Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Zmeselo
- Senior Member+
- Posts: 37343
- Joined: 30 Jul 2010, 20:43
Post
by Zmeselo » 21 Dec 2025, 20:14
ልዩ መረጃ

የጽንፈኛው ህወሃት አፈርሻ እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው! ፅንፈኛው ህወሐት ቡድን የገጠመውን ህዝባዊ ተቃውሞ እና ቅቡልነት ማጣት ለመቀልበስ በሁሉም ዞኖች የአመራር ስብሰባ እንዲሁም ከተለያዩ ማህበራት እና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ስብሰባ ለማካሄድ እና ህብረተሰቡን ለማስፈራራት የሚያደርገውን ጥረት አሁንም አስቀጥሏል። ይሁን እንጂ ቡድኑ አሁንም እየገጠመው የሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በመቀሌ ከተማ ፀረ-ህወሃት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማካሄድ ምልክቶች እየታዩ መሆኑን ከታማኝ ምንጮች ለማረጋገጥ ተችሏል።
በተለይም ታጣቂ ቡድኑ ከደመወዥ እና ከጥቅማጥቅም ጥያቄ ጋር በተገናኘ በቀጣይ ቀናት ተቃውሞ እንደሚያደርግ የሚጠበቅ ሲሆን የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች ይህንን ተቃውሞ ለመስበር በተቃውሞ አስተባባሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም ነው መረጃዎች የሚያሳዩት። በተለይም በመቀሌ ዙሪያ በተሰማሩ አርሚዎች ላይ የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል። በተመሳሳይ በደቡብ ግንባር የተሰማሩ የህወሃት ታጣቂዎች ከቡድኑ በመውጣት የተደራጁ የሀራ መሬት ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተከትሎ ራያ አላማጣ ወረዳ የተሰማሩ የአርሚ 24 ታጣቂዎች ጣፌ ወደተባለ ቀበሌ የቦታ ለውጥ እንዲያደርጉ ከበላይ አመራር ትዕዛዝ የተሰጣቸው ቢሆንም የቡድኑ ታጣቂዎች እና አመራሮች ትዕዛዙን ለመቀበል ፍቃደኛ አልሆኑም ነው የተሰማው። በዚህም ምክንያት በቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል ልዩነቶች ስለመፈጠራቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል ይህ የጥፋት ቡድን ከጥፋት የማይማር በመሆኑ ሌሎች የጥፋት ሃይሎችን ለዚሁ እኩይ አላማ ለማዋል በማስታጠቅ ተልዕኮ እየሰጠ ይገኛል። በተለይም በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው ፀረ ሰላም ቡድን ለዚህ ቡድን በመገበር ክልሉን እና ህዝቡን ለማሰቃየት የጦር መሳሪያ እና ልዩ ልዩ ድጋፍ መቀበል ከጀመረ ሰነባብቷል። ዛሬ ባገኘሁት ታማኝ መረጃም ይሄው ቡድን በሽሬ ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው በለስ አካባቢ ከሚገኝ የጦር መሳሪያ መጋዘን ውስጥ ሃያ አራት ፍሬ የሞርተር ቁምቡላ እና አምስት መቶ የእጅ ቦምብ ወጪ በማድረግ በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሰው ተላላኪ ቡድን መላኩን ማረጋገጥ ችያለሁ።
በተመሳሳይ ቡድኑ አሁን ክልሉን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ባለው ፍላጎት ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን እያንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። ይሄ ቡድን በተለይ የሰሜን ዕዝን ከጀርባው ካጠቃ በኋላ የደበቃቸውን መሳሪያዎች እያንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ምንጮች ያረጋገጡ ሲሆን በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አበርገሌ ወረዳ ተከዜ ሃይል ማመንጫ ግድብ አካባቢ የተሰማራው የአርሚ 26 ኮር 03 የተባለ የጽንፈኛው ታጣቂ ቀብሮት ያቆየውን TM-57 የተባለ ፀረ-ተሽከርካሪ ፈንጂዛሬ እያወጣ እንደሚገኝ ከቡድኑ የተገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ።
በሌላ በኩል ቡድኑ ከፀረ ሰላም ቡድኑ በተጨማሪ ከኤርትራ ጋር የፈጠረውን ፀረ ኢትዮጵያ ጥምረት በተለያየ ደረጃ እያስኬድ ይገኛል። በዚህ ረገደ የቡድኑ ልዩ ልዩ አመራሮች የግል ጉዳዮቻቸውን ጭምር በኤርትራ በኩል እያስፈፀሙ እንደሚገኝ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ለአብነትም የምዕራብ ግንባር ሎጂስቲክስ ሃላፊ ኮ/ል ሀይለ ማርያም ነጋሽ ከኤርትራ ሰራዊት መረጃ አመራሮች ጋር የፈጠረውን ትስስር በመጠቀም ለጊዜው ማንነታቸው ያልተገለፁ የህወሓት አመራር የቤተሰብ አባላትን በኤርትራ በኩል ወደ ውጭ ሀገራት ለማስወጣት ሁኔታ እያመቻቸ እንደሚገኝም ነው መረጃዎች የሚያሳዩት!