Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11566
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ህወሓት በአድዋ እንትጮ አካበቢ በህዝቡ ላይ ድሮን በማውረድ ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድርገውታል፡፡" ብልጽግና | አልገባኝም! ብልጽግና ነው ወይስ ህወሓት ህዝቡን ከሰማይ የደበደበው?

Post by sarcasm » 01 Feb 2026, 10:54

"የ1980ዎቹ ሃውዜን ጥፋት በድጋሚ !ታሪክ እራሱን ሲደግም!

ወትሮውንም የራሱን ዜጋ ለፖለቲካ ቁማር በመጠቀም የምናውቀው ህወሓት ከሴረኛው ሻዕቢያ ጋር በመተባበር በአድዋ እንትጮ አካበቢ በህዝቡ ላይ ድሮን በማውረድ ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድርገውታል፡፡ ህወሓት ሀውዜን ላይ ንጹሃንን በመጨፍጨፍ ዘመናዊ ካሜራን በመጠቀም የያኔውን የደርግ መንግስት በዓለም አቀፍ ተቋማት ለማስወገዝና የትግራይን ህዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ የተጠቀመበትን ስልት በዚህ ጊዜም በእንትጮ ነው የደገመው፡፡ ህወሓት ከነ አስተሳሰቡ ያረጀና ዛሬም 1980ዎቹ ላይ ቆሞ የቀረ የማፍያ ቡድን መሆኑን በተግባር አስመስክሯል ።" የብልጽግና ቃል አቀባይ

Please wait, video is loading...