Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 17 Feb 2026, 08:46

16/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፥- ኣብ ንሓድሕድና ኣይንፍረድ ወይ ኣይንነዓዓቕ፡ ንኣሕዋትና ዕንቅፋት ከይንኸውን ንጠንቀቕ።

ሮሜ 14፡10- ፍጻሜ
10 አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።
11 እኔ ሕያው ነኝ፥ ይላል ጌታ፥ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል መላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና።
12 እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
13 እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንፈራረድ፤ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቍረጡ።
14 በራሱ ርኵስ የሆነ ነገር እንደ ሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኵስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኵስ ነው።
15 ወንድምህንም በመብል ምክንያት የምታሳዝን ከሆንህ እንግዲህ በፍቅር አልተመላለስህም። ክርስቶስ ስለ እርሱ የሞተለትን እርሱን በመብልህ አታጥፋው።
16 እንግዲህ ለእናንተ ያለው መልካም ነገር አይሰደብ፤
17 የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።
18 እንደዚህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛልና፥ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።
19 እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል።
20 በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ንጹሕ ነው፥ በመጠራጠር የተበላ እንደ ሆነ ግን ለዚያ ሰው ክፉ ነው።
21 ሥጋን አለመብላት ወይንንም አለመጠጣት ወንድምህም የሚሰናከልበትን አለማድረግ መልካም ነው።
22 ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ለራስህ ይሁንልህ። ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቈጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብፁዕ ነው።
23 የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው።


ቀስተ ጸሎት፡ - እግዚኣብሔር ሠናይ ኢዩ፡ ምሕረቱ ንዘለአለም ይነብር እዩ’ሞ ኣመስግንዎ።

መዝ 118፡ 1-14
1እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ናትና።
2 ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች የእስራኤል ቤት አሁን ይንገሩ።
3 ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች የአሮን ቤት አሁን ይንገሩ።
4 ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘላለም እንደ ሆነች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይንገሩ።
5 በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ሰማኝ አሰፋልኝም።
6 እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል?
7 እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ እኔም በጠላቶቼ ላይ አያለሁ።
8 በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
9 በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይሻላል።
10 አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤
11 መክበቡንስ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤
12 ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንዲነድድ ነደዱ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው።
13 ገፋኸኝ፥ ለመውደቅም ተንገዳገድሁ፤ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ።
14 ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 17 Feb 2026, 10:17

17/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ቃል እግዚኣብሔር ይፈጥር፣ ይልውጥ፣ ሕይወት ይዘርእ፡ ስለዚ ነንብቦ፡ ንፍለጦ ንንበሮ።
ኢሳ 55፡ 10-11
10 ፤ ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥
11 ፤ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።

ቀስተ ጸሎት፡ - ቃል እግዚኣብሔር ኩሉ ሓቂ እዩ፡ ተግባሩ ኩሉ’ውን እሙን እዩ።
መዝ 33፡ 1-12
1ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖች ምስጋና ይገባል።
2 እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት።
3 አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ፤
4 የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና።
5 ጽድቅንና ፍርድን ይወድዳል፤ የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች።
6 በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤
7 የባሕርን ውኃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው፥ ቀላዮችንም በመዝገቦች የሚያኖራቸው።
8 ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፥ በዓለም የሚኖሩ ሁሉም ከእርሱ የተነሣ ይደንግጡ።
9 እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።
10 እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል።
11 የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘላለም ይኖራል። የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
12 እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።

Abere
Senior Member
Posts: 15174
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Abere » 17 Feb 2026, 15:18

ወንድም መለከት፤

ቃለ ህይወት ያሰማልን!
እንኳን ለዐብይ ጾም በሰላም እና በጤና አደረሰህ!

