Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11655
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ቴዲ አፍሮነት፤ ዳንኤል ክብረትነት አልያም ነብዩ ባዬነት አይደለም...!

Post by MINILIK SALSAWI » 22 Apr 2026, 09:01

ቴዲ አፍሮነት፤
ዳንኤል ክብረትነት አልያም ነብዩ ባዬነት አይደለም...!
በዘመናዊም ይሁን በጥንት የዓለም ስልጣኔዎች ኪነጥበብን በዋናነት ሙዚቃን ለዜጎች የሰብዓዊ መብት ጥበቃ፣ መንግስታዊ ጭቆናን፣ በደልን፣ ረገጣንና በአጠቃላይ አምባገነናዊ ሥርዓትን ለማስቆምና ከጅምሩ እንዳይከሰት ለመከላከል ከያኒያን ተጠቅመውበታል። እየተጠቀሙበትም ነው። ነገም ይቀጥላል።
በተለያዩ የዓለም አገራት፣ በተለያዩ ጊዚያት በኪነጥበብ ስራቸው አምባገነናዊ ሥርዓትን በመቃወም፣ ለፍቅር፣ ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃና ለህዝብ ውግንና የቆሙ አንጋፋና ስመጥር ከያኒያንና ሙዚቀኞች አሉ። ለአብነት፦
~ የአፍሮ ቢት አባት የሚባለው ናይጀሪያዊው ፊላ ከቲ፤ በ1970 ዎቹ "Zombie" ና " "Coffin for Head of State" በተሰኙ ጠንካራ የሙዚቃ ስራዎቹ፣ የናይጀሪያን ወታደራዊ አገዛዝ ኢ ፍትሐዊነት፣ ሙስኝነትና በዝባዥነት በቀጥታ አጋልጧል። በዚህ ምክንያት በወታደራዊ አገዛዙ ከፍተኛ የአካልና
የንብረት ዋጋ ከፍሏል።
~#ዩጋንዳዊው ቦቢ ዋይን፤ በዩሪ ሞሶቪኒ አገዛዝ ወቅት በዜጎች ላይ ይደርስ የነበረውን ኢ ፍትሐዊ አፋና፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል እንዲሁም በአገሪቱ ተንሰራፍቶ የነበረውን ሙስና በማጋለጥ ለሰፊው ህዝብ ድምፅ ሆኗል።
~ 1980ዎቹ በጠንካራ የሮክ ሙዚቃ ስራዎቹ የሚታዎቀው ሚድናይት ኦይል በአውስትራሊያ የሀገሬው መብቶች እንዲከበሩ፣ ማኀበራዊ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የመንግስትን ሀብት ምዝበራና ሙስና እንዲሁም የአካባቢ ደህንነት ጥበቃን አስመልክቶ ያቀነቅን ነበረ።
~ የግብፅ "አቢዮት ድምፅ" የሚባለው ራሚ ኢሳም በፈረንጆቹ 2011 የሁስኒ ሙባረክን አገዛዝ ለመጣል፣ በጣህሪር አደባባይ በሮክ ስራዎቹ አቢዮትን የመራበት ሁኔታ እንዲሁም ስመጥሩ ጃማይካዊው ቦብ ማርሌ፣ የ"አገረሰብ ሙዚቃ ንግስት" ተብላ የምትታወቀው አሜሪካዊት ጆአን ቢዝ፣ ችሊያዊው ቪክቶር ጃራ፣ ኒና ሲሞንና ከኢትዮጵያ ደግሞ እነ ምኒልክ ወሰናቸው... ወ.ዘ.ተ ይጠቀሳሉ።
👉 ባለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ...
