Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4617
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

አዲስ አበባ ፖሊስ መፍረስ አለበት : ራሱ ምን አንደሆነ ግልፅ አይደለም

Post by Abaymado » 25 Mar 2026, 03:33

አዲስ አበባ ፖሊስ የተቋቋመው በወያኔ ግዜ ራሱን አንዲጠቅም ተደርጎ ነው:: አና የወጣው ሕግ የነበረውን መንግስት ጥቅም አንዲያስጠብቅ ሆኖ ነበር የሰራው:: አውነት አንነጋገር ከተባለ የአዲስ አበባን ሕዝብ አይወክልም::
በመጀመሪያ ደረጃ አዲስ አበባ ፖሊስ ማለት ምን ማለት ነው?
ሁሉም ክልል የራሱ ፖሊስ አለው: አዲስ አበባም የራሱ ፖሊስ ይኑረው ብለው ነው ያቋቋሙት: ልክ አንደሌላው ክልል የአዲስ አበባ ፖሊስ ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ሕዝብ መሆን ነበረበት:: ፖሊስ ሲመለመልም ከአዲስ አበባ ነዋሪና ብዙ ዓመት ከኖረ መሆን ነበረበት፡ ደሞዝ የሚከፍለውም የአዲስ አበባ ሕዝብ ነው:: ከግብር የሚሰበሰበው ብር ነው ለደሞዝ የሚከፈለው::
አና የአዲስ አበባ ፖሊስ ይህንን አሟልቷል?

የሚያገኙት ደሞዝ ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀ በላይ ነው: ይህ አንዴት ይሆናል? ኮማንደር ለመሆን ምንም ልፋት ሳይኖረው በየሁለት ዓመቱ በሚያገኘው የማአረግ አድገት ነው ::
አናስ የአዲስ አበባ ፖሊስ አንደገና መቋቋም የለበትም?