በእውነቱ የአዳም ዘር መልካም የሆነውን የእግዚአብሄር መንገድ በመሳቱ ምክንያት የዚህ ዓለም ከባድ ቀንበር ተሸክሞ የሰይጣን መገለጫ እኩይ ባህርይ የሆኑት ሁከት፤ ዋይታ፤ ጦርነት፤ ችግር፤ ወዘተ መርገምት ይጨፍሩበታል። እነኝህ ምግባረ እኩያን ግን ዋጋ ያስከፍላሉ፤ ክፉ ዋጋ።
ቃለ እግዚአብሄር ግን ያለምንም ዋጋ ንጹህ ልብ እና ፍቅር ብቻ የሚጠይቅ እንድሁ በነጻ የሚገኝ በጎ ምርጫ ነው።
እንደዚህ ያለ ቃለ እግዚአብሄር የምህረት እና የሰላም በረከት ያወርዳል። መቸም እንደ ሰው ግምት ( እንደ ፈጣሪ ሳይሆን) ከዚህ ፎረም አንዳንዶቹ ፈጽሞ ማተብ የሌላቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ማተባቸውን የበጠሱ - ሁሉም ግን በግብረ-ዲያብሎስ የተጠመዱ ማየት ያሳዝናል። ለማለት የሚቻለው አንድ ነገር ብቻ ነው - እግዚአብሄር በተዐምሩ በልቦናቸው ይግባ- ከማተቡ ዕድል ይድረሳቸው ነው።

አረጋዊው ስምዖን እየሱስ በህጻንነቱ ቤተ መቅደስ ሲገኝ በእቅፉ ሲያዘው አምላኬን በማምሻ ዕድሜ በማየቴ ዕድለኛ ነኝ ብሎ ነበረ (ሉቃስ 2፡ 25-35) ፤ ከዚህ ፎረም ግን በ84 አመታቸው ኢህፓ፤መኢሶን፤ ደርግ-ኢሰፓ(ነጭ ቀይ ሽብር የተጫዎቱ)፤ ወያኔ /ኢህአድግ፤ አሁን ደግሞ ኦሮሙማ ኮሬ-ነጌኛ ሁነው እንደ ሃብታም ምጥዳ ከዚህ ፎረም 24/7 ተጥደው የአብይ አህመድ(ሊቀ-ሰይጣን) ውታፍ ነቃይ የዕልቂት ተባባሪ ታያለህ።

ለማለት የሚቻለው ዕሪያ ውስጥ ገብቶ የበጠብጠውን ቡዔል ዘቡዔል ያስወጣ እግዚአብሄር ከልቦናቸው ያስወጣው - ዙሮ አይፈልጋቸው ብቻ ነው።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 18 Feb 2026, 02:25

አሜን ወንድም Abere!

እንኳን ለዐብይ ጾም በሰላም እና በጤና አብሮ አደረሰን!

Abere wrote:
17 Feb 2026, 15:18
ወንድም መለከት፤

ቃለ ህይወት ያሰማልን!
እንኳን ለዐብይ ጾም በሰላም እና በጤና አደረሰህ!

በእውነቱ የአዳም ዘር መልካም የሆነውን የእግዚአብሄር መንገድ በመሳቱ ምክንያት የዚህ ዓለም ከባድ ቀንበር ተሸክሞ የሰይጣን መገለጫ እኩይ ባህርይ የሆኑት ሁከት፤ ዋይታ፤ ጦርነት፤ ችግር፤ ወዘተ መርገምት ይጨፍሩበታል። እነኝህ ምግባረ እኩያን ግን ዋጋ ያስከፍላሉ፤ ክፉ ዋጋ።
ቃለ እግዚአብሄር ግን ያለምንም ዋጋ ንጹህ ልብ እና ፍቅር ብቻ የሚጠይቅ እንድሁ በነጻ የሚገኝ በጎ ምርጫ ነው።
እንደዚህ ያለ ቃለ እግዚአብሄር የምህረት እና የሰላም በረከት ያወርዳል።
መቸም እንደ ሰው ግምት ( እንደ ፈጣሪ ሳይሆን) ከዚህ ፎረም አንዳንዶቹ ፈጽሞ ማተብ የሌላቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ማተባቸውን የበጠሱ - ሁሉም ግን በግብረ-ዲያብሎስ የተጠመዱ ማየት ያሳዝናል። ለማለት የሚቻለው አንድ ነገር ብቻ ነው - እግዚአብሄር በተዐምሩ በልቦናቸው ይግባ- ከማተቡ ዕድል ይድረሳቸው ነው።