በኪነጥበቡ ዘርፍ ከወጣት እስከ አንጋፋ ከያኒያን እንደየ መክሊቶቻቸው ስራዎቻቸውን ለተደራስያኑ በተለያየ ዓይነተ (Genre) ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በኢትዮጵያ ባለፉት 50 ዓመታት የበቀሉ ዘረኛ አገዛዞችን አምባገነናዊ ስርዓት ለማጋለጥ፣ በተለይም ባለፉት ሁለት ትውልዶቻችን ጭላንጭል ጥረቶች ሲታዩ ቆይተዋል። ለዚህ ጹሑፍ ግብዓት ይሆን ዘንድ በቅርቡ የምናስታውሳቸውን እናንሳ፦
በአዲስ አበባ በራስ ሆቴል በየወሩ "የጃዝ ግጥም" ዝግጅት ላይ በተለያዩ አንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ይቅርቡ የነበሩና እየቀረቡ ያሉ የኪነ ጥበብ ስራዎች ይጠቀሳሉ። ሞኖሎጎች፣ ሽሙጦች፣ አጫጭር ጭውውቶች፣ ግጥሞች፣ ሙዚቃዎች፣ መነባንቦች፣ ቀልዶችና ውዝዋዜዎች በዋናነት መድረኩን ከሚያደምቁ የኪነ ጥበብ ስራዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ።
በዋናነት መጋቢት/2006 ዓ.ም "ክንፈ" (በኋላ ላይ "እያዩ" በሚል የተለወጠ) ገፀ ባህሪ ግሩም ዘነበ የሚጫዎተው "ፌስታሌን" የተሰኘ ስራ በወቅቱ የአገዛዙን ስርቆት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ዘረኝነትና አምባገነናዊነት በቀልድና ቁምነገር እያዋዛ ይተችና ያጋልጥ ነበረ። በሂደት "እያዩ ፈንገስ" በከፍተኛ ሁኔታ ባገኘው ቅቡልነት በውጭ አገራት ሁሉ ስራውን እንዲያቀርብ ሆኗል። በህወሓት መውደቂያ ዋዜማ ላይ ይሁኔ በላይ "ሰከን በል" ፣ጌትሽ ማሞ "ተቀበል" ፤ፋሲል ደሞዝ "አረሱት" ሻምበል በላይነህ "ደጉ ያገሬ ሰው" ወዘተ የመሳሰሉ ለትግሉ አቢዮት ማነሳሻ የሚሆኑ ዜማዎችን አበርክተዋል።
ኦህዴድ ብልፅግና የአጤዎቹን ቤተ መንግስት ከተረከበበት ማግስት ጀምሮ ወጣትና አንጋፋ ከያኒያን የአገዛዙን አምባገነናዊ ዘረኛ አካሄዶችን በመቃዎም በተለያዩ የጥበብ ስራዎቻቸው ሲያጋልጡና ሲሞግቱ አስተውለናል። በተቃራኒው እንደ አቤል ሙሉጌታ ያሉት ለአገዛዙ አድረው ማሕተማቸውን ጭምር የበጠሱም አልጠፉም።
ወጣቱ ተስፋሁን ከበደ"ፍራሽ አዳሽ" በተሰኙ የመድረክ ሽሙጥ ስራዎቹ በተጨማሪ "ጦቢያ" በተሰኘው የኪነጥበብ መድረክ ላይ በሚቀርቡ ስራዎች የአገዛዙን ፋሽስታዊ አካሄድ ለማጋለጥ በየጊዜው ሙከራ ሲያደርጉ ይስተዋላል። "መንታ መንገድ" በሚል ርዕስ፣ በዋና ተዋናይነት በሽመልስ አበራ (ጆሮ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ይቀርብ በነበረ ስራና "ቧለቲካ " በተሰኘ ርዕስ በግሩም ዘነብ ይቀርብ የነበረው የመድረክ ስራ የአገዛዙን አምባገነናዊ አካሄድ ለማጋለጥ ሞክሯል። የራፕ(ሂፓፕ) ስልት አቀንቃኝ የሆነው ቲዲ ዮ "ወንበረሽ" በተሰኘው ስራው ዜጎች በአብይ አህመድ አገዛዝ የሚደርስባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ አፋናና እንግልት ለማሳየት ሞክሯል። በአገረሰብ የትግል ሙዚቃዎቹ ጎልቶ ስሙ የሚጠቀሰውና ባለ መረዋ ድምጽ ባለቤት የሆነው ቆራጡ ዳኜ ዋለ "አባ ስበር" ፣ "ወይ ፍንክች" ፣ "ወንድ ልጅ ቆረጠ" በመሳሰሉ ስራዎቹ አቢዮቱን ለኩሷል። የአገዛዙን ዘርኝነትም አጋልጧል። ሌሎች አማተር የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችም አገዛዙን ለማጋለጥና ህዝቡን ለመቀስቀስ የበኩላቸውን እየተወጡ ይገኛል።
👉 የቴዲ አፍሮ ጉዳይ...
