Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 39769
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 28 Nov 2025, 14:08
እኔ 17 ቤተ መጻህፍት ባለው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተማርኩ እድለኛ ነኝ! የልጅነት እውቀቴ የጀመረው ደሞ አይረሴው ወመዘከር ነው!!!
አብርሆት ማለት የዚህ ትውልድ አንጎል መፈጠሪያ መቅደስ ነው!
ግን ብዙ ብዙ አብርሆቶች መግምባት አለባቸው 150 ሚሊዮን አንባቢ ባለበት አገር !
-
Naga Tuma
- Member+
- Posts: 6753
- Joined: 24 Apr 2007, 00:27
Post
by Naga Tuma » 28 Nov 2025, 14:29
“Horus” wrote:
ቤተ እውቀት የሌለው ሕዝብ ሺ ቤተ መቅደስ ቢኖረው ከንቱ ነው!
“Naga Tuma” wrote:
Renaissance 1.0:
ሜሪ ከ ጆን ጋር ኣልተኛችም ማለት ዘበት ነዉ። የጎደስ አቴና የጥንት ግሪክ ዲሞክራሲ ዕዉነት ነዉ።
Renaissance 2.0:
ፕሮፌት ሙሴ ከጎደስ አቴና በፊት የኖረ ታላቁ ፈረኦ አክናተን ኣልነበረም ማለት ዘበት ነዉ። የቦረና የገዳ ዲሞክራሲ ስርዓት ዕዉነት ነዉ።
ከመጀመርያዉ ሬይነሳንስ በኋላ የአዉሮፓ ወጣቶች የአዉሮፓን ታሪክ በጥልቅ ኣጥንተዉ የሰዉ ልጅ ታሪክ ራሱ ከአዉሮፓ የጀመረ መስሏቸዉ ነበረ።
ከሁለተኛዉ ሬይነሳንስ በኋላ የኢትዮጵያ ወጣቶች የኢትዮጵያን ታሪክ በጥልቅ ኣጥንተዉ የሰዉ ልጅ ታሪክ ዬት እንደጀመረ በጥልቁ ይገባቸዋል።
የጥናቶቻዉ መሠረቶች እሩቅ ያሉት ቤተልሔም፣ እየሩሳለም፣ ዮርዳኖስ፣ ወዘተ ዝማሬዎች ሳይሆን ቅርብ ያሉት አክሱም፣ ቦረና፣ አንኮበር፣ ጎንደር፣ አደዋ፣ ኤጄርሰ ጎሮ፣ ደደር፣ አምቦ፣ ሐረር፣ ወዘተ ይሆናሉ።
Source:
መለኮት፣ ባህል፣ ሳይንስ፥ ሬይነሳንስ 101 ለሆረስ
እንደ ወደል በዕዉቀት ተቀጥቅጠህ፣ በዕዉቀት መቀጥቀጥ የማይሰለችህ ወደል ተብለህ፣ ስለ ዕዉቀት ሰጋር መሆን ጀመርክ።
የኤልያስ ክፍሌ ዩኒቨርዚቲን ኣመሰግናለሁ በል።
Horus wrote: ↑28 Nov 2025, 14:08
እኔ 17 ቤተ መጻህፍት ባለው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተማርኩ እድለኛ ነኝ! የልጅነት እውቀቴ የጀመረው ደሞ አይረሴው ወመዘከር ነው!!!
አብርሆት ማለት የዚህ ትውልድ አንጎል መፈጠሪያ መቅደስ ነው!
ግን ብዙ ብዙ አብርሆቶች መግምባት አለባቸው 150 ሚሊዮን አንባቢ ባለበት አገር !
-
Axumezana
- Senior Member
- Posts: 18351
- Joined: 27 Jan 2020, 23:15
Post
by Axumezana » 28 Nov 2025, 15:25
ሆረስ በዚህ ዘመን ትልቁ ቤተመፃህፍት እጅህ ላይ ያለው ሞባይል ነው፤
-
Naga Tuma
- Member+
- Posts: 6753
- Joined: 24 Apr 2007, 00:27
Post
by Naga Tuma » 28 Nov 2025, 15:36
ሞባይል አዲስ ኪዳንን ያመጣልሃል እንጂ የሰዉን ኣዕምሮ ተክቶ አዲስ ኪዳንን ኣይመረምርልህም።
ሞባይል ለጥራዝ ነጠቅነት በቂ ነዉ።
Axumezana wrote: ↑28 Nov 2025, 15:25
ሆረስ በዚህ ዘመን ትልቁ ቤተመፃህፍት እጅህ ላይ ያለው ሞባይል ነው፤
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 39769
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 28 Nov 2025, 15:42
Axumezana wrote: ↑28 Nov 2025, 15:25
ሆረስ በዚህ ዘመን ትልቁ ቤተመፃህፍት እጅህ ላይ ያለው ሞባይል ነው፤
ተሳስተሃል!
በቁሰ ነገርና በሃሳብ (ምናበ ነገር) መሃል ያለው ልዩነት ረሳሃው ። ሃሳብ ማተርን አይተካም ! ኢንፎርማኤን ማተርን አይተካም ! መጽሃፍ ቁሳዊ የውቀት መያዣ ቴክኖሎጂ ነው ! ሃርድ ዌር ነው! ስለዚህ በክላውድና በድጓ መሃል መለየት እንዳይሳንህ!