አረጋዊው ስምዖን እየሱስ በህጻንነቱ ቤተ መቅደስ ሲገኝ በእቅፉ ሲያዘው አምላኬን በማምሻ ዕድሜ በማየቴ ዕድለኛ ነኝ ብሎ ነበረ (ሉቃስ 2፡ 25-35) ፤ ከዚህ ፎረም ግን በ84 አመታቸው ኢህፓ፤መኢሶን፤ ደርግ-ኢሰፓ(ነጭ ቀይ ሽብር የተጫዎቱ)፤ ወያኔ /ኢህአድግ፤ አሁን ደግሞ ኦሮሙማ ኮሬ-ነጌኛ ሁነው እንደ ሃብታም ምጥዳ ከዚህ ፎረም 24/7 ተጥደው የአብይ አህመድ(ሊቀ-ሰይጣን) ውታፍ ነቃይ የዕልቂት ተባባሪ ታያለህ።

ለማለት የሚቻለው ዕሪያ ውስጥ ገብቶ የበጠብጠውን ቡዔል ዘቡዔል ያስወጣ እግዚአብሄር ከልቦናቸው ያስወጣው - ዙሮ አይፈልጋቸው ብቻ ነው።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 18 Feb 2026, 02:33

18/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ ፡- ንኣምላኽ ዝፈርሕን ቅንዕና ዝገብርን እንተሎ፡ ኣብ ኣምላኽ ኣድልዎ ስለዘየለ፣ ህያብ መንፈስ ቅዱስ ይቕበል።

ግ.ሓ 10፡ 34 - 38
34 -35 ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ። እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ።
36 የሁሉ ጌታ በሚሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እስራኤል ልጆች ላከ።
37 ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በይሁዳ ሁሉ የሆነውን ነገር እናንተ ታውቃላችሁ።
38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤

ቀስተ ጸሎት ፡- ኣብ እግዚኣብሔር ዝምዕቆቡ ኩሎም ዕዉታት (ብፁዓን) እዮም።
መዝ 6፡ 1 - ፍጻሜ
1 አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ።
2 ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ማረኝ፤ አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ።
3 ነፍሴም እጅግ ታወከች፤ አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?
4 አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ።
5 በሞት የሚያስብህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
6 በጭንቀቴ ደክሜያለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።
7 ዓይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች፤ ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ አረጀሁ።
8 ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።
9 እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ።
10 ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ እጅግም ይጐስቍሉ፤ ወደ ኋላቸው ይመለሱ፥ በፍጥነትም ይፈሩ።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 19 Feb 2026, 08:10

19/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ብዘይ ቅድስና ሓደ’ኳ ንኣምላኽ ዝርእዮ የልቦን’ሞ፣ ቅዱሳን ክንከውን ንጽዓር።
ዕብ 12፡12-17
12 ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤
13 ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።
14 ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።
15 የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥
16 ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።
17 ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና።

ቀስተ ጸሎት፡ - ንስም እግዚኣብሔር ኣብ ኣውጅዎን ኣመስግንዎን።
መዝ 137፡ 1-ፍጻሜ
1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።
2 በአኻያ ዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።
3 የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም። የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።
4 የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
5 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ።
6 ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።
7 አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ። እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።
8 አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።
9 ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።


Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 20 Feb 2026, 04:29

20/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ሓውኻ ተቐዪሙልካ ከምዘሎ እንተዘከርካ፣ ኪድ ቅድም ምስ ሓውኻ ተዓረቕ፡ ደሓር ናብ ኣምላኽ ጸሎትካ ተቕርብ፡ ይቕበለልካ ከኣ።
ማቴ 5፡ 17-26
17 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።
18 እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።
19 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።
20 እላችኋለሁና። ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።
21 ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።
22 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
23 እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥
24 በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።
25 አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤
26 እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።

ቀስተ ጸሎት፡ - ኪድ ቅድም ምስ’ቲ ሓውኻ ተዓረቕ።
መዝ 129፡ 1- ፍጻሜ
1 እስራኤል። ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ይበል፤
2 ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።
3 ኃጢአተኞች በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኃጢአታቸውንም አስረዘሙአት።
4 እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ የኃጢአተኞችን አንገታቸውን ቈረጠ።
5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።
6 በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥
7 ለሚያጭደው እጁን፥ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።
8 በመንገዱም የሚያልፉ። የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 20 Feb 2026, 08:57

