Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11364
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የኣክሱም ጭፍጨፋ: ትግራይ ውስጥ የተፈፀመው ምንድነው? ብረመስቀል ካሳ ታፈረ የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ሓላፊ

Post by sarcasm » 27 Dec 2021, 11:37

የኣክሱም ጭፍጨፋ (ክፍል 01)
*******************************************************************
16 ሕዳር 2013ዓ/ም በግምት ከቀኑ 08:00 ሰዓት አከባቢ፣ ስካይ ላይት ሆቴል አከባቢ እያለሁ አንድ ስልክ ተደወለልኝ። መኪናየን የመንገድ ዳር አስቁሜ ስልኬን አነሳሁት። 10:00 ሰዓት ሂልተን ሆቴል በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት አስቸኳይ ስብሰባ እንዳለ ተነገረኝ። አላቅማማሁም ወደ ቤት መሄድ ትቸ ወደ ሂልተን ሆቴል አመራሁ። ቡና አብዝቼ ከመውደዴ የተነሳ ቡና ለመጠጣት የሆነ ቦታ ጎራ ስል "ቡና በዕጣን" ብየ ነው የማዝዘው። አንድም በአማረኛ ቅላፄን ሁለቱም በነገርየው ቡዙ ሰዎች ተገርሞም፣ እየሳቁም የሚያዩኝ ጊዜ ብዙ ነው።ወደ ሂልተን ከአመራሁ በሗላ ሆቴሉ ውስጥ ያለው የሐበሻ ቡና "ቡና በዕጣን" ብየ አዘዝኩኝ። ከጎኔ የተቀመጡት ሰውየ በሁኔታየ ተገርሞ "ቡና በዕጣን ነው ወይስ ቡና በስኳር የሚባለው" ብሎ አፌዙብኝ። እኔ ግድ የለኝም ለሚጀዋለሁ። ከሰውየው እያወራን 10:00 ደረሰ። የቡና ሂሳቤን ከፍየ ወደ ስብሰባ አደራሽ ገባሁ። የስብሰባ አደራሹን ሞልቶ የተወሰኑ ሰዎች ጥግ ጥግ ቦታ ይዘው ስብሰባውን ሲከታተሉ ነበሩ።

በስብሰባው በትግራይ ክልል ስላለው አስከፊ ሁኔታና፣ በአማራ ልዩ ሀይልና ምልሻ እንዲሁም ፋኖ በምዕራብ ትግራይ፣ በሰሜን ምዕራብ(ፀለምቲና ማይ ፀብሪ)፣ በደቡብ ትግራይ እየተፈፀሙ ነው ስለተባለው ወንጀልና ወረራ ገለፃ ከተደረገልን በሗላ የትግራይ ህዝብን መልሶ የማደራጀትና ከጥቃት የመከላከል ታሪካዊ ሓላፊነት ስለተጣለብን ወደ ስፍራው እንደናመራ ጥሪ ቀረበልን። ስለ ኤርትራ ጉዳይ እዚህ ስብሰባ ላይ ምንም የተባለ ነገር አልነበረም።

