ስለ መለኮታዊ ነገር ጥያቄ ስጀምር ኣሁን ያሉኝን ያህል ጥያቄዎች ኣልነበሩኝም።
ጥያቄዎቹ በየግዜዉ እየበረከቱ የጀመርኩትን ጥያቄ በእኔ አስተሳሰብ እጅግ ጠንካራ ያደርጋሉ።
ኢትዮጵያን የነካ ማለትን እስከዚህ ዘመን ድረስ በጥልቀት ኣስቤበት ኣላዉቅም ነበር።
ተገለጡልኝ የምላቸዉን የበለጠ ሳሰላስል ኣዳዲስ ጥያቄዎች ያስጠይቀኛል።
መለኮታዊ አሰራር ኣለመኖሩ የተረጋገጠ ነዉ እና ይህ ዕዉቀት ከዐለም ሕዝብ ተደብቆ የሰዉ ልጅ ዐለምን ኣሰልፎ ይግዛ የምትሉ ይህ የኣንድ ሰዉ ቅዠት ነዉ ብላችሁ ልታልፉት ትችላላችሁ። እንደለመዳችሁት።
የእኔ ጥረት መለኮታዊ አሰራር ለመኖሩ ምልክቶች ኣሉ ማለት ነዉ።
በቅርቡ ያስጠየቀኝ ጥያቄ የሚከተለዉ ነዉ።
መለኮት በቀዳማዊ ነብይ እና ኣዳኝ በተባሉ መካከል ለቀዳማዊ ነብዩ ብያደላ ምን ለማስተማር ነዉ?
በተጨማሪ ትላንትና ጥር 23፣ 2018፣ ዓም ኤሞስ 9፥7ን ማስታወስ የሚከተለዉን ኣስጠየቀኝ።
እግዝኣብሔር እየሱስ እራሱን ኢትዮጵያን የነካ የምያስብል ይሆን?
ከግብጥ ምድር ኣላወጣሁዋችሁም ወይ ማለት ከጥንት ኢትዮጵያ ምድር ኣወጠሁዋችሁም ማለት ነዉ።
ለምን ነበረ እንደዚህ ኣለ የተባለዉ?
ኢትዮጵያ የተረገመች ምድር ነበረች?
በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ የተቀደሰች ምድር ናት ማለት የጀመራችሁ እርስ በእርስ የሚጋጭ አስተሳሰብ ኣልሆነባችሁም?