Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11655
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የቴዲ አፍሮ "ኢትዮሪካ" አልበም መግለጫ ታገደ!

Post by MINILIK SALSAWI » 14 Apr 2026, 02:10

የቴዲ አፍሮ "ኢትዮሪካ" አልበም መግለጫ ታገደ! የኢቶሪካ አልበም ብቸኛው የሚዲያ አጋር በመሆን ከ Teddy Afro ማኔጅመንት ጋር ከቀናት በፊት ስምምነቱን ፈፅሞ መረጃውን በይፋዊ የ Facebook ገፁ ላይ ይፋ አድርጎ የነበረው አርትስ ቲቪ በአሁኑ ሰዓት ቀደም ብሎ ያጋራው ይህን መረጃ ከገፁ ላይ አጥፍቶታል። ..... በጉጉት የሚጠበቀው የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም "ኢትዮሪካ"ን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ መታገዱ ተሰማ። ....የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ቴዲ ከተለያዩ ጋዜጠኞች ጋር የሚያደርገውን ይህንን መግለጫ በቀጥታ ለማስተላለፍ ከአርትስ ቲቪ (Arts TV) ጋር ስምምነት ተፈራርሞ ነበር። ሆኖም ግን የሚመለከታቸው አካላት በጣቢያው ላይ በጣሉት ጥብቅ እገዳ ምክንያት የቀጥታ ስርጭቱ እንዲቋረጥ ተገዷል። .... የ"ኢትዮሪካ" አልበም ገና ሳይለቀቅ እንዲህ ያለ ከፍተኛ መነጋገሪያና ውጥረት መፍጠሩ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። #MinilikSalsawi

Selam/
Senior Member
Posts: 17842
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የቴዲ አፍሮ "ኢትዮሪካ" አልበም መግለጫ ታገደ!

Post by Selam/ » 14 Apr 2026, 07:14

የኢትዮጵያዊነትን ማማ ያሳዬውን ኩሩውን የአቶ ካሣሁን ገርማሞን አንበሳ ፣ እንክርዳድ የሸኔና የፒፒ ካድሬዎች ጠልፎ ለመጣል ሲፍጨርጨሩ ስምንት ዓመት ሞላቸው። ወያኔም ሞክራ በስተመጨረሻ አፈር ድሜዋን ነው የበላችው።



Post Reply