Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13227
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ታላቋ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስደተኛ ልጆቿን የመንከባከብ አቅም ይኖራታል! ይህ ወጣት ሁሉ ባገሩ ፋብሪካ ይቀጠራል!

Post by DefendTheTruth » 28 Mar 2026, 16:01

የዞረበት ወጣት ብቻ ነዉ በአሁን ጊዜ ከኢትዮጵያ ዉጪ የተሻለ ሕይወት ለመፈለግ ወደ ሌላ አገር ለመፍለስ የምሞክር። ድንቁሪና ታክሎበት። ኢትዮጵያ ማለት በአንድ የኢንቨስትመንት መድረክ 13 ቢሊዮን ዶላር ዉል መፈራረም የምቻልበት አገር ናት። በአገር ደረጀ ይህ እየሆነ፣ ግለሰቦች፣ እንዴት አድርጌ ድርሻዬን አገኛለሁ ብሎ እንደማሰብ ልሰደድ ማለት፣ ድንቁሪና ብቻ ነዉ መሰለኝ።


Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ታላቋ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስደተኛ ልጆቿን የመንከባከብ አቅም ይኖራታል! ይህ ወጣት ሁሉ ባገሩ ፋብሪካ ይቀጠራል!

Post by Horus » 28 Mar 2026, 22:34

በ2026 ኢትዮጵያ ምናልባት 135 ሚሊዮን ሕዝብ አላት ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሚዲያን እድሜ 19 ዓመት ነው ። በእስታጽቲክስ ሚዲያን ማለት ከመቶ ሰዎች ውስጥ 50ኛው ሲሆን ፣ ይህም ማለት ከ135 ሚሊዮኑ ሕዝብ ግማሹ (50%) 19 ዓመትና ከዚያ በታች እድሜ ያለው ነው ። ማለትም ከ1 ዓመት ህጻን እስከ 19 ዓመት እድሜ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 65.5 ሚሊዮን ነው።

በአገራችን በትምህርት እድሜ ላይ ያለ ወጣት ሁሉ ትምህርት ገበታ ላይ ስለማይገኝ ከዚህ የወጣት ቁጥር ለምሳሌ ከ15 እስከ 19 ዓመት ውስጥ ካሉት ስንቱ ሥራ እንደ ሚፈልጉ ለማወቅ ያስቸግራል። ግ ን ብዙ ናቸው።

ሲቀጥል ከ135 ሚሊዮኑ ሕዝባችን ወደ 70% ከ40 ዓመት በታች እድሜ ያለው ነው ። ማለት 94 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ40 ዓመት እድሜ በታች ነው። ይህም ማለት በ20 ዓመት እና 40 ዓመት እድሜ መሃል ያሉት ሕዝብ ቁጥር ወደ 30 ሚሊዮን ይሆናሉ። ይህ 30 ሚሊዮን በሙሉ ሥራ ፈላጊ ወጣት ሕዝብ ነው።

አሁን እንዲያም በ45 ዓመት እድሜና በ65 ዓመት እድሜ መሃል ያሉትን ምናልባትም ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን መጨመር አለብን።

ስለዚህ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ቢያንስ ለ60 ሚሊዮን ሕዝብ ሥራ መፍጠር አለባት ማለት ነው። ይህ ቁጥር ለአንጎል ግምት እንኳ አስቸጋሪ ነው።

ዛሬ ላይ ባገሪቱ ትልቁ ቀጣሪ መንግስት ሲሆን የቀጠረው 1 ሚሊዮን ሰው ብቻ ነው።

ዛሬ ላይ ትልቁ የግል ሥራ ቀጣሪ ያላሙዲን ሚድሮክ ሲሆን የቀጠረው 80 ሺ ሰው ብቻ ነው።

ባገርቱ ውስጥ ግን 60 ሚሊዮን ሥራ ፈላጊ አለ!

ስለዚህ ኢትዮጵያ በግድ በግድ የግል ሥራና የግል ባለሃብት የሚያስፈልጋት አገር ነች ።


Selam/
Senior Member
Posts: 17813
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ታላቋ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስደተኛ ልጆቿን የመንከባከብ አቅም ይኖራታል! ይህ ወጣት ሁሉ ባገሩ ፋብሪካ ይቀጠራል!

Post by Selam/ » 28 Mar 2026, 23:57

ጩሎው ካድሬ

እናንተ ዳይፐር ላይ የምትሸኑትን የዌልፌር አዛውንት ካድሬዎችንስ መቼ ይሆን ፐርዳይም እየበጠሰች የምትንከባከባችሁ?

ክፉ!

Post Reply