Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7365
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?

Post by Naga Tuma » 07 Mar 2026, 17:27

እዚህ መድረክ ላይ መላልሼ እንደጻፍኩኝ እኔ ስለመለኮታዊ ነገሮች ያጠና እና ዕዉቀት ያለዉ ሰዉ ኣይዴለሁም።

ከብዙ ዓመታት በፊት ሰምቻቸዉ የሰዉ ግምት እና የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ናቸዉ ብዬ ያለፍኩዋቸዉ ኣሉ።

ሁለቱ የማልረሳቸዉ ኣንዱ በወቅቱ የድፕሎማ ትምህርት ደረጃ የነበረዉ እስልምና ተከታይ የሐረርጌ ሰዉ ነበር። ከኣሁን በፊት ነብዮች እንደተወለዱት ለወደፊትም ነብይ ይወለዳል ወይም ሊወለድ ይችላል የሚል ነበር።

ሌላዉ ኣንድ ቀን ብቻ በስልክ ያናገረኝ እስልምና ተከታይ የባሌ ሰዉ ነበር። ኣንድ ኣዲስ ድርጅት ዉስጥ ተሳትፎ ስለኣቆምኩ በዛ ምክንያት ስንወያይ የሰዉ ልጅ መንገድ በመለኮታዊ አሰራር የሚመራ ነዉ የሚል ነበር። እንደዛ ዐይነት አስተሳሰብ ከዛ በፊት ሆነ ከዛ በኋላ ሰምቼ ኣላዉቅም።

ስለ መለኮታዊ አሰራር ያላጠናሁ ብሆንም የማነባቸዉ እና የምገነዘባቸዉ ሌሎች ሰዎች ከሚገልጹበት ጋር ተመሳሳዮች ኣሉ። ትይዩ የሆኑ ነገሮችም ኣሉ።

ያላመለኮታዊ አሰራር ማብራራት የማይቻሉ ታሪኮችን ተገንዝቤኣለሁ የሚል ሰዉ ነኝ።

ከኣሁን በፊት ኤርትራ በሚል ስም ከሚሳተፍ ሰዉ ጋር የማይረሳ ዉይይት ኣድርጌኣለሁ።

የተጻፉ ትንቢቶች እየተፈፀሙ ያሉበት ዘመን ላይ ነን የሚል አስተሳሰብ ኣለዉ።

አስተሳሰቡን ሳልቃወም እሱ ይታየኛል የሚለዉ መንገድ እና የእኔ ግንዛቤ መንገድ የተለያዩ ይመስላሉ ብዬዉ ነበር።

ተጨማሪ በሆኑ ነገሮች ምክንያት ከስደት በኋላ ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ ከስደት በፊት ታላቅ ፈረዖ አከናተን ከሆነ፣ የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት የተባለዉ ያልተፈፀመ እና የሚፈፀም የፈረዖ አክናተን ትንቢት ሊሆን ይችላል ወይ እያልኩ ነዉ።

ይህ አስተሳሰብ የምያሳምነዉ ሌላ ሰዉ ኣለ ወይ?


Naga Tuma
Member+
Posts: 7365
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?

Post by Naga Tuma » 08 Mar 2026, 19:59

ነምን ህን ሶበ፣ ኡርጂን ህን ሶቡ ኣለ የቦረና ሰዉ ደበሳ ጉዮ።

የክርስትና ታሪክ ከፈረዖዎች ታሪክ የተሰረቀ ነዉ ከተባለ የፈረዖዎች ታሪክ ሆነ ኣሁንም ያልተገነዘበ ያታላቁ ፈረዖ ትንቢት ያለ ከሆነ ታሪኩ የሚጻፈዉ እና ትንቢቱ የሚገለጠዉ ወደ ፊት ነዉ ማለት ኣይቻልም?

Naga Tuma
Member+
Posts: 7365
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?

Post by Naga Tuma » 11 Apr 2026, 12:29

ይህ ጥያቄዬ ጥልቅ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ሁለት እርስ በእርስ የማይተዋወቁ ሰዎች፣ ማለትም eritrea እና እኔ፣ የዚህን ዘመን ክስተቶችን ኣስተዉለን የመለኮታዊ አሰራር ኣመልካቾች ይመስላሉ ካልን ሁለታችንም መለኮታዊ አሰራር መኖሩን የምንገነዘብ ነን ማለት ይቻላል።

ክስተቶቹ ወደ ተለያዩ ኣቅጣጫዎች ኣመልካቾች ናቸዉ የምንል ከሆነ ያልተመለሰ ጥያቄ ኣለ ማለት ነዉ።

ኣይዴለም?

