Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7160
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ቀልድ እና ቁምነገር፥ ሕልም እና ቅዠት (ቁጥር 2)

Post by Naga Tuma » 05 Feb 2026, 16:51

ዛሬ ሊነጋጋ አከባቢ ሌላ የማይረሳ ሕልም ኣየሁ።

የምኖርበት ከተማ መኪና እየነዳሁ፣ የአጎቴ ልጅ ከኋላ ቁጭ ብላ እጅግ የበራች ሙሉ ጨረቃ ኣየሁ። ከዛም በጨረቃዋ ቀኝ እና ግራ በኩል በእኩል ርቀቶች ደብዘዝ ያሉ ሌሎች ጨረቃዎችን በኣንድ ቀጥታ መስመር ላይ ኣየሁዋቸዉ።

የጨረቃዋ ነጸብራቅ ናቸዉ ብዬ ገርሞኝ እየሳኩኝ የአጎቴን ልጅ ስም ጠርቼ ስንት ጨረቃዎች ይታዩሻል ብዬ ጠየኩዋት።

ሁለት፣ ሶስት፣ እያለች እየቆጠረች ብዙ ኣለች።

እየተገረምኩ መስታወት ነጸብራቅን እንፍኒቲ ኣድርጎ እንደምያሳየዉ የሚታዩት ደብዛዛ ጨረቃዎች ቁጥር እንፍኒቲ እንደሆነ ገመትኩኝ።

ከዛም እሩቅ የነበረች እጅግ የበራችዉ ጨረቃ ወደ ከተማዉ መሃል እጅግ ቀርባ የምድርን ካርታ በጀርባዋ የምታሳይ ሆነች።

ከጨረቃዋ ጀርባ ያየሁት የምድር ካርታ ከኣሁን በፊት ያየሁኝ ሻማዎች በርተዉ የሚታዩባት ነዉ።

ከነቃሁ በኋላ ስለ ኣየሁት ሕልም ሳሰላስል የሰዉ ልጅ ኣዕምሮ በእንቅልፍ ዉስጥ ትዉስታ ወይም ሜሞሪን ኣንድ ላይ ኣምጥቶ ማሰላሰል መቻሉን ነዉ።

ስለዚህ ቅዠት ነዉ ማለት ይቻል ይሆናል።

ኣሁን መልስ ያጣሁለት ጥያቄ ቅዠቱን የሚቀሰቅስ ወይም ትሪገር የምያደርግ ምንድነዉ የሚል ነዉ።

ትላንትና ስለኣሰላሰልኩኝ ኣንድ ነገር ኣስታወስኩኝ።

ለታሪክ ስለ ራጁ እና ራጂ ኣጭር መልስ ጽፌ ነበር።

ከኣሁን በፊት ኣንድ የህንድ ሰዉ ስራ ቦታ ተዋዉቀን ስለ ሃይማኖታቸዉ ስያወራ ሌሎች ዓለማት ኣሉ ብሎ ልያብራራልኝ ሞክሮ ነበር።

ስለ ኣልተጨበጠ ነገር የምያወራ ነዉ ብዬ ኣለፍኩት።

በዚህ ምክንያት ትላንትና ስለ ሕንዶች ወሬ ሰምቼ ራጁ እና ራጂ ብዬ ፅፌ ዛሬ ሊነጋጋ አከባቢ ከዚህ በፊት ፍጹም ኣስቤዉ የማላዉቀዉ እጅግ ብዙ ጨረቃዎችን በቅዠት ማየት ከኣሁን በፊት ስለ ሰማሁት የሕንዶች ብዙ ዓለማት ኣሉ ባህል ትዉስታ መሰለኝ።

ይህ ከሆነ የሰዉ አካል እንቅልፍ ዉስጥ ቢሆንም የሰዉ ኣዕምሮ እራሱን ችሎ ትዉስታዎችን ወይም ሜሞሪዎችን ሰብስቦ ማንጸባረቅ ይችላል ማለት ይሆናል።

እንደዚህ የምያስደርግ ሌላ ምንም ነገር የሌለ ከሆነ ማለት ነዉ።