Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Meleket
Member
Posts: 4931
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: እውቆ የተኛን ሲቀሰቅሱት አይነቃም እንዲሉ የመለከት ኤርትራ ከጣልያን በፊት አልተፈጠረችም! የትግራይ አካል ነበረች! ቢባል አይሰማም!

Post by Meleket » 09 Feb 2026, 08:18

ወዳጃችን አዅሱመጫላ ታሪኩ በቅጡ ስላልገባህ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር በጥቂቱም ቢሆን እናስረዳሃ።

የአሁኗ ኢትዮጵያና የአሁኗ ኤርትራ የጣልያንና የምኒልክ ስሪት ናቸው። [4 ሚልዬን ነጥቦች + 120 ሚልዬን ነጥቦች]

እርግጥ ነው የያኔዋ ትግራይ ባንድወቅት ከደጋማው የባሕረነጋሲ (ኤርትራ) ክፍል ጋር የታሪክ ግንኙነት ነበራት፤ ነገር ግን የያኔዋ ትግራይ ኣብዛኛውን የአሁኗን የኤርትራ ክፍል በጭራሽ አታውቃቸውም ነበር። ጋሽን ባርካን ሳሕልን ሰንሒትን ደንከልን ምጽዋዕን ዓሰብን ቀይባሕርን ወዘተን በፍጹም አታውቃቸውም ነበር። አልፎ አልፎ ጡንቻዬ ፈርጥሟል ብላ ታስብ በነበረበት ወቅት ከደጋማው የአሁኗ ኤርትራ ክፍል በመነሳት ወደ ቆላማው ክፍል ለመዝመት ቋምጣ፡ በተወሰነ መልኩ፡ በኩናማና በናራ ህዝብ ላይ “ጄኖሳይድ” ብትፈጽምም እንኳ የመስፋፋት ምኞቷ ሳይሳካላት ቀርቷል። [4 ሚልዬን ነጥቦች]

የያኔዋ ትግራይ ለጥቂት ዓመታት የአሁኗን ኤርትራ አንዳንድ ደጋማ ክፍሎች ለመቆጣጠርና ለማስገበር ሞክራ ነበር። ነገር ግን እምቢ “አንገብርም” ባሉ የምድሪ ባሕሪ አርበኞች በየግዜው አይቀጡ ቅጣት እዬተቀጣች ወደ መጣችበት እንድትመለስ ተደርጓል። [4 ሚልዬን ነጥቦች]

የአሁኗ ኤርትራ የትግራይ አካል ነበረች ዬሚለው አባባል ፉርሽ ዬሚሆነው፡ ትግራይ ምጽዋን ሆነ ዓሰብን ቓሮራን ሆነ ናቕፋን፡ አቖርደትን ሆነ ባረንቱን፡ ዳህላክን ሆነ ሓንሽን ቀይባሕርን ጭምር ለአንዲት ሰከንድ እንኳን አስተዳድራ ባለማወቋም ነው። [4 ሚልየን ነጥቦች]

ታሪካዊው ሓቅ ይህ ከሆነ ዘንዳ፡ አውቆ ዬተኛው ማንኛችን ሆነ?

Axumezana wrote:
09 Feb 2026, 07:11
እውቆ የተኛን ሲቀሰቅሱት አይነቃም እንዲሉ የመለከት ኤርትራ ከጣልያን በፊት አልተፈጠረችም! የትግራይ አካል ነበረች! ቢባል አይሰማም!
viewtopic.php?f=2&t=306818&sid=a94e6a62 ... 132df731f8

Axumezana
Senior Member
Posts: 18974
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: እውቆ የተኛን ሲቀሰቅሱት አይነቃም እንዲሉ የመለከት ኤርትራ ከጣልያን በፊት አልተፈጠረችም! የትግራይ አካል ነበረች! ቢባል አይሰማም!

Post by Axumezana » 09 Feb 2026, 12:25

የመለከት ዘፈን ዲማርኬሽን ዳይ ይቀፅል
የኢሱ መፈክር በኢትዮጵያ ልሁን አባ ጠቅልል
Axumezana ለባህር በር ካርታ ቢስል
ሁለቱም ፈረጠጡ ዘንዶው ብቅ ሲል


መፅሐፍ ትውዳለህና፥ እየመረረህም ቢሆን ይችን ጎንጨት በል!

viewtopic.php?f=2&t=375021


[/quote]
[/quote]
[/quote]
[/quote]
Last edited by Axumezana on 09 Feb 2026, 12:30, edited 1 time in total.

Right
Member
Posts: 4640
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: እውቆ የተኛን ሲቀሰቅሱት አይነቃም እንዲሉ የመለከት ኤርትራ ከጣልያን በፊት አልተፈጠረችም! የትግራይ አካል ነበረች! ቢባል አይሰማም!

Post by Right » 09 Feb 2026, 12:30

Ax,
What were you thinking when you fought for Eritrea’s independence?
Now, you want to fight them back to unite with Tigray.

What is wrong with you Tigrian elites? Clueless. No principles and craving for endless war.

Meleket
Member
Posts: 4931
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: እውቆ የተኛን ሲቀሰቅሱት አይነቃም እንዲሉ የመለከት ኤርትራ ከጣልያን በፊት አልተፈጠረችም! የትግራይ አካል ነበረች! ቢባል አይሰማም!