ቴዲ አፍሮ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች አንዱ ነው። በነጠላም ይሁን በአልበም ደረጃ የሚለቃቸው ስራዎቹ የህዝብ ውግንና ያላቸው ናቸው። ባለፉተ 25 ዓመታት ውስጥ ከሰራቸው 6 የሙዚቃ አልበሞቹ፦
አቡጊዳ 1993 ዓ.ም፣ ቴዲ 1994 ዓ.ም፣ ጃ ያስተሰረያል 1997 ዓ.ም ፣ ጥቁር ሰው 2004 ዓ.ም ኢትዮጵያ 2009 ዓ.ም ኢቶሪካ 2018 ዓ.ም ውስጥ፣ በዋናነት ጃ ያስተሰርያል፣ ጥቁር ሰው፣ ኢትዮጵያና ኢቶሪካ የተሰኙ ስራዎቹ፣ የኢትዮጵያ ገዥዎች በአገሪቱና በህዝቡ ላይ የሚያደርሱትን በደልና ግፍ፣ ስርቆት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ዘርኝነት፣ አፈናና ግድያ በጥብቅ ያዎግዛሉ። በግልፅ ያጋልጣሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ በነጠላ ዜማ ደረጃ የተሰሩ፦
ሰው፣ ልክ ባንሆንም ልክ ነን እኛ ፣ኮርኩማ አፍሪካ፣ ዋሽቶ ለመኖር፣ አርማሽ፣ ቤዛና ናዕት በተመሳሳይ አምባገነን ገዥዎች በሰፊው ህዝብ ላይ የሚያደርሱትን አስተዳደራዊ በደል የሚያጋልጡ፣ አንድነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን የሚሰብኩ፣ ስርቆትን፣ አፈናንና እንግልትን የሚያጋላጡ ናቸው። ቴዲ አፍሮ ቀደምት የኢትዮጵያ ነገስታትን በዘርና በኃይማኖት ሳይከፋፍል በስራዎቹ ያከብራል፤ ይዘክራል። ጥቁር ሰው ( አጤ ምኒልክን) ፣ ኃይለ ሥላሴ ( ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ)፣ ካሳ ካሳ (ለአፄ ቴዎድሮስ)፣ ለእነ ባልቻ አባነፍሶ፣ ለእነ አብዲሳ አጋ፣ ለእነ ዘራይ ድረስ፣ ለንገሱ ሚካኤል፣ ለእነ እቴጌ ጣይቱ፣ ለእነ እቴጌ ምንትዋብ ወ.ዘ.ተ አቀንቅኖል።
ቴዲ አፍሮ ማኀበራዊና ስፖርት ጉዳዮችንም በስራዎቹ አበረታቷል። ለአብነት፦ ኃይሌ ገብረ ሥላሴና ቀነኒሳ አምበሳ የተሰኙ ስራዎቹ ምስክር ናቸው። ለደራስያን ያለውንም ክብር "ሰብልዬን" በመዝፈን አረጋግጧል።
👉ቴዲ አፍሮን አገዛዞች ለምን ይጠሉታል (ይፈሩታል?)
ቴዲ አፍሮ ትክክለኛ የከተማ ጠባይ ያለው የኪነጥበብ ባለሙያ ነው። ለአምላኩ ሰጋጅ ነው። ለስራውና ለህዝብ ታላቅ ክብር አለው። ከገንዘብ ይልቅ እውነትን ዋጋ ይሰጣል። በየቦታው በቀላሉ አይገኝም። ቴዲ አፍሮ ዙፋን ላይ ከነበሩትም ይሁን ካሉት የተሻለ ስምና ዝና አለው። ከአስደማሚ የኪነጥበብ ስራዎቹ ባሸገር የቴዲ አፍሮ ትልቁ አቅሙ ይህንን (ያለውን ሰብዓዊ ሐብት) ለይቶ ማዎቁ ነው። ቴዲ አፍሮን፣ በገንዘብ የማትሸነግለውም ለዚሁ ነው። ረብጣ ዶላርም ይሁን ቅንጡ ቁሳቁስ አቅርበህ ቤተ መንግስትም ይሁን ትላልቅ ቦታዎች ላይ ብትጠራው የማይመጣውም ከዚሁ አቅሙ በሚመነጨው በራስ መተማመኑ ነው። ኢትዮጵያን አብዝቶ ይዎዳል። ጠንካራ የሙዚቃ ግጥሞቹ፣ ዜማውና አዚያዚያሙ የአምባገነኖች መምቻ መዶሻ ናቸው። ቴዲ ዘመን የማያዋዥቀው፣ ገንዘብ የማያጠይመው፣ ፍራቻ የማይለዉጠው ፅኑ አቋም ያለው ሰው ነው። ቴዲ ሁሌም ከእውነት ጋር እንጂ በሀሰት ድንኳን አይገኝም። ሁሌም ለድምፅ አልባዎቹ፣ በስራዎቹ፤ ድምፅ ሆኖ ከፊት ይቆማል። በዚህ የተነሳ ከፍተኛ ህዝባዊ ቅቡልነትን አትርፏል። ተፅዕኖ ፈጣሪነቱም ባህር ተሻግሯል። ይህ በመሆኑ ቴዲን አምባገነኖች ይፈሩታል።
👉 ከአብይ ጋር ምን አጣላው?