16 ሕዳር 2013ዓ/ም ጠዋት በገንዘብ ሚኒስተር ግቢ ውስጥ ጥሪውን ተቀብሎ ወደ ትግራይ ለመሄድ የተገኘው ሰው ግን 13 ብቻ ነበር። በሶስት ቡድን ማለትም ወደ ምዕራብ ትግራይ(ማይካድራ)፣ ሰሜን ምዕራብ(ሽረ)፣ ደቡብ ትግራይ (ኣላማጣ) ተከፋፍልን ወደ ትግራይ አመራን። ሁሉም ቡድኖች በዚህ ቀን በወልድያ፣ በደብረማርቆስ መግብያና በባህርዳር ከተማ በአማራ ልዩ ሃይል ተከበን ከፍተኛ ወከባና ዛቻ ከደረሰብን በሗላ ወደ አዲስ አበባ በሚቀጥለው ቀን ተጨማሪ የመከላኪያ ሀይል ተልኮልን እንድንመለስ ተደረገ። እኛ ያገተን የልዩ ሀይል አዛዥ "ምዕራብ ትግራይ ከፍተኛ ወንጀል የተፈፀመ ስለሆነ ማንም የትግራይ ተወላጅ አከባቢውን ሳይፀዳ እንዲገባ እንደማይፈቅዱ፣ እንድንገባ ከተፈቀደ በወንጀል የሚጠየቀው የአማራ ክልል መንግስት ብቻ ሳይሆን የፌደራል መንግስትም ጭምር እንደሆነ፣ ህወሓት (በእነሱ አጠራር ትህነግ) ምሽጉ የፈረሰው በመከላኪያ ሳይሆን በአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖና ምልሻ መሆኑን፣በተጨማሪም አማራ በደሙና በአጥንቱ በሀይል ያስመለሰው መሬት ለትግራይ አሳልፎ አይሰጥም" ሲል አስረግጦ ለሓላፊው በስልክ አሳወቀ። ሰውየው ወደእኔ ተጠግቶ መከላኪያ አምናቹህ ምዕራብ ትግራይ ብትሄዱ ሂወታቹ አደጋ ላይ ይወድቃል፣ ይገድላቸዋል፣ የሚያድናቹ የለም፣ መከላከያ እንኳን እናንተ ሊያድን ለራሱ የሚያድነው አካል ያስፈልገዋል"አለን በከፍተኛ ንቀትና ትዕቢት። ሌሎች ቡድኖች የገጠማቸው ዕገታ፣ ዛቻና ማስፈራርያም ተመሳሳይ ነው። የኛ ቡድን(ምዕራብ ትግራይ) በ16 ሕዳር ደብረማርቆስ ከተማ ታግተን ካደርን በሗላ፣ 17ሕዳር 2013 ዓ/ም በመከላኪያ ታጅበን ባህርዳር ከታገተው የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ቡድን ጋር ተቀላቀልን። ምሳ ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የሀገር መከላኪያ ሰራዊት ካምፕ ውስጥ ከበላን በሗላ፣ አመሻሽ ላይ ከወታሃደራዊ ካምፑ በከፍተኛ ጥበቃ፣ጥንቃቄና ምስጢር ወደ ሞጣ ከተማ አመራን። 17 ሕዳር 2013ዓ/ም ያደርነው እዚቹ ከተማ ነው። 18 ሕዳር 2013 ዓ/ም ጥዋት ተነስተን ወደ ኣዲስ አበባ አመራን። ፊቼ አከባቢ በመኪና አደጋ ምክንያት መንገድ ተዘግቶ ብዙ ስዓት ስለጠበቅን ኣዲስ ኣበባ የደረስነው ከሰዓት በሗላ 10:00 ስዓት አከባቢ ነው። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ዋና መስራቤት አዲስ አደረጃጀትና ገለፃ ከተደረገ በሗላ ለሊት 09:ዐዐ ደብረዘይት በሚገኘው የኣየር ሀይል ቅጥር ግቢ ውስጥ እንድንገኝ ተነገረ።

19 ሕዳር 2013 ዓ/ም ጥዋት 02:00 ስዓት ከደብረዘይት አየር ሀይል በወታሃደራዊ የጭነት አውሮፕላን ተሳፍረን ወደ ሽረ ከተማ አመራን። ያ ጊዜ ሁሉም ነገር ጨላማ ነው። ሽረ ኣየር ማረፍያ እንደደረስን ለሁላችንም አዲስ የሆነ፣ አዲስ ክስተት በዐይናችን አየን። ብዛት ያላቸው የኤርትራ ወታሃደሮች በሽረ ሲርመሰመሱ አየን። አያናችን ያየውን ነገር ማመን ከበደው። የሆነውን የኤርትራ ወታሀደሮች ወደ ሽረ መግባታቸው አይደለም።