Post by Meleket » 10 Feb 2026, 01:59

ወዳጃችን አዅሱመጫላ፡ ሥጋ ቁጠር ብትባል ጣፊያን አንድ አልክ አይደል? :mrgreen:

የሰዉየውን ጥሑፍ ታነበብነው ቆይተናል። የታችን ልጅ ሸቃ አሉላ፡ ጦረኛ እንደነበሩ ግልጥ ነው። አመሻሹ ላይ ሓዲሽ አበባ ሂደው አጤ ምንሊክን ድንጋይ ተሸክመው ይቅርታ ጠይቀው እንደነበረም እናውቃለን።
:mrgreen:
Axumezana wrote:
09 Feb 2026, 12:25
የመለከት ዘፈን ዲማርኬሽን ዳይ ይቀፅል
....
መፅሐፍ ትውዳለህና፥ እየመረረህም ቢሆን ይችን ጎንጨት በል!

viewtopic.php?f=2&t=375021
....
viewtopic.php?f=2&t=308857
Meleket wrote:
09 Nov 2022, 10:35
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ 146ቱ የጋራ ፈርጦች! - የ146ቱ ካምፖች ወግ!

ጐበዝ እነዚህ 146 የጋራ ፈርጦቻችን ከነ 'ኮኦርዲኔታቸው' በማያሻማ መልኩ “ይግባኝ በማይባልበት” ፍርድ ተወስነው፡ ቁልጭ ብለው ትግባሬን እየጠበቁ የተቀመጡ ናቸው።

https://legal.un.org/riaa/cases/vol_XXVI/771-799.pdf

ታድያ ሃገራችን ኤርትራና ጐረቤቷ ኢትዮጵያ በሰላም ይኖሩ ዘንድ፡ እንዲህ ቢደረግ ምን ይመስላችኋል?

1.) በ146ቱ ነጥቦች፡ በያንዳንዷ ስፍራ የጋራ ወታደራዊ ካምፕ በመገንባት የደንበር ጸጥታ አስከባሪ ሃይል ማስፈር።

2.) በ146ቱ ካምፖች የሚኖሩት የሁለቱ ሃገራት የሰራዊት ብዛት 80 ከኢትዮጵያ (ሁሉን ኢትዮጵያዊ ብሄር ብሄረሰቦች የወከለ እንዲሆን ማለትም ኣልተወከልኩም የሚል ኢትዮጵያዊ ብሄር እንዳይኖር ማለት ነው።) ኤርትራም በበኩሏ ከ80 ያልበለጡ የሰራዊቷ ኣባሎችን በነፍስወከፍ 146ቱ ካምፖች ውስጥ እንድታስቀምጥ ማድረግ።

3.) ይህም ማለት 146*80 = እያንዳንዷ ሃገር ቢያንስ ቢያንስ 11,680 በወታደራዊ ዲሲፕሊን የተመሰከረላቸውን የሰራዊት አባሎቿን ለድንበር ጥበቃ እንድታሰማራ ማድረግ። ይህ የሁለቱ ሃገራት መንግስታት የሰራዊት ክፍል፡ ፈጣን በሆነ ዘመናዊ የመገናኛ መሳርያዎች የታጠቀ ማድረግ። [ስለ ወጪው አትጨነቁ፡ የሁለቱ ሃገራት ህዝብ ሊሸፍነው ይችላል፤ የሁለቱ ሃገራት ህዝብ በረባ ባልረባው ከመናቆር፡ ገንዘብ አዋጥቶ ሰላሙን ማስጠበቅ ይቀለዋል!]

4.) የሁለቱም ሃገሮች የአየር ሃይል፡ ሃገሮቹ ዬተስማሙባቸውን ያህል የአሰሳና ዳሰሳ ሂሊኮፕተሮችና ድሮኖች ለዚሁ ድንበር ጸጥታ መመደብ። [በሂሊኮፕተርና በድሮን ከመጨፋጨፍ ይሄ ሳይሻል ኣይቀርም ትላላችሁን?]

5.) በዚህ መሰረት፡ በድንበር አካባቢ ምናልባት ሊፈጥር የሚችልን ግጭት በግዜ ማጤንና ፈጣን ፈውስ በመሻት እልባት ላይ ማድረስ።

በዚህ መልኩ “ፊዚካል ዲማርኬሽኑን” ብንጀምረው የሁለቱ አጎራባች ሃገሮች ህዝቦች ዘለቄታዊ ሰላምና እፎይታን ለማግኘትና ለማጣጣም አይችሉም ትላላችሁን? እስከ መቼ ድረስ እርስ በእርስ ማናቆር ጐበዝ!

ለዛሬ 146 የጋራ ፈርጦቻችንን እዚህ ተመልከቷቸው!ከገጽ 786-794 ወይም ከ ገጽ 17-25 ቁልጭ ብለው አሉላችሁ።



ጐበዝ "ፊዚካል ዲማርኼሽኑ" በዚህ ሃሳብ አኳያ ቢተገበር ምን ይመስላችኋል? እስቲ የሚጐድለውን አጉድላችሁ፡ የሚጨመረውን ጨምራችሁ ሃሳባችሁን አክሉበትና ወደ ትግባሬ እናምራ። የየሃገሮቻችን ቦተሊከኞቻችንን እንዲህ አድርገን 'ጭራውን መያዝ' የፈሩትን ነገር በማደፋፈር እናግዛቸው እንጂ ጐበዝ! አይመስላችሁም። "ፊዚካል ዲማርኼሽን ይቻላል!"

ተጻፈ፡ በኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
:mrgreen:
ሲጠቃለል አዉቆ የተኛዉ ማንኛችን ሆነ?

Post Reply