Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Axumezana!

Post by Selam/ » 18 Apr 2026, 02:39


Axumezana
Senior Member
Posts: 19138
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Axumezana!

Post by Axumezana » 18 Apr 2026, 03:25

ይኸ ነገር የአክሱም የእምነት አባቶች ላለፉት 1400+አመታት የከለከሉት ጉዳይ ነው። መካ ላይ ቤተመቅደስ እንደማይሰራ፥ አክሱምም መስጊድ አይሰራም ብለው ፋይሉን ዘግተዋል። ከአክሱም ወጣ ብሎ አድዋም ሆነ ሰለክለካ መስጊድ መስራት ይቻላል። ጠብ መፍጠሩ አላስፈላጊ ነው። በጉልበት እናደርጋለን ካሉ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን መከላከል ይችላሉ። አክሱም ግን ዳንኪራ፥ አስማት፥ ጥንቆላና ድብትርና እየፈቀደች እስልምናን ብትቃወም፥ ግብዝነት ስለሆነ፥ ራሷን መቀደስ ይገባታል፤ Medan TVን መመልከት ነው፤

መሃመድ አለ ሀበሻን አትንኩ
ግራኝም አልቻለም የቱርክ ተላላኪው
አብይም አይችል ሽህ ሁሴን አምላኪው
ብቻ ትግራይን በገንዘብ እንዳይገዙት
ችግርና የንዋይ ፍቅር እምነትን እንዳያስክዱት

Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Axumezana!

Post by Selam/ » 18 Apr 2026, 04:40

ጅል ነህ ልበል እንዴ?

ኢትዮጵያ ውስጥ እምነት በምርጫ ነው። ደግሞም የአንተ አይምሮ ነው እንጂ ስስታሙና ፈሪው፣ መስጊድ ስለተሰራ አምላክ አይደነግጥም ክብሩም አይቀንስም። የሌላ ሃገር ምሳሌ ላምጣ ካልክ ደግሞ እየሱስ ተወልዶ ባደገበት ቤተልሄም ውስጥ እኮ መስጊዶች አሉ፣ እንዲሁም ባስተማረበትና ተገርፎ በተሰቀለበት ኢየሩሳሌም መስጊዶች በሽ በሽ ናቸው።

ሙስሊሞች አክሱም ውስጥ እየኖሩ፣ ግብር እየከፈሉና በየጎዳናው እያመለኩ፣ ህንፃችሁን ግን ማየት አንፈልግም ማለት ግብዝነትና በራስ ያለመተማመንና የአናሳነት ምልክት ነው። ጥንቆላውን ተወውና ፣ አክሱም ውስጥ ትህነግ ክቡሩን የሰው ልጅስ ታስርና ትገድል አልነበረም እንዴ? በማርክስና ኤንግልስ ተጠምቃ ቤተ እምነትን ታጠቃ አልነበረም እንዴ?

ግን ፈጣሪ ሁልጊዜም በራሱ ሂደት ክብሩን ያፀናል፣ አንተ ሃጢያተኛው ውር ውር ስላልክ ምንም ለውጥ አታመጣም፣ ራስህን ለማታለል ካልሆነ በስተቀር።

Axumezana
Senior Member
Posts: 19138
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Axumezana!

Post by Axumezana » 18 Apr 2026, 13:06

መስጊድ ይሰራ አይሰራ ወደ ሚለው ክርክር መግባቱ ጥቅሙ እይታየኝም፤ 1400+ አመታት የቆየውን አሰራር መለወጥ የማይቻል ጉዳይ ነው። እዮርሳሌም መስጊድ በጉልበት ስለተሰራ አክሱምም መሰራት አለብን ካልን ልክ አይሆንም! መካም እንደዚሁ። ህንድ ውስጥም የዚሁ አይነት ጭቅጭቆች አሉ። ታቦተ ጽዮን አክሱም አለች ካልን አክሱማውያን መስጊድ እንዳይሰራ መከልከላቸው ምክንያታዊ ነው! ወጣም ወረደም በእየሱስ ክርስቶስ አምነን፥ ብንድን፥ ምድራዊው ጭቅጭቅ ያበቃለታል።

Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Axumezana!

Post by Selam/ » 18 Apr 2026, 13:31

ልክ እንደ ፖለቲካው ፣ የሃይማኖቱን የጎል post እያንሸራተትከው አስቸገርከኝ እኮ።

በአንድ በኩል ኋላ ቀር የኦርቶዶክስ የዕምነት ስርዓት መሻሻል አለበት ትልና፣ ለአክሱም ሲሆን ለሺህ ዓመት የቆየ አሰራር አይለወጥም ትላለህ። መካ ለምን ዘለህስ ትሄዳለህ፣ እዚሁ አጠገባችን ሃረር እያለልህ?

በነገራችን ላይ በሚቀጥለው ዓመት ወደ አክሱም ለመሄድ አስቤያለሁ። የትኛውን ሃጥያት ነው ወደ ከተማው ይዞ መግባት የማይፈቀደው?

Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Axumezana!

Post by Selam/ » 18 Apr 2026, 19:45

እዚህ የአክሱም ቡና ቤት ጠበል ነው እንዴ የሚሸጠው?


Axumezana
Senior Member
Posts: 19138
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Axumezana!

Post by Axumezana » 18 Apr 2026, 22:06

የእስልምና አላህ ነኝ የሚል መንፈስ አንድ እጅሽን ብትሰጪው ሁሉቱን አምጪ ይልሻል፥ ሁሉቱን ከሰጠሽው ደግሞ ሁለመናሽን ካልበላሁ ይልሻል፥ ለዚህ መድሃኒቱ አለመስጠት ነው። ሀረር ና አክሱምን አንድ አድርገሽ ካየሽ ፥ አክሱም የታቦተ ጽዮን መቀመጫ መሆኑን አታምኝም ማለት ነው። ከዛሬ ስንት አመት በፊት የታቦተ ጽዮን የማግኘት እድል እግዚአብሄር ሰጥቶኝ፥ አነጋግሬዋሎሁ!

Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Axumezana!

Post by Selam/ » 18 Apr 2026, 22:41

ወዳጄ
የአንተ ችግር ምን መሰለህ ፣ በአንድ ቦታ ፀንተህ አትቆምም። በየአቅታጫው ትሹለከለካለህ።

- ኦርቶዶክስ ስርዓቱ አርጅቷልና ይታደስ vs. የአክሱሙ አይነካም

- አክሱምን ከመካ ማወዳደር vs. ሃረርና እየሩሳሌምን አታንሱብኝ

- መሸታ ቤት ይፈቀዳል vs. ሌላ ዕምነት አይፈቀድም

- ወያኔ ሃገር መምራት አለባት vs. የሙስሊሞች እምነት ሰይጣናዊ ነው

አየህ በመንፈሳዊውም በፖለቲካውም መንገድ አንድ ወጥ አቋም የለህም! ማቴዎስ 7:1-5ን አንብብ በደረትህ መሳቡን እንድታቆም።


Axumezana wrote:
18 Apr 2026, 22:06
የእስልምና አላህ ነኝ የሚል መንፈስ አንድ እጅሽን ብትሰጪው ሁሉቱን አምጪ ይልሻል፥ ሁሉቱን ከሰጠሽው ደግሞ ሁለመናሽን ካልበላሁ ይልሻል፥ ለዚህ መድሃኒቱ አለመስጠት ነው። ሀረር ና አክሱምን አንድ አድርገሽ ካየሽ ፥ አክሱም የታቦተ ጽዮን መቀመጫ መሆኑን አታምኝም ማለት ነው። ከዛሬ ስንት አመት በፊት የታቦተ ጽዮን የማግኘት እድል እግዚአብሄር ሰጥቶኝ፥ አነጋግሬዋሎሁ!

Axumezana
Senior Member
Posts: 19138
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Axumezana!

Post by Axumezana » 18 Apr 2026, 23:15

ጥያቄ ጠየቅሽ መልስ ሰጠሁ፥

መሸታ ቤት ትክክል ነው አላልኩም፥ እንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጭው፥ ቤተክስርስትያናችን ትስተካከል ማለት ትክክል ነው፥ የሙስሊም፥ የአክራሪዎች መረማመጃ እንድትሆን ግን አልፈቅድም!

የወለንጪቷ ልጅ ግራ የገባት
ጠብ ያለሽ በዳቦ ልግዛ እያለች
አክሱም ውሰዱና ጠበል አስረጭዋት
ነፃ እንድትወጣ ከስድብ ልክፍት

Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Axumezana!

Post by Selam/ » 18 Apr 2026, 23:44

ጅል ነህ ያልኩት ያለምክንያት አይደለም።

ሙስሊሞችን ከተጠየፍክ እነሱ እደረሱበት አትድረስ። ይኸም ማለት ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ አስተዳደር አንድም ነገር ማውራት አትችልም ማለት ነው። እኔ ከደብረፖርኖ ጋር ፅዮን ማርያም ከምገባ ፣ ፅድት ያለው ሙስሊሙን ወንድሜን እጁን ይዤ ብሳለም እመርጣለሁ።



Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Axumezana!

Post by Selam/ » 18 Apr 2026, 23:54




Axumezana
Senior Member
Posts: 19138
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Axumezana!

Post by Axumezana » 19 Apr 2026, 01:19

If you are Christian you are not allowed to mix light with darkness( any belief that does not believe "Jesus is the Son of God and died for our Sin and resurrected on the third day, ascended to heaven on the 40th day and he sits at the right hand of the Father and He shall come back to rule for 1000 years and ultimately judge the dead and the living. judge the world").

Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Axumezana!