ትግራይ ምድሯ በደም አጥቧታል። በጠራራ ፀሐይ በሸራሮ፣ ዓዲ ነብሪኢድ፣ ዓዲ ሃገራይ፣ ዓዲ ዳዕሮ ቄሶች፣ ካህናትና ዲያቁናት እንደ በግ ታርዷል። ሴቶች፣ ህፃናትና መንኩሳት በግፍ ተዳፍሯል። የመንግስትና የግል ንብረት በጠራራ ፀሓይ በግላጭ ተዘርፏል፣ወድሟል። ይህንን ሁሉ ምሕረት የለሽ ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል ሲፈፀም የኢትዮጵያ የሀገር መከላኪያ ሰራዊት ቁሞ አይተዋል። እኛ (የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር) በሽረ ከተማ ካገኘነው የሀገር መከላኪያ ሰራዊት ኣዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ብርሃኑ ጥላሁን ጋር ውይይት አደረግን። የሚሆነውን ሁሉ እንዲያቆሙ ጠይቀናቸዋል። ሓላፊውም የሚቻላቸው ሁሉ እንደሚያደርጉ ሁኖም ግን ይህ የበላይ የፖለቲካ ውሳኔ የሚያስፈልገው እንጂ የእሳቸው ሓላፊነት እንዳልሆነ አክብሮት በተሞላበት ንግግራቸው ነገሩን። የኤርትራ ሰራዊትም በትግራይ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሀገር መከላኪያ ሰራዊት እኩል ሓላፊነትና ስልጣን እንዳለው ነገሩን። እዚህ ላይ በሽረ ከተማና አከባቢው በነበረው ዘረፋና ውድመት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የኢትዮጵያ ወታሃደሮችም እንዳተሳተፉ መገንዘብ ያስፈልጋል። በዚች ቀን ትግራይ በኢትዮጵያና ኤርትራ እንደተወረረችም በአይኔ አየሁ። እነዚህ ሀይሎች ሳልፈራ እንድታገላቸውም በውስጤ ወሰንኩኝ።



20 ሕዳር 2013 ዓ/ም በኣክሱም ከተማ በኤርትራ ሰራዊትና የኣክሱም ህዝብ መካከል ከፍተኛ ግጭት መፈጠሩ በሀገር መከላኪያ ሰራዊት በኩል መረጃ ደረሰን። እኔ ሽረ ከተማ ከደረስን በሗላ በአዲሱ አደረጃጀት መሰረት የተመደብኩት ምስራቅ ትግራይ ዞን (ዓዲግራት) ቢሆንም ይህንን አስፈሪ ዜና ከተሰማ በሗላ ወደ ኣክሱም መሄድ እንደምፈልግ ያቀረብኩት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ከሰዓት በሗላ ከሌሎች ሶስት የስራ ባልደረቦቼና፣ 120 የፌደራል ፖሊስ ኮማንደዎች፣ 120 እግረኛ ጦር ጋር ከፊትና ከሗላ በኤርትራ ሰራዊት ታጅበን ወደ ኣክሱም ኣመራን። በሰዐቱ ከእኛ በግራ ክንፍ በኩል ከፍተኛ ትንቅንቅ የተሞላበት ጦርነት ሲካሄድ ነበረ። ከሽረ እስከ መቐለ ያለው 300 ኪ.ሜ በላይ ዋና መንገድ በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ወድቀዋል። ኢትዮጵያ ሉዕላዊነቷ ተድፍሮ፣ ከማንም በታች ሁኗ እጅጉን ዝቅ ብላ አየኋት። ይህንን ሁሉ ውርደት በእኔ ዕድሜና በእኔ ዘመን መፈፀሙ አዘንኩኝ። እንባየን ወደ ውስጥ አድርጌ እንደምንም ራሴንን ለማረጋጋት ሞኮርኩኝ። ከሽረ ወደ ኣክሱም የነበረው ጉዞ ኣስፈሪ፣ አስቀያሚና እጅግ አሳዛኝ ሁኔታዎችን ያየሁበት ነው።

መንገድ ሁሉ በተቃጠሉ ታንኮችና ከባባድ ወታሃደራዊ መኪኖችና ተሞልቷል። መንደሮች በእሳት ጋይቷል። ከአንዲት ህፃን የያዘች ሴት ውጪ ማንም ሰው መንገድ ላይ ኣላገኘንም፣ አላየንም። 20 ሕዳር 2013ዓ/ም ወደ ኣክሱም ከተማ ለመግባት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ምክንያቱ ደሞ የከተማው ምዕራባዊ ክፍል ያለው መግብያ(በተለምዶየንግስተ ሳባ ቤተ መንግስት) ተብሎ በሚጠራ አከባቢ የነበረው የኤርትራ ክምርየአወሬ ሰራዊት እንድንገባ ፍቃድ አልሰጠም። የኢትዮጵያ ወታሃደሮች ኣክሱም ከተማ ለመግባት የኤርትራ ሰራዊት ፍቃድ ግድ ይላቸዋል። የሆነውም ያየሁትም ይሄ ነው። ኢትዮጵያ ተፀንሳ የተወለደችባት፣ የስልጣኔና የእምነት ማዕከል የሆነችው ቅድስት ከተማችን ኣክሱም በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ናት። በኢትዮጵያ ታሪክ ከዮዲት ጉዲት ቀጥሎ ወታሃደራዊ ካምፕ በቅድስት ከተማቲቱ ኣክሱም የሰራ፣ ከሺህ ዓመታት በሗላ የኤርትራ ሰራዊት ብቻ ነው። በውርደት ተከናንበን ከእነ 240 አጃቢዎቻችን የኣክሱም ከተማ መግበያ ጋር አስፓልት መንገድ ጋር በየመኪናችን ስር ተኝተን አደርን። እንቅልፍ ግን ሊይዘኝ አልቻለም።