21/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ስም ኢየሱስ ተኣምራት ዝገብር ሓይሊ ኣለዎ፡ ብእምነት ምስ እንጽውዖ ከኣ የሕውየና።
ግ.ሓ 3፡ 11-16
11 እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።
12 ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ?
13 የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው።
14 እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፥
15 የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፥ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን።
16 በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፥ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው።

ቀስተ ጸሎት፡ - ንኣይ ግና ናብ ኣምላኽ ምቕራብ ይሕሸኒ።
መዝ 69፡ 1-16
1 አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ።
2 በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቋሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ።
3 በጩኸት ደከምሁ ጕሮሮዬም ሰለለ፤ አምላኬን ስጠብቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ።
4 በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጕር በዙ፤ በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፤ በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።
5 አቤቱ፥ አንተ ስንፍናዬን ታውቃለህ፥ ኃጢአቴም ከአንተ አልተሰወረም።
6 አቤቱ የሠራዊት አምላክ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይፈሩ፤ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ የሚሹህ በእኔ አይነወሩ።
7 ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥ እፍረትም ፊቴን ሸፍናለችና።
8 ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥ ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው፥
9 የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
10 ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ።
11 ማቅ ለበስሁ ምሳሌም ሆንሁላቸው።
12 በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፤ ወይን የሚጠጡ እኔን ይዘፍናሉ።
13 አቤቱ፥ በመልካሙ ጊዜ ጸሎቴ ወደ አንተ ነው፤ አቤቱ፥ በምሕረትህ ብዛት በማዳንህም እውነት አድምጠኝ።
14 እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፤ ከሚጠሉኝና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ።
15 የውኃው ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥ ጕድጓድም አፉን በእኔ ላይ አይዝጋ።
16 አቤቱ፥ ምሕረትህ መልካም ናትና ስማኝ። እንደ ርኅራኄህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት።


Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 21 Feb 2026, 03:05

22/02/2026 - ሰንበት ዘቅድስት

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ንእግዚኣብሄር ዘሐጕስ ሕይወት ክንነብር እምበር ከቶም ንኣምላኽ ዘይፈልጡ ኣሕዛብ ብፍትወት ስጋና ከይንምራሕ፡ ንኣምላኽ እምበር ንገንዘብ ከይንግዛእ፡ ብፍቕሪ ክንነብር እምበር ንሓውና እናበደልና እናተበለጽናን ብርእሰይ-ይጥዓመኒ ክንነብር አይኮናን ተጸዊዕና።
1 ጴጥ 1፡ 13 - 25
13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።
14 እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
15 - 16 ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
17 ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
18 - 19 ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።
20 - 21 ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፥ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።
22 ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደደ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።
24 ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤
25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።

ቀስተ ጸሎት፡ - ፍቓድ ኣምላክ ንስኻትኩም ክትቅደሱን፡ ካብ ምንዝርና ክትርሕቁን እዩ።
መዝ 96፡ 1-6
1 ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፤ ምድር ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
2 እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ።
3 ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ፤
4 እግዚአብሔር ታላቅ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና።
5 የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
6 ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።


Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 23 Feb 2026, 05:41

23/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ከምቲ ወርቂ ብሓዊ ሓሊፉ ዝዅላዕ፡ ንሕናውን ኣብ ህይወትና ብብዙሕ ፈተናታት ክንሓልፍ እንከለና ኣብ እምነትና ክንዓቢ፡ ምሕረትን ፍቕሪን እግዚኣብሔር ከነስተማቕር ይገብረና።
ሉቃስ 4፡ 1-15
1 ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ከዮርዳኖስ ተመለሰ፥ በመንፈስም ወደ ምድረ በዳ ተመርቶ፥
2 አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።
3 ዲያብሎስም። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ይህን ድንጋይ። እንጀራ ሁን ብለህ እዘዝ አለው።
4 ኢየሱስም። ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት።
5 ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።
6 ዲያብሎስም። ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤
7 ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው።
8 ኢየሱስም መልሶ። ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው።
9 -ወደ ኢየሩሳሌም ደግሞ ወሰደው፤ በመቅደስም ጫፍ ላይ አቁሞ፦
10 ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፥ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና፦
11 የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ከዚህ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።
12 ኢየሱስም መልሶ። ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎአል አለው።
13 ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ።
14 ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው አገር ሁሉ ዝና ወጣ።
15 እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።

