The National Election Board of Ethiopia has released a new polling station jurisdiction directory that places most of the long disputed areas, including Alamata, Setit Humera, Kafta Humera, Wolkait, Tsegede, Mai Kadra, Korem, Alamata, etc. under the Tigray regional administration rather than Amhara.
Most of these territories are currently under Amhara administration, except Alamata, Tselemt, and Korem, which Tigray forces took control of earlier this week.
These territories have been contested for decades, with both regions claiming historical and constitutional rights over them.
By assigning them to Tigray for electoral purposes, the Board has prompted observers to question whether this reflects the Abiy government’s emerging stance on the still unresolved Tigray–Amhara territorial dispute.
ከወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
በትናንትናዉ ዕለት ማለትም ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የምርጫ ክልል እና ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር መረጃ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህ መሠረት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን "ምዕራብ ትግራይ" በሚል ምድብ ሥር ተጠቅሰዉ ተመልክተናል።
እንዲሁም ምርጫ ቦርዱ ለወደፊቱ በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በመዳሰስ እና በመገምገም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተጨማሪ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ዳሩ ግን የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነትና ወሰን ጥያቄ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለፌደሬሽን ምክር ቤት፣ ለትግራይ ክልል ምክር ቤት እና አስተዳደር እንዲሁም ለአማራ ክልል መንግሥት መቅረቡ ይታወቃል።
በመሆኑም ሕወሓት በድርጅቱ ውሳኔ አካባቢውን ከ1984 ዓ.ም. ሕገ መንግሥቱ ከመጽደቁ በፊት በጉልበት እና ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ፍላጎት እና ፈቃድ ውጪ ወደ ትግራይ ክልል ማካለሉ ይታወሳል። ስለሆነም አካባቢያችን ለሦስት ዐሥር ዓመታት አማራዊ ማንነቱ ተደፍጥጦ እና የትግራይ ማንነት ተጭኖበት መቆየቱ ይታወቃል።
ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በአገራችን የሰሜኑ ጦርነት ሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት ማለትም ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በተወሰደዉ እርምጃ ከሕወሓት አገዛዝ ነጻ በመውጣት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዞን ደረጃ ተደራጅቶ በ4 የገጠር ወረዳዎች፣ 5 ከተማ መስተዳድሮች እና 93 ቀበሌዎች ይዞ ራሱን በራሱ በማስተዳደር ላይ ይገኛል። በተጨማሪም ከነጻነት ማግስት በአቶ አደም ፈራሕ የኢፌዴሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ‐ጉባኤ የተመራ ልዑክ ቡድን ስለ አካባቢዎቹ የሕዝብ ፍላጎት እና ሁኔታ ዳሰሳዊ ጥናት በማድረግ ሪፖርት ማድረጋቸውም አይዘነጋም።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብ
አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም!
በሚል መሪ ቃል በተደጋጋሚ ድምጹን በተለያየ መንገድ ማሰማቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ስለሆነም ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚደረገዉ አገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ የበኩላችን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን እያረጋገጥን፤ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ላለፉት 5 አመታት በአማራ ክልል አስተዳደር ሥር ሆኖ መቆየቱ እየታወቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል የምዕራብ ትግራይ ምርጫ ክልል ሥር አድርጎ መመደቡን ተገቢነት ስለሌለው፤ ቦርዱ ይህንን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ዞኑ በአማራ ክልል ሥር ሆኖ ምርጫ እንዲያካሄድ ስንል በአክብሮት እየጠቅን ከህዝባችን ፍላጎት ውጪ የሚደረግ አካሂድ የማንቀበል መሆኑ ከወዲሁ እንገልፃለን።
የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ
ጥር 23/2018 ዓ.ም.
ሁመራ
TIGRAY ― In a letter addressed to the Chairperson of the African Union Commission, the TPLF chair welcomed the call for restraint and urged a commitment to a genuine, inclusive, and result oriented dialogue with the federal government to resolve outstanding issues in full adherence to the Pretoria Agreement.
TIGRAY ― Renewed fighting broke out on Wednesday between Tigray forces and the federal army, after TPLF forces reportedly took control of the towns of Alamata and Korem.
Residents have reportedly fled the area in large numbers, seeking refuge in the neighboring towns of Kobo and Woldiya.
BBC Amharic reports indicate that residents fled both out of fear for their safety and to avoid forced military conscription, particularly among young people.
Eyewitness accounts suggest that the takeover involved minimal direct fighting between the two sides, apart from sporadic warning shots fired into the air.
However, once TPLF forces seized government offices and raised their flag, federal troops reportedly retreated overnight to nearby Kobo and Chobe.
The withdrawal is believed to have been a tactical decision to preserve heavy weaponry from felling on TPLF hands and regrouping for a possible counteroffensive.
Alamata and Korem, are now fully under the control of Tigray forces.
The fighting marks the first major breakdown in security since the cessation of hostilities agreement signed in Pretoria three years ago. Critics accuse the Abiy Ahmed administration of deliberately delaying full implementation of the agreement, while actively working to weaken the TPLF from within through establishing proxy forces and alternative political party.
At the same time, prolonged restrictions on budgets, fuel supplies, basic commodities, flights, banking access, etc ... have deepened economic pressure in Tigray.
Local sources describe the current escalation as the result of accumulated frustration and stalled peace, rather than a calculated choice to return to war.