21 ሕዳር 2013ዓ/ም ጥዋት ወደ ኣክሱም ከተማ እንድንገባ በኤርትራ በኩል ፍቃድ ስለተሰጠ፣ አዲሱ የከተማውን አስፓልት መንገድ ይዘን ወደ ዓድዋ ከተማ መስመር ከተጓዝን በሗላ፣ አቅጣጫችን ቀይረን ከምስራቅ ወደ ምዕራብ የድሮ አስፓልት መንገድ ይዘን፣ ወደ መሀል ከተማ ገባን። ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ ባንኮች ሁሉም ተዘርፏል። ከተማው መሀከል ያለው ብራና ሆቴል በቦምብ ሆነ ተብሎ ወድሟል። ከሁሉም በለይ ደሞ የኤርትራ ሰራዊት 19 ሕዳር 2013 ና 20 ና 21 ሕዳር 2013 በመቶዎች የሚቆጠሩ የአክሱም ነዋሪዎች በቤት ለቤት አሰሳና በየመንገዱ ረሽኗል። ቤተሰብ የሚወድዋቸው ዘመዳቻቸው እንዳይቀብሩ ለሶስት ቀን ሙሉ ተከልክሎ ነው እኛ የደረስነው። በከተማዋ ሁሉም ስፍራዎች የተጨፈጨፉት ዜጎች የኤርትራ ሰራዊት አስፈቅደን በጋሪ ቀብረናቸዋል። ይህንን ሁሉ የፌደራል ፖሊስ ኮማንዶ እየመራ ከእኛ ጋር የሄዱት ኮማንደር መሓመድና ኢንስፔክተር ግርማ፣ ከሀገር መከላኪያ ሰራዊት ብርጋዴር ጀነራል የሻምበል ፈረደና ሻምበል ዓሊ በአይናቸው አይተዋል።በከተማዋ የተጨፈጨፉትን ዜጎች በጋሪ ለቀመን ለመቅበር ሁለት ቀን ፈጅቶብናል። ገሚሶችም በአወሬ ተበልቷል።

20 ሕዳር 2013 ዓ/ም እኛ ኣክሱም ከመግባታችን በፊት የኤርትራ ሰራዊት የኣክሱም ከተማ ነዋሪዎችን ሰብስቦ ከዚህ በሗላ አማራ የሚባል ሀይል (በእነሱ አጠራር ኢትዮጵያ ማለታቸው ነው) በኣክሱም ከተማ እንደማያልፍና የኤርትራ መታወቅያም እንደሚሰጣቸው ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። እኛም በሚቀጥለው ቀን በማክሮፎን እየዞርን ከፌደራል መንግስት የኢትዮጵያ ግዚያዊ አስተዳደር ክልል እንደተመሰረተና አሰንደተዋቀረ አስነገርን። በኣክሱም ከተማ ከአስር ቀናት በላይ የቆየን ሲሆን በእነዚህ ቀናቶች ሁሉ የኤርትራ ሰራዊት ከጥዋቱ 02:30 እስከ 10:00 ስዓት ዘረፋ ሲፈፅሙ ነበር። ዘረፋውን የሚፈፀመው እጅግ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ነው። ከኤርትራ የጦር መኮንኖች በግሌ ባደረግኩት ድርድር የጅምላ ጭፍጨፋዎች ማቆም ብችል እንኳን፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት ግን ለመከላከል አልተቻለም። ዓይናችን እያየ የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ክፍል ነቃቅሎ ለመውሰድ ስላልቻሉ ሆን ብሎ እንዲወድም ተደርጓል። በከተማዋ የነበሩ የግልና የመንግስት ኮሌጆች፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣብያዎች፣ ፋብሪካዎች በሙሉ ያለ ምሕረት ተዘርፏል፣ ወድሟል። እኔ ያገኘሁት የኤርትራ ጦር መሪ ሰፊ ውይይት ያደረግን ቢሆን እንኳን እነሱ እያደረጉት ያሉት ወንጀል ሁሉ በበላይ ሓላፊዎች ትዕዛዝና ከኢትዮጵያ መንግስት ቀደም ብሎ በገቡት ውል መሰረት እንደሆነ ነግሮኛል። በግዜው የፌደራል መንግስት ተጨማሪ ሀይል ልኮ ከተሞች እንዲጠበቁ ብንጠይቅም "የኤርትራ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ የለም፣ ኣርፋቹና ካለው ሀይል ጋር ተስማምታቹ ስሩ" የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ነው የተሰጠን። አሁን ኣክሱም ከተማ ላይ በጋሪ የቀበርኳቸው ከ 800-1100 የሚሆኑ ንፁሀን ዜጎች መንግስት ለኤርትራ ወግኖ አልተገደሉም፣ በገለልተኛ አካልም አይጣራም እያለን ነው። ስለዚህ ባንዳ፣ ጡት ነካሽና የኢትዮጵያ ጠላት ማን ነው? ይህንን ፅሁፍ ለሕሊናየ ነፃነት፣ ለህዝቤ ያለኝ ቀናኢነት ግምት ውስጥ በማስገባት የፃፍኩት ነው። ከዚህ ፅሁፍ ውስጥ አንዲት ውሸት ከተገኘች፣ ሁሉንም የሚያይና የሚሰማ እግዚአብሔር ይቅጣኝ!