Post by Selam/ » 19 Apr 2026, 09:09

እኔ ሃይማኖትን በልቤ ውስጥ እንጂ የማበለፅገው፣ እንደ ነጠላ ከላይ ተከናንቤ ለዕይታ አልጠቀምበትም። እስር ቤት ብገባ፣ ጂዳን ብጎበኝ፣ ጀጎል ብንሸራሸር፣ ቬጋስ ብሄድ፣ ልቤ ውስጥ የተገነባውን የቤተ ክርስቲያን ውቅር ማንም አይነቀንቀውም። ሮሜ 10፥9ን አንብብ። በአንተ አተያየት ከሆነ ግን እንደ መነኩሴ ከፅዬን ማርያም ቅጥር ግቢ ውስጥም መውጣት የለብኝም።

የአንተ ግብዝነት ጥግ የለውም ያልኩህ ለዚህ ነው። በየቀኑ ፖለቲካ ውስጥ ገብተህ እገሌ ይጨፍለቅ እገሌ ይሾም እያልክ እያቦካህ፣ ህይወቴን በመፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው የምመራው ትለኛለህ።

የአረማውያኑን፣ የሌባውን፣ የሴሰኛውንና የገዳዩን ፖለቲካ ሆ ብለህ እየደገፍክ፣ በምን ሂሳብ ነው ዞር ብለህ ሙስሊሞች ሲሆኑ በጥላቻ የምትንገፈገፈው? ከምትጠላው የእስልምና ዕምነት ጀርባ እኮ 40 ሚሊዮን የሚሆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች አሉ። አንድ ቀን የትግራይ ወይንም የአክሱም አስተዳዳሪ ሊሆኑ ይችላሉ። በሃገራችን መተዳደሪያ ደንብ ደግሞ፣ አህዛቡም ይሁን የትኛውም የዕምነት ተከታይ ማስተዳደር ይችላል። ለዚህ ነው አረማዊዎቹና ኮሚኒስቶቹ መንግስቱና መለስ መሪ የሆኑት፣ የዛሬዋ ደብረፖርንም ጣጥ ጣጥ የምትልብህ።

ሌላ ልጨምርልህ፣ በአንድ የዕምነት ርስት ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ሰዎች የትም ቦታ ሄደው የቤተ ዕምነት እንዲሰሩ የኢትዮጵያ መስተዳደር ይፈቅዳል። በእርግጥ ነው ድምፅና ትራፊክ ስለሚበዛ፣ ወይንም በዕምነቱ የሚወከለው ህዝብ ትንሽ ነው ብለህ መቃወም ትችላለህ፣ ተገቢም ነው። በጭፍኑ መከልከል ግን አትችልም። ይልቅ በፍቅር፣ በአስተምሮና በፀሎት ወደ አንተ ዕምነት እንዲመጡ ጥረት አድርግ። በጥላቻ የጠቆረው የራስህ ልብህም ቀስ በቀስ ይፀዳልሃል።

Axumezana
Senior Member
Posts: 19138
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Axumezana!

Post by Axumezana » 19 Apr 2026, 10:14

ጥላቻና እምነታቸውን አለመቀበል አይገናኝም።ጔታችን እየሱስ የሞተው ለሰው ልጅ ሁሉ ነው። ሁሉንም መውደድ የግድ ነው።

Selam/
Senior Member
Posts: 17805
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Axumezana!

Post by Selam/ » 19 Apr 2026, 11:06

ኧረ አትሹለክለክ፣ እስልምና ሰው ይበላል ያልከው እኮ አንተው ነህ። አስተዳደሩንና ቤተ-ክህነቱን ጨምሮ ስልቅጥ አድርጎ የሚበላውን ሰይጣን የሚያመልኩ ኮተታሞች አክሱም ከተማ ውስጥ ስለመኖራቸው ማመንህ ግሩም ነው። ግን ታዲያ በዓለማዊ አስተዳደር ያለ መንግስት እነዚህን አስፀያፊ ነገሮች ሊያጠፋቸው እንደማይችል ሊጠፉም እንደማይችሉ ልቦናህ ያውቃል። ስለዚህ እስልምናን ነጥለህ ማውጣትህ የጥላቻ ምልክት ነው።

እንዲያውም አክሱም እንደገና የኢትዮጵያ መንበር ትሆናለችም ብለህ ነበር። ሙስሊሙን ህብረተሰብ አስወግደህ ማለት ነው?

Axumezana wrote:
18 Apr 2026, 22:06
የእስልምና አላህ ነኝ የሚል መንፈስ አንድ እጅሽን ብትሰጪው ሁሉቱን አምጪ ይልሻል፥ ሁሉቱን ከሰጠሽው ደግሞ ሁለመናሽን ካልበላሁ ይልሻል
Axumezana wrote:
19 Apr 2026, 01:19
If you are Christian you are not allowed to mix light with darkness
Axumezana wrote:
18 Apr 2026, 03:25
አክሱም ግን ዳንኪራ፥ አስማት፥ ጥንቆላና ድብትርና እየፈቀደች እስልምናን ብትቃወም፥ ግብዝነት ስለሆነ፥ ራሷን መቀደስ ይገባታል

Post Reply