መጽሃፍ ዘላለማዊ ነው ። ኢንተርኔት የእውቀት መያዣ ዐይም መስሪያ ሳይሆን መረጃ መላኪያ መሳሪያ ነው! እንዲያውም ሰው ሰራሽ ምስልን ሪያሊቲ አስመስሎ በማታለል የእውቀት ተቃራኒ እይሆነ ነው! ፌክ ኒውስ የሚባለው ያ ነው ። እውቀት ፋክት ነው ። አርቲፊሻል እውቀት የሚባል የለም ። እውቀት እውነት ማለት ነው! እውነት ፋክት ማለት ነው ። ይህን ከመገናኛ ቴክኖሎጂ ጋር አታደባልቅ!
-
Axumezana
- Senior Member
- Posts: 18351
- Joined: 27 Jan 2020, 23:15
Post
by Axumezana » 28 Nov 2025, 16:27
Horus you are living in the past , build more hospitals & few libraries !
-
Naga Tuma
- Member+
- Posts: 6753
- Joined: 24 Apr 2007, 00:27
Post
by Naga Tuma » 28 Nov 2025, 21:48
ዛሬ የማዳምጣቸዉ፥
1) የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን እልመ መዻ ታሪካዊ ትረካ
በተለይ፥
ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ ኣንተ ነህ
ተነባቢ የአስር ምስጥር
የሚለዉን።
አደጌን ቃሉ ጄቹ ህን ቤክኔ
አደጌን ቃሉ ቤካ ህን ሴኔ
አደጌን ቤካ ህን ቤክኔ
አደጌን ቤኩምሰ ህን ቤክኔ
አደጌን መዳን ጉረ ህንሴኔ
ጄቴ በር አደዊን ደቺ ሴኔ
2) የኣርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን ኢትዮጵያ የሚል ዘፈን
በተለይ፥
ዞሮ መጀመርያ የሚለዉን።
ወደፊት በሰፊዉ ፕሮፌት ሙሴም ዞሮ መጀመርያዉ ቀዳማዊ ፕሮፌቱ ታላቁ ፈረኦ አክናተን ነበረ ይባል ይሆናል።
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 39769
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 28 Nov 2025, 23:20
ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረ መድህን ሎሬት ያሰኘው በተለኩ ፣ በተጠረቡ ፣ በተከሸኑ ቃላት፣ አረፍተ ነገራትና ስንኞች ቋጥሮ በራሳቸው የሚቆሙ ጽኑ ሕያዋን ስለሰጠን እንጂ ሃሳቡ ለሰው እንዳገባ በቃላት ትርምስና በአረፍተ ነገራት ትብታብ እንዲደበቁ አድርጎ ተረጓሚ የመሃል ደላላ እንዲፈልጉ ስለአደረገ አይደለም ።
አንድ ጸሃፊ አንዲት አረፍተ ነገርን ጽፎ ለሕዝብ ከለቀቃት በኋላ ከዚያ ጸሃፊ ነጻ ሆና ለብቻዋ የምትቆም፣ አላማና ትርጉሙዋ በራሷ የምትገልጽ ፍጡር እንጂ አንባቢ አልገባ ሲለው የጸሃፊውን ድጋፍ የምትሻ ከሆነ ያ ጸሃፊ መጻፍ አያውቅበትም ማለት ነው።
አንድ ሰው በሆዱና አንጎሉ ውስጥ ያዘለውን ሃሳብ በቀጥታ ግልጽ በሆነ ቋንቋና ስልት መግለጽ ሳሆን ያረፍተ ነገሮች ዲሪቶን እውቀት አዘል ቢያስመሰል በንግ ሊዝኛ ኦብስኪዩራንቲዝም ይባላል። ስለዚህ ሎሬት ጸጋዬን መጥፎ ስም መስጠት አይገባህም አቶ ናጋ ቱማ።
አንተ ስራዬ ብለህ የምትደረድራቸው አረፍተ ነገሮች ማንም ሰው በቀጥታ አንብቦ ሃሳብህ ምን እንደሆነ ፣ ምን ለማለት እንደ ምትጥር ፣ የአረፍተ ገረህ አላማና ተልኮ ምን እንደ ሆነ ሊገባው ስለማይችል አንተ ለራስህ በምስጢር ቋንቋ የምትናገር ሰው ነህ ። ይህን መሰል ፍጹም ከስነጽሁፍ ጥበብና መርህ ተቃራኒ የሆነን ባህሪ ከሎሬት ጽጋዬ ስም ጋር አብሮ ማቅረብ ወንጀል ነው ።
እያንዳንዱ ቃልና አረፍተ ነገር ግልጽ የሆነ አላማና ተልኮ አለው ። ካንተ ከዘራነት ድጋፍ ነጻ ሆኖ ካንባቢ ጋር መግባባት አለበት ። መስመር ከተጻፈ በኋላ ካንተ ሙሉ በሙሉ ተለይቶ ለብቻው ሌላው ቀርቶ አንተ ሞተህ እንኳ በራሱ የሚኖር ፍጡር ነው ። ያን መስመር ስትጽፍ አነብሃለሁ ። እስከዚያ ግን አፍረፍተ ነገርህ የማይነግረኝ ሃሳብክን አንጎልህ ውስጥ ስፈልግ ግዚዬን አላባክንም።
ይህ ግንዛቤዬ ስህተት ነው ካልክ ሌሎች ያነበቡህ ታዳሚዎች ይመስክሩልህ።