ቀስተ ጸሎት፡ - ቃልካ ንስጉምተይ መብራህቲ ንመንገደይ ብርሃን’ዩ።
መዝ 119፡ 1-8
1 በመንገዳቸው ንጹሐን የሆኑ፥ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።
2 ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፤
3 ዓመፅንም አያደርጉም፥ በመንገዶቹም ይሄዳሉ።
4 ትእዛዛትህን እጅግ እንጠብቅ ዘንድ አንተ አዘዝህ።
5 ሥርዓትህን ለመጠበቅ፤ መንገዶቼ ይቀኑ ዘንድ እወድድ ነበር።
6 ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም።
7 አቤቱ፥ የጽድቅህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።
8 ሥርዓትህን እጠብቃለሁ፤ በፍጹም አትጣለኝ። ቤት


Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 24 Feb 2026, 04:14

24/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ‘ንርእሰይ ይጥዓመኒ እምበር፡ ናይ ካልእ እንታይ ኣእተወኒ’ እናበልና ንርእስና ኣይንጠብር። ለጋሳት ንዅን፡ ከምቲ ኣምላኽ ብልግሲ ዝሃበና ንኣሕዋትና ነማቕል።
2ይ ቆሮ 8፡1-12
1 ወንድሞች ሆይ፥ ለመቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እናስታውቃችኋለን፤
2 በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፤
3 እንደ ዓቅማቸው መጠን ከዓቅማቸውም የሚያልፍ እንኳ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁና።
4 ለቅዱሳን በሆነው አገልግሎት እንዲተባበሩ ይህን ቸርነት በብዙ ልመና ከእኛ ይለምኑ ነበር፥
5 አስቀድመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለጌታ ለእኛም ሰጡ እንጂ እንዳሰብን አይደለም።
6 ስለዚህም ቲቶ አስቀድሞ እንደ ጀመረ እንዲሁ ደግሞ ይህን ቸር ሥራ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ሊፈጽም ለመንን።
7 ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነትና በቃል በእውቀትም በትጋትም ሁሉ ለእኛም በፍቅራችሁ እንደ ተረፋችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ትረፉ።
8 ትእዛዝ እንደምሰጥ አልልም፥ ነገር ግን በሌሎች ትጋት በኩል የፍቅራችሁን እውነተኛነት ደግሞ ልመረምር እላለሁ፤
9 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።
10 በዚህም ነገር ምክር እሰጣለሁ፤ ከአምና ጀምራችሁ ለማድረግ ብቻ ያይደለ ነገር ግን ለማሰብ ደግሞ አስቀድማችሁ የጀመራችሁት ይህ ይጠቅማችኋልና፤
11 አሁንም ለማሰብ በጎ ፈቃድ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እንዳላችሁ መጠን መፈጸም ደግሞ ይሆን ዘንድ፥ ማድረጉን ደግሞ ፈጽሙ።
12 በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም።

ቀስተ ጸሎት፡ - እቲ ንድኻ ዝህብ፡ ንእግዚኣብሔር ኣለቕሖ።
መዝ 92፡ 12-15
12 ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።
13 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
14 ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ።
15 አምላኬ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ ይነግራሉ፥ በእርሱም ዘንድ ዓመፃ የለም።


Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 25 Feb 2026, 03:18

25/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ብግልጺ እዚ ቃል ዝነግረና፡ እቲ ንሓዉ ዘየፍቅር ‘ንኣምላኽ ኣፍቕር’ እንተበለ ሓሳዊ እዩ። ንኣምላኽ ነፍቅሮ እንተደኣ ኮይንና ንኣሕዋትና ድማ ነፍቅሮም።
1ዮሓ 4፡7-21
7 ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።
8 ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።
9 በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።
10 ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
11 ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።
12 እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።
13 ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን።
14 እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።
15 ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።
16 እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
17 በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።
18 ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።
19 እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
20 ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
21 እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።

