Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Mesob
Member
Posts: 2926
Joined: 23 Dec 2013, 21:03

ኢሳያስ ኣፈወርቂ ካብ ተምቤን ይውለድ ድዩ?

Post by Mesob » 23 Dec 2025, 15:11

ኢሳያስ ኣፈወርቂ ካብ ተምቤን ይውለድ ድዩ? ናይ መምህር ሙሉወርቅ መልሲ

Meleket
Member
Posts: 4931
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኢሳያስ ኣፈወርቂ ካብ ተምቤን ይውለድ ድዩ?

Post by Meleket » 24 Dec 2025, 05:14

ይህ መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የተባለው የትግራይ ሰው፡ እንደኛው በረኸት ኣማረ፡ የስነ ትውልድ ተመራማሪም ነው ማለት ነውን? ይህ የአቶ ወልደአብ ወልደማርያም የትውልድ ሃረግስ ምን ያህል እዉነትነት አለዉ? የኛዎቹ ዓዲ-ዛርና ሰዎች ምን ኣስተያዬት ኣላቸው! እዉነትነት ካለው የትውልድ ሃረግ የታሪክ ኣካል ስለሆነ እንዲህ ቁልጭ ብሎ ሲጻፍ መልካም ነው!
Please wait, video is loading...

https://www.facebook.com/photo/?fbid=23 ... 2207520000

Mesob
Member
Posts: 2926
Joined: 23 Dec 2013, 21:03

Re: ኢሳያስ ኣፈወርቂ ካብ ተምቤን ይውለድ ድዩ?

Post by Mesob » 24 Dec 2025, 15:25

ኣቶ ወልደኣብ ወልደማርያም በትግራዋይነት ሓረገ ትውልዳቸው እጅግ በጣም የሚኮሩ ሰውና ፡ ከትግራይ ከየትኛው የትውልድ ማይቤት እንደሚወለዱ ብደምብ ኣጥንተው ያውቁታል። ለምሳሌ ፡ ታላቁ ልጃቸው ራስ ኣሉላ ኣባነጋን ለማስታወስ ፥ ኣሉላ ወልደኣብ ብለውታል።

quote=Meleket post_id=1597619 time=1766567679 user_id=47534]
ይህ መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የተባለው የትግራይ ሰው፡ እንደኛው በረኸት ኣማረ፡ የስነ ትውልድ ተመራማሪም ነው ማለት ነውን? ይህ የአቶ ወልደአብ ወልደማርያም የትውልድ ሃረግስ ምን ያህል እዉነትነት አለዉ? የኛዎቹ ዓዲ-ዛርና ሰዎች ምን ኣስተያዬት ኣላቸው! እዉነትነት ካለው የትውልድ ሃረግ የታሪክ ኣካል ስለሆነ እንዲህ ቁልጭ ብሎ ሲጻፍ መልካም ነው!
Please wait, video is loading...

https://www.facebook.com/photo/?fbid=23 ... 2207520000
[/quote]

Meleket
Member
Posts: 4931
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኢሳያስ ኣፈወርቂ ካብ ተምቤን ይውለድ ድዩ?

Post by Meleket » 26 Dec 2025, 11:45

በትውልድ ሃረጉ የሚያፍር ኣካል ካለ፡ ሞኝ ብቻ ነው። አቶ ወልደአብ መቼም እንደሚታወቀው መጀመርያ ላይ “ትግራይ ትግርኚ” ዬሚል አቋም ነው የነበራቸው፡ ለዛም ይመስላል “የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ተስፋ ኣዅሱም ላይ ነው።” ምናምን ዬሚል ጽሑፍ በወቅቱ ጋዜጦች ላይ ያስተላልፉ የነበሩት። ይህ እንደማይሆን ሲያዉቁ ነው “ኤርትራ ለኤርትራውያን” ወደሚል ኣመለካከት የቀየሩት።

ልጃቸውን አሉላ ብለው ከሰየሙት መብታቸው ነው። ነገር ግን በኩናማ ስፍራዎች ወንጌል ሰብከዋል አስተምረዋልም የሚባሉት አቶ ወልደአብ፡ በኩናማ ህዝብ ላይ ሸቃ አሉላ የሰራውን ግፍስ ያዉቁ ነበር ወይስ አያውቁም ነበር? ያን እያወቁ ልጃቸውን አሉላ ካሉት ትንሽ ደስ አይልም።

የኛው የስነ ትውልድ ተመራማሪ በረኸት ኣማረ፡ የሸቃ አሉላን የናታቸው ወገን የትውልድ ሃረግ ከኤርትራ ነው የሚመዘዘው ብሎ ለህትመት አብቅቶ ነበር! ትውልድ ማለት ሃረግ ስለሆነ፡ እንቁጠር ከተባለ አዳም ላይ ከመድረሳችን በፊት መቼም ስንትና ስንት ቀዬዎችን በትውልድ ጉብኝት እንደምንጎበኝ ግልጥ ነው። ለምሳሌ የአቶ ወልደአብ ዓዛርና ከመድረሱ በፊት ስንት መንደሮችን እንደዳሰሱ እላይ በመምህር ሙሉወርቅ የቀረበው መረጃ ይጠቁመናል። ኣይደለም እንዴ? ኣቶ ወልደኣብን ነፍሳቸውን በመንግስተ ሰማያት ያሳርፍ!

Mesob wrote:
24 Dec 2025, 15:25
ኣቶ ወልደኣብ ወልደማርያም በትግራዋይነት ሓረገ ትውልዳቸው እጅግ በጣም የሚኮሩ ሰውና ፡ ከትግራይ ከየትኛው የትውልድ ማይቤት እንደሚወለዱ ብደምብ ኣጥንተው ያውቁታል። ለምሳሌ ፡ ታላቁ ልጃቸው ራስ ኣሉላ ኣባነጋን ለማስታወስ ፥ ኣሉላ ወልደኣብ ብለውታል።
....

Post Reply