Naga Tuma
Member+
Posts: 7365
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?

Post by Naga Tuma » 20 Apr 2026, 21:59

ብዙዎች ዓመታትን ወደ ኋላ እያየሁ እና የዚህን ግዜ ዉሎዎችን እያስተዋልኩ ዐለምን ሁሉ ኣሳማኝ ሊሆን የሚችል መለኮታዊ ክስተት በኢትዮጵያ በኩል እየተፈጸመ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ይህ የዚህ ዘመን መለኮታዊ ክስተት በጥንታዊ የኢትዮጵያ ፈረዖዎች በኩል እና በጥንታዊ የኢትዮጵያ ቦረናዎች በኩል ሆኖ ክርስትናን ጡረታ የምያወጣ እና ፈርሃ እግዝኣብሔርነትን በዐለም ላይ የምያነግስ ሊሆን ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።

በዚህም ምክንያቶች የተገለጡልኝ የምላቸዉን ወይም የሚመስሉኝን ስመክር ሰንብቻለሁ።

ይህ ምክሬ ለብዙዎች የኣንድ ግለሰብ ምናብ እንደመሰላቸዉ እገምታለሁ።

እኔ ስመክር የሰነበትኩኝ ኣንድ ፐርሰንት እንኳን ትክክል ከሆነ እና የኣንድ ግለሰብ ምናብ ናቸዉ የሚሉት ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት ትክክል ከሆኑ የሚወስዱት ርስክ እንፍኒቲ ነዉ።

ምክንያቱም ዬለም ያሉት ኣለ ከተባለ ኣንድ ፐርሰንትም ቢሆን በእንፊኒቲ ሲባዛ ዉጤቱ እንፍኒቲ ነዉ።

ስለዚህ የራሳቸዉን ሴናርዮ ብቻ ከማራመድ ሁለቱንም ሴናሪዮዎች ጎን ለጎን ማራመድ ይቻላል።

ስለ መለኮታዊ ክስተቶች ምልክቶችን ማወቅ የሚችሉት ቃሉዎች፣ ቄሶች፣ ሼሆች፣ ወዘተ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ስለ መለኮታዊ ክስተቶች ያላቸዉ ዕዉቀት ለሺህዎች ዘመናት ባህል ሆነዉ የኖሩ ስለሆነ ብዙዎቹ ያልተጠኑ ስህተቶች ይሆናሉ።

ቢሆንም ሳይናቁ ቢጠኑ ኣንድ ቃሉ ወይም ቄስ ወይም ሼህ ስለ መለኮታዊ ክስተት ምልክቶች መቶ ነገሮችን ቢናገር ምናልባት ኣንዱ ኣሳማኝ ሊሆን ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።

ኣንድ ኣሳማኝ የሆነ ምልክት ከተገኘ ለሌሎች ምልክቶች ጥናት ሆነ ማለት ነዉ።

ኣንድ ከተስተዋለ የመለኮታዊ ተዓምራዊ አሰራር ስክሪፕት ተገኘ ማለት ነዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7365
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የተፈፀመ የሙሴ ትንቢት ኣለ ከተባለ ፈረዖ አክናተን ትንቢት የነበረዉ ሊሆን ይችላል?

Post by Naga Tuma » 20 Apr 2026, 22:33

የተፈጸመ የሙሴ ትንቢት ያልተፈጸመ የፈረዖ አክናተን ትንቢት ሊሆን ይችላል ወይ ለማለት ምክንያቶች ዉስጥ ሁለቱ፥

ኣንዱ የዚህ ዘመን ክስተቶች በመላዉ ዐለም ኢን ሪል ታይም መሆናቸዉ ነዉ።

ሌላዉ የሃይማኖት ትምህርቱ ከክርስትና ጋር ተፎካካሪ የነበረዉ የፐርሽያዉ ፕሮፌት ማኒ ስም በዚህ ዘመን መነሳት ነዉ።

አክናተን ማለት አሙን ኢዝ ሳቲስፋይድ ማለት ነዉ።

ስለዚህ ይህ ርዕስ ሁለት የጥንት ነብዮችን ወይም ፕሮፎቶችን ይመለከታል።

የሁለቱም ፕሮፌቶች ስሞች በዚህ ዘመን መነሳት ክስተት ነዉ ወይ ያስብላል።

Post Reply