Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7179
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ስምንተኛዉ ሺህ ማለት የተለመደባት የፍጥረት በር ኢትዮጵያ፥ ልጆችሽ እግዝኣብሔር ኣለ እና ዬለም የምል ክርክር ስለጀመሩ ተዓምር ነዉ በይ

Post by Naga Tuma » 05 Mar 2026, 19:46

እኔ ስለ መለኮታዊ ነገር ያጠናሁ ሰዉ ኣይዴለሁም።

የሃገሬ ሰዎች በመለኮታዊ ነገር ከልብ ማመን ከመጠን በላይ እየመሰለኝ የኖርኩ ሰዉ ነኝ።

በመለኮታዊ ነገር የማያምን ብቻ ሳይሆን ያለመለኮታዊ ነገር ሆነ ብሎ እየተከራከረ ፖለትካን ለማራመድ የሚጥር የሃገሬ ሰዉ በህይወቴ ዉስጥ ያጋጥመኛል ብዬ ኣልጠበኩም።

ይህ ክርክር ለገባቸዉ የእግዝኣብሔር ኣለ እና ዬለም ክርክር ሆኗል።

እኔ እግዝኣብሔርን በዐይኖቼ ኣይቼ ኣላዉቅም። ጆሮዎቼ ድምጹን ሰምተዉ ኣያዉቁም።

ነገር ግን በምክንያታዊ ክንዉን ሳይንሳዊ አስተሳሰብ የማምን ሰዉ ብሆንም ያለመለኮታዊ አሰራር ይከሰታሉ ብዬ የማላምን ተዓምራትን የምቆጥር ሰዉ ነኝ።

ስለዚህ እግዝኣብሔር ዬለም የሚሉት ኢትዮጵያዊያን ስለ ኮምኒዩዝም ከዉጪ ሰምተዉ ወደ ኢትዮጵያ ይግባ ወይም እምፖርት እናድርግ እንዳሉት እግዝኣብሔር ዬለም ማለትንም ከዉጪ ሰምተዉ ወደ ኢትዮጵያ እምፖርት እናድርግ የሚሉ ይመስለኛል።

ይህ ዳያብሎሷን በዳያብሎስ እንተካ ዐይነት ክርክር ይመስላል። እንግልዛዊ ሆነች፣ አሜሪካዊ ሆነ፣ ወይም ሌላ ዳያብሎሳዊ ዳያብሎሳዊ ነዉ፣

እግዝኣብሔር ኣለ ብላችሁ የምታምኑ ማስረጃዎች ናቸዉ ብላችሁ የምታምኑ ተጨባጭ ክስተቶችን መጥቀስ ትችላላችሁ?

እኔ ከኣንድ ተጨባጭ ክስተት እጀምራለሁ።

ይህ ክስተት ያለመለኮታዊ አሰራር ሊሆን ይችላል ብሎ ማብራራት የሚችል የሰዉ ልጅ ከተገኘ ተጋባዥ እንግዳዬ ይሆናል።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7179
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ስምንተኛዉ ሺህ ማለት የተለመደባት የፍጥረት በር ኢትዮጵያ፥ ልጆችሽ እግዝኣብሔር ኣለ እና ዬለም የምል ክርክር ስለጀመሩ ተዓምር ነዉ በይ

Post by Naga Tuma » 06 Mar 2026, 05:59

እግዝኣብሔር ባዩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ባለህበት፥

የድሮ ተማሪህ፣ አሜሪካ ኣንድ ቀን ጓደኛህን ስትጠይቅ እግረመንገድህን የተገናኘን ሰዉ ነኝ።

ስምህን እዚህ የማናሳዉ በቅንነት ነዉ።

የኢትዮጵያ እስር ቤት የሚናገረዉ ኦሮምኛ ነዉ የተባለ ዘመን እኔ ዉጪ ሃገር እየኖርኩ ሃገር ዉስጥ የነበረዉ የፖለትካ ጫና ስያሳስበኝ የኖርኩ ሰዉ ነኝ።