ቀስተ ጸሎት፡ - ኣምላኽ ፍቕሪ እዩ’ሞ እቲ ዘየፍቅር ንኣምላኽ ኣይፈልጦን እዩ።
መዝ 2፡10-12
10 አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ።
11 ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
12 ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 26 Feb 2026, 03:58

26/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ኣብ ትሕቲ’ታ ጽንዕቲ ኢድ ኣምላኽ ትሕት ኢልና፡ ኩሉ ዝኸብደናን ዝጨንቀናን ኣብ ኣምላኽ ብእምነት ነቕርቦ፡ ንዅሉ ሓልዮትና ኣብቲ ዝሓልየልና ኣምላኽ ነውድቆ።
1ጴጥ 5፡5-11
5 እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
6 እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
7 እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
8 በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤
9 በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
10 በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁምል ያበረታችሁማል።
11 ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።

ቀስተ ጸሎት፡ - ንሱ ይሓልየልኩም እዩ’ሞ ንዅሉ ሓልዮትኩም ኣብኡ ኣውድቕዎ።
መዝ 102፡ 18-22
18 ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ፥ የሚፈጠርም ሕዝብ ለእግዚአብሔር እልል ይላል፤
19 እግዚአብሔር ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና፤
20 የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ ሊገድሉ የተፈረደባቸውን ያድን ዘንድ፤
21 የእግዚአብሔርን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ፤
22 አሕዛብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ መንግሥታትም ለእግዚአብሔር ይገዙ ዘንድ።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 27 Feb 2026, 03:04

27/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ቃል ኩሉ ትእዛዛት ኣምላኽ ክንፍጽም እንተደሊና፡ እቲ ዝሓጸረ መንገዲ ንኣሕዋትና ምፍቃር እዩ። ፍቕሪ ንብጻያ ክፉእ ስለ ዘይትገብሮ፡ ኣብ ፍቕሪ እንተለና ኣብ ሓጢኣት ኣይንህሉን።
ሮሜ 13፡8-14
8 እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።
9 አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ የሚለው ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ። ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።
10 ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።
11 ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
12 ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
13 በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤
14 ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።

ቀስተ ጸሎት፡ - ንብጻይካ ከም ነፍስኻ ኣፍቅር።
መዝ 119፡ 71-72
71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።
72 ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል። ዮድ

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 28 Feb 2026, 04:47

28/02/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ናብቲ ጀማሪን ደምዳሚን እምነትና ዝኾነ ኢየሱስ ንጠምት፡ ብዝገጥመና ፈተና ኣይንተሓለል፡ እግዚኣብሔር ምስ እንጽውዖ ቀረባና እዩ።
ዕብ 12፡ 1-11
1 እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥
2 እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
3 በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ።
4 ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤
5 - 6 እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር። ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።
7 ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
8 ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
9 ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
10 እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።
11 ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።

ቀስተ ጸሎት፡ - ኣምላኽ ናይ ቅድስናኡ ተማቐልቲ ምእንቲ ክንከውን ኢሉ ንጥቕምና ይቐጽዓና።
መዝ 73፡ 27-28
27 እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው።
28 ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።


Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 28 Feb 2026, 05:34

01/03/2026 - ሰንበት ዘምኩራብ

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ልብና ቤት-መቕደስ ኣምላኽ እዩ። ልብና በይኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ክነግሰሉን ክገዝኦን እምበር ዓለማውነት፣ ሓጢኣት፣ ባህሊ፣ ስስዐ፣ ቂምን ጽልእን . . . ወዘተ መሊኡ ከይህሉ ኣብ ቅድሚ እግዚኣብሔር ትሕት ኢልና ልብና ንፈትሽ።
ዮሓ 2፡ 13-25
13 የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
14 በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤
15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥
16 ርግብ ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።
17 ደቀ መዛሙርቱም። የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።
18 ስለዚህ አይሁድ መልሰው። ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት።
19 ኢየሱስም መልሶ። ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።
20 ስለዚህ አይሁድ። ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት።
21 እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።
22 ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።
23 በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤
24 - 25 ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።

