Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7160
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ቱለማ ቦረና ነዉ? ቱለማ ቦረና ከልሆነ ጎሳዉ ምንድነዉ?

Post by Naga Tuma » 09 Feb 2026, 17:29

ይህን ጥያቄ ለመጀመርያ ግዜ እራሴን የጠየኩኝ ከጥቂት ቀናት በፊት ነዉ።

ያስጠየቀኝም የፈረዖዎች ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክን ማጥናት ነዉ። ይህ ማለት ከስደት በፊት የነበረዉ የጥንት ኢትዮጵያ ታሪክን ማጥናት ማለት ነዉ።

በእኔ አስተሳሰብ ለዚህ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት በር የከፈተዉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ነዉ።

የጥናት በሩን የከፈተዉ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ድሬ ሊበን፣ ቦረና፣ ሄዶ ጻፍኩት ባለዉ ለካ ኣንተ ነህ! ሶስት ቃሎቹ ነዉ።

ደጋግሜ እዚህ መድረክ ላይ እንደጻፍኩኝ እኔ እንደገባኝ ከሆነ ሎሬቱ ለካ ኣንተ ነህ! ያለዉ እስራኤላዊ ፕሮፌት ሙሴ ተብሎ ይታወቅ የነበረዉ የጥንት ኢትዮጵያ ታላቅ ፈረዖ የነበረዉ አክናተንን ነዉ።

ለዚህ ፍንጭ ተነባቢ የአስር ምስጥር ያለዉ ነዉ።

በእኔ ግምት ተነባቢ የአስር ምስጥር ያለዉ የፕሮፌት ሙሴን አስርቱ ትዕዛዛት ማለቱ ነዉ። አስርቱ ትዕዛዛት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታቦት የሚሸከመዉ እና የሚጠብቀዉ ነዉ።

ለካ ኣንተ ነህ! ማለቱ እስራኤላዊ ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ የጥንት ኢትዮጵያ ታላቅ ፈረዖ አክናተን ነዉ ማለቱ ነዉ።

እኔ የሎሬቱን ጥናት ሳላዉቅ በፊት እስራኤላዊ ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ ከስደት በፊት ታላቅ ፈረዖ አክናተን የነበረ መሆኑን ከሃያ ዓመታት ገደማ በፊት ደርሼበታለሁ።

በእኔ አስተሳሰብ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ከሃምሳ ዓመታት በፊት ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ ያለዉ እና እኔ ከሃያ ዓመታት ገደማ በፊት ዋቀ ቶክቸ ኤንደ ሞኖቴይዝም ያልኩኝ ስለ ኣንድ ርዕስ ነዉ።

ከስደት በፊት ስለነበረዉ የተከፈተዉ የፈረዖዎች ዘመን የኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ እስከኣሁን የደረሰባቸዉ ማስረጃ የታላቁ ፈረዖ አክናተን ታሪክ ዋነኛዉ ነዉ።

በእኔ አስተሳሰብ የማያሻማ የሚመስል ሌላ ማስረጃ የሌላ ታላቅ ፈረዖ ምነስ ታሪክ ነዉ።

ምክንያቱም ኢትዮጵያ ዉስጥ ምናስ የተለመደ ስም ብቻ ሳይሆን ምናሲ የሚባል ጎሳ መኖሩን ኣዉቃለሁ።

ምነስ የሚባል ታላቅ ፈረዖ ታሪክ ዉስጥ መኖሩን የደረስኩበት ታህሳስ ሚካኤል ቀን፣ 2018፣ ዓም ነዉ።

ከብዙ ዓመታት በፊት የቀነኒሳ በቀለን ፎቶ እና የሌላ ታላቅ ፈረዖ ቱታንከአሙን ምስል ጎን ለጎን ኣድርጌ ወንድማማቾች ናቸዉ ቢባል ስህተት ኣይመስልም ኣስብሎኝ ነበር።

ስለዚህ የፈረዖ ምነስን ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ በቅርቡ ኣንብቤ ሌላ ፕቶለሚ የተባለ ታላቅ ፈረዖ ስምን ማስታወስ ቱለማ ቦረና ነዉ ወይ ኣስብሎኛል።

ቱለማ ቦረና ከሆነ ምናልባት በግራኝ ዘመን ቱለማ የደረሰ የቦረና ሰዉ ሐረግ ሊሆን ይችላል።

ይህን እኔ ማረጋገጥ ኣልችልም።

ስለዚህ ስለ ቱለማ ታሪክ ያጠናችሁ ቱለማ ቦረና መሆኑን ኣረጋግጣችሁ ታዉቃላችሁ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 7160
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ቱለማ ቦረና ነዉ? ቱለማ ቦረና ከልሆነ ጎሳዉ ምንድነዉ?

Post by Naga Tuma » 11 Feb 2026, 15:17

ከሳምንታት በፊት ያየሁትን ሕልም እንደ ቀልድ ጽፌ ከዛ በኋላ ከቀልድ በላይ የሚመስል ሆኗል።

ቀልድ እና ቁምነገር፥ ሕልም እና ቅዠት

ቱለማ ዉስጥ የታላቅ ፈረዖ ስም ወይም ሐረግ ከተገኘ ይህ ሕልም የተፈታ ሆኗል።

የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ ፊደል ሠራዊት መሪ የነበረዉ፣ የኒልሰን ማንዴላ ኣሰልጣኝ የነበረዉ፣ እና ዮሓንስ ለታ እንደጻፈዉ የኦነግን መመስረት የመራዉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጄነራል ታደሰ ብሩ የቦረና ጎሳ መሆን ወይም ኣለመሆን የምያዉቅ የኢትዮጵያ ምሑር ኣለ?

ካልተሳሳትኩ የቱለማ ሰዉ ነዉ።

Post Reply