Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 43103
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ቅጠል ተራ፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርካቶ ሄዳ ለቴዲ አፍሮ ምርር ያለ መልስ እየሰጠች ነው!

Post by Horus » 25 Apr 2026, 21:49

በመሰረቱ እነ አቢይ ቀስ እያለ የቴዲን ቅኔ እየበሉት ይመስላል!

እንደ ምታውቁት ቴዲ አፍሮ እስከ ዛሬ ድረስ አንድም የጉራጌኛ ዘፈን ዘፍኖ አያውቅም ነበር ።

ለምንድን ነው ኢቶሪካ ውስጥ ጉራጌኛ ዘፈን የጨመረው? መጨመር ብቻ ሳይሆን ጉሬጌ የተባለው ዜማ አሁን በዚህ ሰዓት ከ8 ሚሊዮን ግዜ በላይ እየተሰማ ከ18ቱ ዘፈኖቹ 2ኛ ሆኖ እየተደመጠ ያለ ዜማ ነው!

በዚህ ዜማ ውስጥ ቴዲ አፍሮ አባይ እየሞላ እንጎድላለን እኛ ብሉ ያዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛውን ግብር ቢከፍልም በወያኔን በአቢይም ተረስቶ የተተወው ምራብ አዲስ አበባ ነው ። የቴዲ ቅኔ አለምንም ጥርጥር የተቀኘው ስለጎደለስ ፣ ስለተቀነሰው ስለተረሳው መርካቶና ምራብ አዲሳባ ነው የተቀኘው ። ይህ ብቻ ሳይሆን ቴዲ አፍሮ ስለ መዘመን ያነሳው በዚህ ዜማ ውስጥ ብቻ ነው ።

ስምምነነ የተሰኘው ጉራጌኛ ዘፈን አይደለም በመርካቶ ፣ አይደለም ድፍን የጎርጊስ ቲፎዞ በሆነው ምራብ አዲሳባ በሰሜን አሜሪካ አገር ቶፕ 30 ዘፈኖች 27 ወይም 28ኛ ነው። ልብ በሉ አሜሪካን አገር ። ዳስ ጣል 13ኛ ነው ።

ስለዚህም ይመስለላል ዛሬ ቀን አዳነች አቤቤ የቅጠል ተራ መርካቶን ነዋሪ ሰብስባ የሚከተለውን ትላለች!

ግን የሚገርመው ይህን መሰረት መጣል የማደርገው ለምርጫ ወይም ለሽንገላ ወይም ለፕሮፓጋንዳ አይደለም ብላለች! ይህን አባባል ምን አመጣው?

ለማንኛውም ለቴድ መራር ትችች መልሱ ቢያንስ ይህን መሰል ነገር እንጂ ክራርና ማሲንቆውን መስበርና መስረቅ አይደለም!

ንግግሯ መጨረሻ ላይ በቀጥታ ለቴዲ ስትመልስ ስሙት!


Last edited by Horus on 25 Apr 2026, 22:04, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 43103
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቅጠል ተራ፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርካቶ ሄዳ ለቴዲ አፍሮ ምርር ያለ መልስ እየሰጠች ነው!

Post by Horus » 25 Apr 2026, 22:00

Right at this moment 8, 068, 200 views and 28th on US Music Trending chart


Post Reply