ቀስተ ጸሎት፡ - ‘ንቤት ኣቦይ ቤት ሸቐጥ ኣይትግበርዎ፡ ቤተይ ቤት ጸሎት እዩ ዝስመ።’
መዝ 69፡ 9-10
9 የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
10 ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 02 Mar 2026, 03:11

02/03/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ገና ሓጥኣን እንከሎና ክርስቶስ ኣብ ክንዳና ሞይቱ፣ በዚ ከኣ እግዚኣብሔር ኣብ ልዕሊ ነፍስወከፍና ዘለዎ ፍቕሪ ገለጸልና። እግዚኣብሔር ከምዘለናዮ ኩሉ ግዜ የፍቅረና።
ሮሜ 5፡ 1-11
1 እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤
2 በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን።
3 - 4 ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤
5 በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።
6 ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።
7 ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።
8 ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።
9 ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።
10 ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤
11 ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።


ቀስተ ጸሎት፡ - ውሉድ ኣምላኽ ተባሂልና ክንጽዋዕ እግዚኣብሔር ኣቦ ከመይ ዝበለ ፍቕሪ ለገሰልና። (1ይ ዮሓ 3፡1)
መዝ 31፡ 14-24
14 አቤቱ፥ እኔ ግን በአንተ ታመንሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ አልሁ።
15 ርስቴ በእጅህ ነው፤ ከጠላቶቼ እጅና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
16 ፊትህን በባሪያህ ላይ አብራ፥ ስለ ምሕረትህም አድነኝ።
17 አቤቱ፥ አንተን ጠርቻለሁና አልፈር፤ ክፉዎች ይፈሩ በሲኦልም ዝም ይበሉ።
18 በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።
19 በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት፥ ቸርነትህ እንደ ምን በዛች!
20 በፊትህ መጋረጃ ከሰው ክርክር ትጋርዳቸዋለህ፥ በድንኳንህም ከአንደበት ክርክር ትሸፍናቸዋለህ።
21 በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ እግዚአብሔር ይመስገን።
22 እኔስ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፥ በድንጋጤ አልሁ፤ አንተ ግን ወደ አንተ በጮኽሁ ጊዜ የልመናዬን ቃል ሰማኸኝ።
23 ሁላችሁ ቅዱሳኑ፥ እግዚአብሔርን ውደዱት፤ እግዚአብሔር እውነተኞችን ይፈልጋል፥ ትዕቢተኞችንም ፈጽሞ ይበቀላቸዋል።
24 በእግዚአብሔር የምታምኑ ሁላችሁ፥ በርቱ ልባችሁም ይጥና።

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 03 Mar 2026, 02:43

03/03/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ንዝበደሉና ኣሕዋትና በደሎም ክንሓድግ ግዱዳት ኢና፡ እንተዘየሎ ‘ከምቲ ዝበደሉና ዝሓደግናሎም በደልና ሕደገልና’ ኢልና ስለ እንጽሊ ‘ሰማያዊ ኣቦና ሓጢኣትና ሕደገልና’ ኢልና ክንልምን የብልናን።
ማቴ 18፡ 21-35
21 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።
22 ኢየሱስ እንዲህ አለው። እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።
23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች።
24 መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።
25 የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።
26 ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና። ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው።
27 የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥ ዕዳውንም ተወለት።
28 ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና። ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው።
29 ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ። ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው።
30 እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው።
31 ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ።
32 ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ። አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤
33 እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው።
34 ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው።
35 ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።

ቀስተ ጸሎት፡ - መሓርቲ ምሕረት ክረኽቡ እዮምሞ ብፁዓን እዮም።
መዝ 119፡ 105 - 112
105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
106 የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።
107 እጅግ ተቸገርሁ፤ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
108 አቤቱ፥ ከአፌ የሚወጣውን ቃል ውደድ፥ ፍርድህንም አስተምረኝ።
109 ነፍሴ ሁልጊዜ በእጅህ ውስጥ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
110 ኃጢአተኞች ወጥመድን ዘረጉብኝ፤ ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም።
111 የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘላለም ወረስሁ።
112 ለዘላለም ለፍጻሜውም ትእዛዝህን አደርግ ዘንድ ልቤን አዘነበልሁ። ሳምኬት

Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 04 Mar 2026, 04:16

04/03/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - እግዚኣብሔርን ንሓያል ፈረስ ኣይብህጎን፡ ብንፉዓት ሰራዊት ኣይሕጎስን፡ በቶም ዚፈርኍኦን ብምሕረቱ ተስፋ ዝገብሩን ግን ይሕጎስ።
ዘፍ 29፡ 1-12
1 ያዕቆብም ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሰዎች አገር ሄደ።
2 ፤ በሜዳውም እነሆ ጕድጓድን አየ፥ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፤ ከዚያ ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ።
3 ፤ መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፤ ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደ ገና ይገጥሙት ነበር።
4 ፤ ያዕቆብም። ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንት የወዴት ናችሁ? አላቸው። እነርሱም። እኛ የካራን ነን አሉት።
5 ፤ የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን? አላቸው። እነርሱም። እናውቀዋለን አሉት።
6 ፤ እርሱ። ደኅና ነውን? አላቸው። እነርሱም። አዎን ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት።
7 ፤ እርሱም። ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚከማቹበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው አላቸው።
8 ፤ እነርሱም አሉ። መንጎች ሁሉ እስኪከማቹና ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም፤ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።
9 ፤ እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረሰች፤ እርስዋ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና።
10 ፤ ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የእጎቱን የላባን በጎች ባየ ጊዜ፥ ቀረበ ከጕድጓዱም አፍ ድንጋዩን ገለበጠ፥ የአጎቱን የላባን በጎችንም አጠጣ።
11 ፤ ያዕቆብም ራሔልን ሳማት፥ ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ።
12 ፤ ያዕቆብም የአባትዋ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት፤ እርስዋም ሮጣ ሄዳ ለአባትዋ ይህን ነገር ነገረችው።

ቀስተ ጸሎት፡ - ነቶም ልቦም ዝተሰብረ ይፍውሶም፡ ነቝሳሎም ይዝንን። (መዝ 147፡3)
መዝ 147፡ 1 - ፍጻመ
1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና። ለአምላካችን ምስጋና ያማረ ነው።
2 እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።
3 ልባቸውን የቈሰሉትን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል።
4 የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።
5 ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም።
6 እግዚአብሔር የዋሃንን ያነሣል፥ ኃጢአተኞችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል።
7 ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤
8 ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፤ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል፤ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም።
9 ለሚጠሩት ለቍራዎች ጫጩቶች ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል።
10 የፈረስን ኃይል አይወድድም፥ በሰውም ጭን አይደሰትም።
11 እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑት ይደሰታል።
12 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥
13 ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና።
14 በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።
15 ነገሩን ወደ ምድር ይሰድዳል፥ ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።
16 አመዳዩን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፤
17 በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤ በበረዶውስ ፊት ማን ይቆማል?
18 ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
19 ቃሉን ለያዕቆብ፥ ሥርዓቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይናገራል።
20 ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። ሃሌ ሉያ።


Meleket
Member
Posts: 4942
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓቢይ ጾም + ጾመ 40 + ከአንዳንድ የቅዱስ መጸሐፍ መንፈሳዊ ሃሳቦች ጋር + 40 ጾም

Post by Meleket » 05 Mar 2026, 02:10

05/03/2026

መስተንተኒ ሓሳብ፡ - ብመንፈስ ቅዱስ እንተተመራሕና ትምኒት ስጋና ማለት ሰብኣዊ ባህርይና ምስ ፍትወቱን ትምኒቱን ገዲፍና ብፍቕሪን ቅድስናን ንንበር።
ገላ 5፡ 13 -26
13 ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ።
14 ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው።
15 ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።
16 ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።
17 ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።
18 በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።
19 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥
20 መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥
21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
23 እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።
24 የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።
25 በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።
26 እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።

ቀስተ ጸሎት፡ - ብመንፈስ ንበሩ፡ ትምኒት ስጋ ከኣ ኣይክትፍጽሙን ኡኹም። (ገላ 5፡16)
መዝ 17፡ 1- 5
1 አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጥ።
2 ፍርዴ ከፊትህ ይውጣ፥ ዓይኖችህም በቅንነት ይዩ።
3 ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
4 የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
5 እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።


Post Reply