለው የራሳቸው ከተማ( ሰለክለካ) አላችው አድዋም እንዲሁ።
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
በእርግጥ ኢትዮጵያ ከእስራዔል በመቀጠል ቅድስት አገር ተብላ ትጠራለች። ይህ ማለት ደግሞ አንድ አንድ ስፋራዎች የቅድስና መገለጫ የሆኑ ሃይማኖታዊ ምስጢር ያለባቸው በመሆኑ ነው። ታዲያ እነዚህ ቦታዎች ለየት ባለ መልኩ ቅድስናቸውን ጠብቀው የሚያረክሳቸው ምግባር እንዳይቀርባቸው ማድረግ ግደታ ነው። ዲሞክራሲ መብት ማለት የግድ ቅዱስ ቦታዎችን ካልደፈርኩ ማለት የለበትም። ወንጀል ነው።
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
ጴንጤስ፣ ምኩራብስ?
እንደ ታሪካዊ ቦታ፣ ማንኛውም አይነት ግንባታ ከተከለከለ እስማማለሁኝ!

አዅሱምን “አፍሪካዊቷ ቫቲካን” ብለው የሚያስቡ “የኤርትራ ክፍለ ሀገር” ተወልጀዎች መኖራቸው የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገር ወዳጆቻችን ሲያወጉ በመስማታችን “ጎልዓና ዓሊተናን” እንዳያኮርፉ አስብሎናል።
35ኛ የነጻነት በዓሏን ለማክበር ሽርጉድ የምትለው ኤርትራ የመሀልና የመስመር ዳኞች ደግሞ፡ የቫቲካኑ ጳጳስ ቢልዮኖችን በመንፈሳዊው ረገድ እንደሚመሩ እናዉቃለን። የአዅሱሙ ማለትም የመንበረ ሰላሙ እጨጌ ስንት ሰዎችን በመንፈሳዊው ረገድ እንደሚመሩም፡ ወዳጆቻችን ኢትዮጵያዉያን ተመራማሪዎች እስኪነግሩን እንጠብቃለን። “ቫቲካን” የምትታወቀው የክርስቶስ ተከታዮቹ የክርስትና ታላላቅ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ በሰማእትነት ያረፉባት ስፍራ በመሆኗም ጭምር እንደሆነ “ቤተክርስትያንም የምትገነባው በክርስቶስና በሰማእታት ደምና አጥንት መሆኑን” ታሪክን አጣቅሰው ታሪክን የሚበረብሩ ተመራማሪዎች አስቀድመው ነግረውናል።
አዅሱም ከታላላቆቹ ሓዋርያትና ሰማእታት ማንን ማንን አስተናግዳለች? የሚለውን ጥያቄ የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገር ወዳጆቻችን እስክትመልሱልን፤ “ታቦተ ጽዮንን” እኮ አቅባለች የሚል አገላለጻችሁን ተቀብለናል።
እርግጥ ነው እስከ አሁን ድረስ ጠብቃችሁ ካቆያችሁት፡ በአንድ የታሪክ አጋጣሚ ግራኝ መሓመድ የተባለ ወፈፌ የጦር መሪ በቱርክ እርዳታ ሰክሮ፡ ሃገረምድሩን ስለሙ እያለ በሚፏልልበት ወቅት፡ አንድ ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርስን ከአክሱም ኣሸሽታችሁ፡ ድግሳ በተባለችው ኤርትራዊት ቀዬ አስጠልለን ከውድመት እንዳዳነው መንገር አይጠበቅብንም። “ድግሳ ንሃገር ርእሳ” የሚሉት የኛዎቹ ሊቃዉንት ይህንን ያደባባይ ምስጢር ሲያወጉ ሰምተናል! የአዅሱሞቹ ሊቃዉንትም ቢሆኑ፡ ለወዳጃችን ኣዅሱመጫላ ‘ወንጌላዊነቱን’ አጢነው፡ ይህን ምስጢር አልነገሩት ይሆናል እንጂ፡ “ድግሰኞቹ” እነማን እንደሆንን ጠንቅቀው ያዉቁናል።
እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ከስከሰና አዱሊስ እንዲሁም መጠራና ወዘተ ላይ አስቀድመው ለተሰሩ ቅድመ ኣዅሱም ታሪኮችና ሃወልቶች ለኣዅሱሙም ጭምር “አቢሲኒያዊ ክብር” አለን። በመንፈሳዊው ረገድም ከዚህ በፊት አስቀድመን ቁልጭ አድርገን እንደገለጥነው፡ በአሲሲው ፍራንሲስ ሰላማዊ መንፈስ፡ ሁሉም ቤተ እምነቶች በጋራ እንዲጸልዩ እንዲወያዩ እንዲማከሩም እናበረታታለን። ከዚህ በተጨማሪም ሁሉም ሃገራት እርስ በእርስ ድንበር ሳይጋፉ፡ አባቶች ያኖሩትን ድንበር በማክበር፡ ዓለም ዓቀፋዊ ድንበርን ሳይጥሱ ተከባብረው እንዲኖሩም እንመክራለን፤ ምክራችንም ለመንፈሳዊ ሆነ ለሃገር መሪዎችና ለመላሞቹ የብዕር ‘አርበኞች’ እና ለክፉዎቹ ካድሬዎችም ጭምር ነው። ይህንን ምክራችንንም በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምርም ነው የምንለግሰው።
ያ አስቀድመን ዲጂታሉን የጠየቅነው ጥያቄ አልተመለሰም፡ እስቲ ሌሎቻችሁም የምታውቁት ምልከታ ካለ አጋሩን
“ኣዅሱም ምቕማጡ ሕሱም” ለምን ተባለ!” እንዲያ ያሉት እነማን ናቸው? መቼ? ለምን?
ሲጠቃለል እንደሚታወቀው የአኵሱም የወደፊት ዕጣ ብቻ ሳይሆን፡ የቀጠናችን የወደፊት ዕጣን በመቅረጽ ረገድ ቀን ከለሊት ያለመታከት የምናቀርበውን ገንቢ አስተያየት በቅጡ በመረዳት ምስጋና በማቅረብ ለጋስነታችሁን የምታሳዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገር ወዳጆቻችን በሙሉ፡ “ዳስ ጣል” የሚለውን የቅርብ ዜማ እየኮመኮምን እኛም አጸፌታዊ ምስጋናችንን ልናቀርብላችሁ እንወዳለን።እንደ የታችን ልጅ “ኣዅሱም ለደቡቡ ምኑ ነው?” ወይም “ ኣዅሱም ለሰሜኑ ምኑ ነው?” የሚል አላስፈላጊ እንካሰላምትያ ውስጥ መግባትም አንመርጥም።

ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ፡ አምላክ መላዋን ምድር ባህሩንም ጭምር ቅዱስ አድርጎ ፈጥሯል። ከዚህ በተረፈ አንዳንድ እርኩስ አስተሳሰብ ከሳጥናኤል የተጋባባቸው ሰዎችና ኃይሎች እርኩሰትን መልመድና መለማመድ ማንገስም ጭምር ሲሹ፡ ቅዱሳን የተባሉ ስፍሮች ሳይቀሩ በርክሰት ይበከላሉ። መድኃኔዓለም እንዲህ ዓይነት ጉድ ከማዬት ይሰውረን፡ ብለንም “ታቦተ ጥዮንን” ከነ መላ ንዋዬ ቅዱሳቷና ቀሳውስቷ፡ በቀውጢዉ ሰዓት አስጠልለን፡ ከግራኝ መሓመድ ውድመት ያዳናት እኮ፡ እኛ ኤርትራዉያን የድግሳዎቹ አናብስት መሆናችንን ዘንግተሃል። ስለ ኣዅሱም ጥዮን ምንነትና ማንነት እኛን ቀደምቶቹን የመጠራዎቹንና የአዱሊሶቹን የከስከሰዎቹንና የዓዲ ግራማተኖቹን የሰምበሎቹንና የማይጭሆቶቹን የማይበላዎቹንና የማይተመናዎቹን የወዘተዎቹን ኤርትራዉያን ለምምከር መሞከር “ለቀባሪው አረዱት” እንዳይሆንብህ! “ባህር ባህር እዬተጫወትክ”፡ የሰው ንብረት እየተመኘህ፡ ጽምዶንና ስምምነትንና የሰላም መንፈስን እያደፈረስክ፡ ትግሬ ሆይ ጐንደሬ አማራ ጠላትህ ነው እያልክ እየለፈፈክ፡ አዳዲስ ካርታዎችም እንዳሻህ እዬሳልክ በወኔ መፍጨርጨርህንና “ወንጌላዊ አርበኝነትህን” አይተንልሃል!
እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በምንም ዓይነት ነገር ላይ ኣንቀናም። ይልቅስ በየታሪክ አጋጣሚው ወደ ባሕር በራችን የተከሰቱትን ወንጌል ሰባኪዎችን፡ አጅበንና በመልካም መንፈስ ወደ ትግራይ ሆነ ወደ ጦቢያ ባጠቃላይ በመላክ፡ ለወንጌል መስፋፋት የበኩላችንን በጎ ተግባር ፈጽመናል። ኣኵሱም ውስጥ ብቻ ሳይሆን መላዋ ጦቢያ ውስጥ ያሉ ታሪካዊ ክስተቶች ባጠቃላይ፡ የኛ የኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞችም ጭምር መንፈሳዊ ቡራኬና አሻራ የታከሉባቸው እንደነበሩ ስንገልጽልህ፡ ከቅናትና ምቀኝነት የጸዳ ምንነታችን ፍንትዉ ብሎ እንዲታይህ በማለም ነው።
እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በምንም ዓይነት ነገር ላይ ኣንቀናም። ይልቅስ በየታሪክ አጋጣሚው ወደ ባሕር በራችን የተከሰቱትን ወንጌል ሰባኪዎችን፡ አጅበንና በመልካም መንፈስ ወደ ትግራይ ሆነ ወደ ጦቢያ ባጠቃላይ በመላክ፡ ለወንጌል መስፋፋት የበኩላችንን በጎ ተግባር ፈጽመናል። ኣኵሱም ውስጥ ብቻ ሳይሆን መላዋ ጦቢያ ውስጥ ያሉ ታሪካዊ ክስተቶች ባጠቃላይ፡ የኛ የኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞችም ጭምር መንፈሳዊ ቡራኬና አሻራ የታከሉባቸው እንደነበሩ ስንገልጽልህ፡ ከቅናትና ምቀኝነት የጸዳ ምንነታችን ፍንትዉ ብሎ እንዲታይህ በማለም ነው።
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
በግራኝ አህመድ ጊዜ ኤርትራ የሚባል ምድርና ኤርትራዊ የሚባል ህዝብ አልነበረም፤
ማንነቱን የከዳ ሰው
ማንነቱን የተቀማ ሰው
በማእበል የሚሰቃይ መርከብ
ተቅበዝባዥ ውል የለሽ ልብ
የማሃል ዳኛ የመስመር ዳኛ
ሁሉ አማረሽ ሴረኛ
ለጆኖሳይድ አይኑ የታወረ
ስለ ዲማርኬሽን እየቀባጠረ
ማንነቱን የከዳ ሰው
ማንነቱን የተቀማ ሰው
በማእበል የሚሰቃይ መርከብ
ተቅበዝባዥ ውል የለሽ ልብ
የማሃል ዳኛ የመስመር ዳኛ
ሁሉ አማረሽ ሴረኛ
ለጆኖሳይድ አይኑ የታወረ
ስለ ዲማርኬሽን እየቀባጠረ
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ ጥሩ ግጥም ገጥመሃል። ኤርትራና ህዝቧ በግራኝ ኣሕመድ ዘመን ካልታዩህ፡ ወደ አቢሲኒያ ሄደው ነበር ማለት ነው ብለን አንቀልድብህም! አኵሱም የተወለደችው ከነ ቅድመ አያቶቿ አያቶቿና ወላጆቿ መጠራና ከስከሰ እንዲሁም አዱሊስ ነው ብለን ደም አጥንቷን አናስቆጥርህም፡ ምክንያቱም ልብህ ስለሚያዉቀው። ለማንኛውም የጎንደሬይቱን ባልተቤት ያቶ ካሳሁን ገርማሞን ልጅ ግጥምና ዜማ ጋብዘንሃል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
ዳስ ጣል!
ወይድ አንት አትንገረኝ ማንነቷን፡
ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን።
ወይድ አንት አታስቆጥረኝ ደም አንጥንቴን፡
እኔ አውቀው የለም ወይ ማንነቴን!
Re: Axum is a Holy City, free from Alcohol,Chat, adultery! ጥንቆላ፥ አስማት፥ ድብትርና ይወገዱ ይሆን?
እውቆ አበድን በዱላ ካልሆነ በፀበል ልታድነው አትችልም!