Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4935
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

በቦሌም ሆነ በባሌ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 06 Feb 2026, 04:46

በቦሌም ሆነ በባሌ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

በባቢሌም ሆነ በበደሌ፡
በገናሌም ሆነ በሸበሌ፡
በሰገሌም ሆነ በመቀሌ፡
በሞያሌም ሆነ በነገሌ፡
በቦሌም ሆነ በባሌ፡
የኤርትራን ቀይባሕር የተመኙ፡
ምን ያህል ተሞኙ!


በ2026 የፈንቅል ዋዜማ፡ ተጻፈ በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Axumezana
Senior Member
Posts: 18984
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: በቦሌም ሆነ በባሌ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Axumezana » 06 Feb 2026, 09:04

ቁሞ ቀር መለከት
የተሰጥህን የቤት ስራ ተመልከት

[/quote]
[/quote]
[

Meleket
Member
Posts: 4935
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: በቦሌም ሆነ በባሌ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 06 Feb 2026, 10:32

“ቁሞ ቀር” አለን ቁሞቀሩ፡
“ወንጌላዊነቱ” አቤት ‘ማማሩ!’

የብልጽግና ወንጌል ‘አማኙ’፡
አዅሱመጫላ ሞኛ ሞኙ።
የቤቱን ስራ ሳይሰራ፡
ባሕር እያለ አቅራራ።

ለብልጥግኖች ጣዖት፡ ሆኖ ባሕሩ፡
ደም ሊያፈሱ ሊገብሩ፡
ቀይ ባሕርን ሊያጠቋቁሩ፡
እነ አዅሱመጫላ ፎከሩ፡
በብልጽግናው መንፈስ እያጓሩ፡
እንደልማዳቸው ሊቀበሩ፡
በህልማቸው ተንጠራሩ።

Axumezana wrote:
06 Feb 2026, 09:04
ቁሞ ቀር መለከት
የተሰጥህን የቤት ስራ ተመልከት
[/quote]
[
[/quote]

Axumezana
Senior Member
Posts: 18984
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: በቦሌም ሆነ በባሌ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Axumezana » 06 Feb 2026, 13:43

ዲማርኬሽን ስትናፍቅ
የAbiy-Isaias allance አደረግነው ድቅቅ!

Meleket
Member
Posts: 4935
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: በቦሌም ሆነ በባሌ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 07 Feb 2026, 04:16

የሰዎች alliance እንክትክት ቢልም፡
የህዝቦች alliance ይኖራል ዘላለም።

የህዝቦቻችን ብሂል፡ “የሰው ወርቅ አያደምቅ”፡
መሆኑን አትርሳ፡ በደንብ አርገህ እወቅ።

ህዝቦች ዋሾ አይደሉም፡ እዉነትን ያውቃሉ፡
ዲማርኬሽኑንም ይተገብራሉ።

ያኔ ነው ሚሰፍነው ሰላም በቀጠናው፡

እስከዚያው ድረስ ግን ይህን እውነት አጥናው!

https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308857&

Axumezana wrote:
06 Feb 2026, 13:43
ዲማርኬሽን ስትናፍቅ
የAbiy-Isaias allance አደረግነው ድቅቅ!

Post Reply