በአደዋ ግዜ እና የጣልያን ወረራ ግዜ ከሃገሩ ወገኖች ጋር ቆሞ የተከበረ ሕዝብ የፖለትካ ጫና ወደ ሰፈሩ የመጣበት ዘመን ነበር።

ምናልባት የመለኮታዊ ተዓምራዊ አሰራር ምስክር ልትሆን ትችላለህ ብዬ ኣስባለዉ።

ተዓምራዊ አሰራሩ የፖለትካ ጫናዉ እንዲቀየር የፖለትካ ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆነዉ መረራ ጉድና እና አቶ ግርማ ብሩ ከነበራቸዉ ይልቃል ብዬ ኣስባለሁ።

የሚከተለዉ ታሪክ በምን ተዓምር ሊሆን እንደሚችል ማብራራት ያስቸግረኛል።

እስቲ ኣንብቦ ማብራራት የሚችል ሰዉ ይገኛል?

የታሪክ ሐቆች፥

1) ከዉሳኔ 96 በፊት ዶክተር ስለሺ በቀለ አሜሪካ መጥቶ ነበር።

ዉሳኔ 96 የምለዉ የኦሮምያ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ ይዛወር የተባለዉ ነዉ።

በእኔ አስተያየት ዉሳኔ 96 እና ምርጫ 97 የኢትዮጵያን የፖለትካ ኣቅጣጫ ቀይረዋል።

2) ጓደኛዉን ሲጠይቅ እግረመንገዱን እንድንገናኝ ጠይቆ ኣንድ ቀን ተገናኝተናል።

3) የተገናኘን ቀን እኔ ያልተሳተፍኩበት ኣንድ ደቂቃ የማይሞላ ግዜ ዉስጥ የሚከተለዉን አስተያየቶች ሰምቻለሁ።

በወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች ዉስጥ ኣዕምሮ ያላቸዉ ተብሎ ኣንድ ሰዉ ኣንድ ኤከሌ ነዉ ሲል ሌላዉ ሰዉ እከሌ እና እከሌ ናቸዉ ማለታቸዉን ሰምቻለሁ።

4) በኣጋጣሚ ከመገናኘት በኋላ ሰንበት ብሎ የተለያየ አስተየየቶችን ታዝቤ ያለኝን አስተያየት ኣካፍዬ ወደ አካዳሚ ላተኩር ብዬ ጽፌኣለሁ። ባለ አረት ክፍል ጽሑፍ ሲሆን እከሌ ነዉ እና እካሌ እና እከሌ ናቸዉ የተባለዉን እኔ የጻፍኩት አስተያየት ዉስጥ ኣካትቻለሁ።

5) የዉሳኔ 96 መንስኤ ምን እንደሆነ ባላዉቅም እኔ የጻፍኩኝ አስተያየት በኋላ የተወሰነ መሆኑን ኣዉቃለሁ።

6) ነሓሴ 28፣ 2018፣ ዓም የሚከተለዉን ጥያቄ እዚህ መድረክ ላይ ጠይቄኣለሁ፥ “… አምላክ ምን እንደሆነ እና አሰራሩ እንዴት እንደሆነ እንዲገባህ ማጥናት ትችላለህ?”

“አምላክ ማለት ብቻ ሳይሆን መኖሩ የተገለጠልህ እና የምታምን ከሆነ ነዉ።”

7) ከዚህ ጥያቄ በኋላ የሚከተለዉ ቪድዮ ተለጥፏል።



እኔ ጥያቄዉን ስጠይቅ ቪድዮዉ መኖሩን ኣላዉቅም ነበር።

ይህ ቪድዮ የተቀዳዉ ለቅንነት ይሁን ለተንኮል ዶክተር ስለሺ በቀለ ማወቁን ኣላዉቅም።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7179
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ስምንተኛዉ ሺህ ማለት የተለመደባት የፍጥረት በር ኢትዮጵያ፥ ልጆችሽ እግዝኣብሔር ኣለ እና ዬለም የምል ክርክር ስለጀመሩ ተዓምር ነዉ በይ

Post by Naga Tuma » 06 Mar 2026, 16:29

ይህ መለኮታዊ ምልክት ያላቸዉ ከሚመስሉ ገጠመኞች ዉስጥ ኣንዱ ነዉ ያልኩኝ ነዉ።

ሰዎች መለኮትን ፍሩ ብዬ ከለጠፍኩኝ ርዕስ ዉስጥ ኣንዱ ነዉ።

Post Reply