Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 41921
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢምክንያታዊ ተቃዋሚዎች (ፖለቲካዊም ወታደራዊም) የሚከስሙበት እስትራተጂና ሂደት

Post by Horus » 12 Jan 2026, 13:38

እኔ ሆረስ ቃላት በመፍለጥ ግዜያችሁን አላባክንም ። መልሶቹ አጫጭር ናቸው ። እነሆ ።

ወታደራዊ ተቃዋሚ፡
ትህነግ
ፋኖ
ሸኔ

ፖለቲካዊ ተቃዋሚ፡
የትግሬ ፣ አማራና ኦሮሞ ጎሳ ፖለቲክኛ

እነዚህ ተቃዋሚዎች የሚከስሙት በምንድን ነው?
(1) በኃይል
(2) በግዜ
(3) በስልት
(4) በእድገት

ኃይል ማለት ተቃዋሚውን በዉጊያ መደምሰስ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚው ያሰበወን ያለመውን እንዳይፈጽም መግታት ማገድ መገደብ መከልከል ማለት ነው

ግዜ ያመጣል ግዜ ይወሳዳል፤ ግዜ ይወልዳል ግዜ ይገድላል። እነዚህ ተቃዋሚዎች ያሰቡትን ሳያሳኩ በከረሙ ቁጥር አርጅተው ተሰለቻችተው ተስፋ ቆርጠው ይከስማሉ ። ዋናው ነገር እነሱ ባሰቡት ፍጥነትና የግዜ ስሌት ያቀዱትን እንዳይፈጽሙ እድል አለመስጠት ፤ አለ ምንም ፋይዳዊ ስኬት ግዜ እንዲያስቆጥሩ ማስገደድ ነው። ይህ ሲሆን ግዜ እራሱ በልቶ ያከስማቸዋል። ግዜ በረዘመ ቁጥር የነገሮች ሁሉ ህልውናዊ ምክንያት እየተለወጠ የሰው ልጆችም ምኞት አላማና ገፊ ምክንያት አብሮ ይለወጥና ተቃዋሚዎቹ የተነሱለት ተግባር ትርጉም አልባ ይሆናል። ማንኛውም ማህበራዊ ፖለቲካዊ ወታደራዊ ንቅናቄ በነባራዊ ምክንያት ላይ ካልቆመ በራሱ ትርጉም አልባነት ይከስማል።

ስልት ብዙ አይነት ሲሆን በተቃዋሚዎች ህብረት ውስጥና በያንዳንዱ ድርጅት ውስጥ ያሉትን ቅራኔዎችን በመጠቀም ጠላትን ማድከምና ሽባ ማድረግ ማለት ነው

እድገት እጅግ ትልቁ እነዚህን ፋይዳ ቢስ ተቃዋሚዎችን ማክሰሚያ ፍቱን መድሃኒት ነው። ዛሬ የተቃዋሚ አላማ መንግስትን በአመጽና ሁከት ወጥሮ ከአገር ልማት ፣ ከእድገትና ከስልጣኔ በማደናቀፍ ማህበራዊ ጥያቄዎችን ማበራከትና ሕዝባዊ ቅሬታዎችን ማስፋት ነው። ስለዚህ አንዱና ዋናው ተቃዋሚ ማክሰሚያው ፍቱን እስትራተጂ መንግስት አሁን በያዘው ፈጣን ያገር እድገት ማቀጣጠል ነው። በተቃዋሚዎች ላይ የሚባክነው ግዜና ሃብት ከላይ እንደ ተባለው ተቃዋሚው በግዜ ውስጥ እንዲበሰብስ በሚያደርግ ልክ ተመጥኖ 95% ያገሪቱ ትኩረት እድገት ላይ በማድረግ ተቃዋሚዎች ሁሉ ምክንያት አልባና ኢታሪካዊ በማድረግ ተበታትነው እንዲከስሙ ማድረግ ነው ።

ለምሳሌ ዛሬ ላይ እንኳ አንዳችም የማህበረሰብ ክፍል (ጫካ ውስጥ ከሚታመሰውና ጥቂቶች በተቀር) ሸኔን ፋኖን እና ትህነኝ እንደ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ንቅናቄ አስቦም ሆነ ደግፎ የሚንቀሳቀስ ሕዝብ የለም። ለዚህ ነው ከማህበራዊ ንቅናቄ ያልተወለደ የጎሬላ ተዋጊ ሽፍታ ነው የሚባለው ። ሸኔ ፣ ፋኖና ትህነግ ሽፍቶች ናቸው።


Horus
Senior Member+
Posts: 41921
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢምክንያታዊ ተቃዋሚዎች (ፖለቲካዊም ወታደራዊም) የሚከስሙበት እስትራተጂና ሂደት

Post by Horus » 12 Jan 2026, 14:30

ክብር? ድርድር? ምርኮ?
ከወሎ ከጎንደር ከጎጃም ከሸዋ መዓት ወደ መንግስት እየገባ ነው ! ይህ መልካም ዜና ነው! ያማራ ሕዝብ እረፍት ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 41921
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢምክንያታዊ ተቃዋሚዎች (ፖለቲካዊም ወታደራዊም) የሚከስሙበት እስትራተጂና ሂደት

Post by Horus » 12 Jan 2026, 16:15

በመግቢያዬ ላይ እንዳልኩት ኢሳያስና ተላላኪዎቹ በግዜ ርዝመት፣ ስልትና እድገት ጉዞ ተረስተው በስብሰው እንዲክስሙ እንጂ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ትኩረት እነሱ ባሰሉት እቅድ ወጥመድ ውስጥ መታዝ ስለሌለበት ልክ እንደ ዛሬ እየተሳደቡ ወደ ትቢያ እንዲወርዱ ማድፍረግ ነው የኛ ስራ መሆን ያለበት!

ኢሱ የተባለ የግብጽ ተላላኪ አሁን ላይ ተስፋ መቁረጡን ነው የሚነግረን አለቀ!




Post Reply