1ኛ, " ገበታ ለሀገር" በተሰኝ የጠቅላይ ሚንስትሩ የገንዘብ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ መርኀ ግብር ላይ በተደጋጋሚ እንዲገኝ ቢጠራም ፈቃደኛ ሳይሆን መቅሩቱ። ይባስ ብሎ ፦
"...ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ፣
ማን ሊታደም በድግሱ፤
እያረረ ሆዴ፣ ብስቀ በማሽላ ዘዴ፣
ና ታደም ይለኛል፣ ደግሞ በእነ ኡኡ ሬጌ።" ብሎ ገመናውን በማጋለጡ።
2ኛ, አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ቤት፣ ቴዲ አፍሮ ሀዘን ሊደርስ በሄደበት ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ፎቶ እንዲነሳና በጋራ እንዲቀመጥ ሲጠየቅ አሻፈረኝ ብሎ በመሄዱ።
3ኛ) በህወሓትና በአብይ አህመድ የእርስ በእርስ የስልጣን ጦርነት ወቅት፣ አብይን ወግኖ እንዲቀሰቅስና እንዲከፋፋል ሲጠየቅ ባለመታዘዙ። ይባስ ብሎ፦
"...አርማሽ ቀና ይበል፣
ቀን እየሄደ ቀን መጣ፣
ልቤ ከሀሳብ ሳይዎጣ፣
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ፣
አገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ።" ብሎ በማዜሙ!
4ኛ) የዓባይ ግድብ መጠናቀቁን ተከትሎ በአደባባይ እንዲጎበኝና በምርቃት ፕሮግራሙ እንዲገኝ ቢጠየቅ አምቢ በማለቱ።
5ኛ) በተለያዩ የምስጋናና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶቹ፣ የኦህዴድ ብልፅግና አምባገነናዊ አገዛዝን በድፍረት በማጋለጥ፣ ህዝብ እንዲታገለው ጥሪ በማድረጉ።
6ኛ), "ኢቶሪካ" በተሰኘው 6ኛ አልበሙ... "ዳስ ጣል" ፣" ጀምበር" ፣ "የአዞ እምባ" ወ.ዘ.ተ በመሳሰሉት ስራዎቹ የአብይ አህመድን ቃል አባይነትና ጨፍጫፊነት በማጋለጡ።
"...አባይ ለዘዴው፣ በአፍ ይቀድማል፣
አምኖ መከዳት፣ እንዴት ያማል፤
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን፣
ምጥ አታስተምርም፣ ልጅ እናቷን፤
ወይድ አንተ፣ ላንሳበት ባንዲራዬን፣
አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ አርማዮን!" ብሎ ማጋለጡ!
7ኛ) ኢትዮጵያ አገሩን፣ ሰንደቁን፣ ማንነቱን፣ ባህሉን፣ እሴቱን፣ ቋንቋውንና እምነቱን አክብሮ ለትውልድ እንዲሸጋገር በመስራቱ ይህ ደግሞ ከአገዛዙ የብልፅግና ርዕዮት ጋር በመቃረኑ ነው። በህዝብ ዘንድ መወደዱና ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆኑ ጭምር በአገዛዞች ይፈራል።
👉 ሲጠቃለል፦ ቴዲ አፍሮን በቀላሉ እንደ አቤል ሙሉጌታ ማኃተሙን አታስበጥሰውም። እንደ ካሙዙ ካሳ የስንዴ ነዶ አስታቅፈህ አትነዳውም። እንደ ንዋይ ደበበ፣ አንደ አረጋኃኝ ወራሽ፣ እንደ አስጌ ዴንዳሾ በየ መድረኩ ሳንቲም ሰጥተህ አታልከሰክሰውም። እንደ ነብዩ ባዬ፣ ኃሊናውን አከራይቶ፣ ኪነ ጥበብን ለማይገባው መውድስ በመጠቀም የከርስ መሙያነት እንዲያውለው ልታዝዝው አትችልም። እንደ ሠርፀ ፍሬ ስብዓት ኪነጥበብን መዎድስ አብይ እንዲያቀርብበት ልትጠይቀው የምትችለው ሰው አይደለም።
እንደ ዳንኤል ክብረት በ"ዲያቆን" ማዕረግ፣ የጌታን ለቄሳር ገብሮ ይሁዲነትን እንዲኖር በ30 ዲናር የምትገዛው ሰው አይደለም።
"...ፍቅርን ብዬ አንጂ፣ ተግቼ ለሰላም፣
እኔስ መታገሴ፣ መች ከአገር ይበልጣል፣
እኔስ አንድ ነፍሴ..." ብሎሃልና፣ አታድከም።
ወግደረስ ጤናው ሚያዚያ/ 2018 ዓ.ም