Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

እስራኤል ስምሽን ሳታዋርጂ ከቶራ ታረቂ፣ ዕዉነቱን ኣዉጪ

Post by Naga Tuma » 31 Mar 2026, 15:17

እኔ የሚታየኝ ይህ ዘመን የፍርድ ዘመን የተባለዉ መሆኑን ነዉ።

ይህ ዘመን የፍርድ ዘመን የተባለዉ ይመስላል ያልኩኝ ስለ ፕሮፌት ማኒ ምንም ነገር ሳላዉቅ በፊት ነበር።

ይህ ማለት ነገ ወይም ከነገ በኋላ ምን ዐይነት መለኮታዊ ምልክት እንደሚገለጥ ኣላዉቅም ማለት ነዉ።

ሲገለጡ የቆዩት መለኮታዊ ምልክቶች የእኔን ኣማኝነት በጣም ኣጠንክሯል።

በዚህም ምክንያት ይህ ዘመን ኣማኞች ሃይማኖት ከሌላቸዉ የሚለዩበት ዘመን ሆኗል ብዬ ኣስባለሁ።

የእስራኤል ኣማኝነት በፕሮፌት ሙሴ አኮርድ በኩል ነዉ። ያንን አኮርድ ወይም ቶራን መተዉ ወደ ኣማኝ ኣለመሆን መዝቀጥ ነዉ።

ከስደት በኋላ ፕሮፌት ሙሴ የሆነዉ ከስደት በፊት የአሙን ፕሮፌት እንደነበረ በሁለተኛዉ የዐለም ጦርነት ዋዜማ ዕዉነቱን ያወጣዉ ኣይሁዳዊዉ ስግመንድ ፍሪዩድ ነበር።

ሴት ሳትጋደም ወንድ ልጅ ወልዳ ኣቀፈች የሚለዉን ዘበትን የመጀመርያዉ ሬይነሳምስ ዘመን ወደ ኋላ ትቶ ሳይንስን ከተረሳበት ኣንስቶ ማሳደግ የቀጠለ ነዉ።

ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ዘመንም ተመሳሳይ አነሳስ ተነስቶ የሳይንስን እድገት የቀጠለ ነዉ።

ስለዚህ የእስራኤል በፕሮፌት ሙሴ በኩል ከአሙን የነበራትን አኮርድ ትቶ ከኣማኝነት መዝቀጥ፣ ፕሮፌት ሙሴ ከስደት በፊት የአሙን ፕሮፌት ነበረን ዕዉነት በቸልተኝነት ማለፍ፣ የመጀመርያዉ እና ሁለተኛዉ ሬይነሳምንሶች ዘመኖች ሴት ሳትጋደም ወንድ ልጅ ወልዳ ኣቀፈችን የተተወ ዘበት በቸልተኝነት ማስፋፋት መሞከር ይህ የፍርድ ዘመን የምያዋርዳቸዉ እንጂ የምያስከብር ኣይመስለኝም።

ስለዚህ ነዉ እስራኤል ስምሽን ሳታዋርጂ ከቶራ ታረቂ፣ ዕዉነቱን ኣዉጪ የሚል ምክርን እኔ ለመለገስ እዚህ የለፋሁኝ።

በተጨማሪ በዚህ የፍርድ ዘመን የሚመስል ግዜ መለኮታዊ ምልክቶችን ማጥናት እና ከኣሁን በፊት ለዘመናት የኖሩትን ዘበቶች ማረም ሲቻል በቸለተኝነት ማለፍ የማያዋርድ ባይሆን ትክክለኛ ታሪክ የሚሆን ነዉ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: እስራኤል ስምሽን ሳታዋርጂ ከቶራ ታረቂ፣ ዕዉነቱን ኣዉጪ

Post by Naga Tuma » 15 Apr 2026, 17:18

ይህ ዘመን የፍርድ ዘመን ይመስላል ከተባለ የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ከጥንት ግዜ ጀምሮ የኖረ ግንኙነትም መለኮታዊ ፍርድ ያገኛል ማለት ነዉ።

ከጥንት ግዜ ጀምሮ የኖረ የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ግንኙነት ታሪክ ሆነ ወሬ በሁለት በኩል ነዉ።

ኣንደኛዉ በስደት ወይም ኤክሶደስ በኩል ነዉ።

ሁለተኛዉ በንግስት ሳባ ንጉስ ሰለሞንን የመጎብኘት ወሬ በኩል ነዉ።

ስደት የመጀመርያዉ ሲሆን ጉብኝት ቀጥሎ የመጣ ነዉ።

የስደት ታሪክ ዕዉነት ነዉ የተባለዉ ከስደት በኋላ የእስራኤል ፕሮፌት ሙሴ ሆነ የተባለዉ ከስደት በፊት የጥንት ኢትዮጵያ ታላቅ ፈረዖ አከናተን ነበር የሚል ነዉ።

የጉብኝት ወሬ ዘበት ነዉ የተባለዉ ንግስት ሳባ እና ንጉስ ሰለሞን የኖሩበት ዘመናት የተራራቁ ስለሆነ ነዉ የሚል ነዉ።

ጉብኝቱ ዕዉነት ነበር ቢባል እንኳን ኣንድ የጥንት ንግስት ብያንስ መቶ ቤተሰቦች ንግስት የነበረች ከሆነ ከንጉስ ሰለሞን ወለደች የተባለዉ ቀዳማዊ ምኒልክ ምናልባት ከመቶዎች ልጆች ዉስጥ ኣንድ ነዉ።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ምሁራን ነን ባዮች ሆኑ የፖለትካ መሪዎች ነን ባዮች ዬትኛዉ ዕዉነት እና ተገቢ ትምህርት እንደሆነ ማረጋገጥ የሚሳናቸዉ ናቸዉ?

Post Reply