ሰላም ለእናንተ ይሁን
ገብረመስቀል ካሳ ታፈረ
የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ሓላፊ
09 ታህሳስ 2014 ዓ/ም


ትግራይ ውስጥ የተፈፀመው ምንድን ነው?
*የኣክሱም ጭፍጨፋ ክፍል 02
*********************************************************************

22 ሕዳር 2013ዓ/ም ጥዋት አልጋ ከያዝንበት ኣትራኖስ ሆቴል ተነስቸ ወደ ፅዮን ማርያም ቤተክርስያን ለመሄድ ፈልጌ ስንቀሳቀስ ለእኛ የተመደበው የዕጀባ ክፍልም አብሮኝ ተንቀሳቀሰ። ለፀሎት ወደ ቤተክርስቲያን እንደምሄድና ዕጀባ እንደማያስፈልገኝ ብነግራቸውም ኮለኔል ብርሃኑና ሻምበል ዓሊ (የ23ኛ ክ/ጦር አባላት) በሃሳቤ አልተስማሙም። ያለ ዕጀባ መንቀሳቀስ ይቅርና ከተማ ውስጥ በዕጀባም ጭምር መንቀሳቀስ እጅግ አደገኛ እንደሆነ ነገሩኝ። ወደ ቤተክርስትያን አብረን ከሄድን በሗላ ምዕመናን ወታደሮች ማየት ስለማይፈልጉ ኸእኔ ራቅ ብሎ እንዲቆዩ ተማፀንኳቸው። ከሰሜን በኩል ባለው የፅዮን ማርያም ቤተክርስትያን በር፣ የዓለም የስልጣኔ ማማ ማሳያ ከሆኑት የኣክሱም ሓወልቶች በስተ ደቡብ አቅጤጫ ቁሜ እንደምንም ሀሳቤን አሰባስቤ ፀሎት ለማድረግ ሞኮርኩኝ። ደንገት አጠገቤ አንዲት እናት በተመስጦና ከልብ ከመነጨ ሀዘኔታ እንዲሁም ከባድ የሀዘንና የልብ ስብራት በተሞላበት አኳሃን እግዚኣብሔር ያ ሁሉ ሰቆቃ በቅድስቷ ምድር ኣክሱም እንዲያቆመው ፈጣሪያቸውን እንባ ከፊታቸው እየፈሰሰ ለመኑት። ከዚህ በላይ አልቻልኩም፣ ፀሎቴን ኣቋርጨ ወደ ቤትየ ተመለስኩኝ።

ከቤተክርስያን ከተመለስኩኝ በሗላ ከስራ ባልደረቦቼ ሁነን የኣክሱም ህዝብ ተከፋፍለን ለማወያየት የስራ ክፍፍል አደረግን። ኣክሱም በአምስት ቀበሌዎች የተከፋፈለች ነች። እኛ አራት ሰዎች ብቻ ነን። እኔ ሁለት ቀበሌዎች እንድሰበስብ ተስማማን። ካልተሳሳትኩኝ ቀበሌ 04 ና 05 (ክንዳያ ና ንግስተ ሳባ ቀበሌ ነዋሪዎች ) እኔ ነኝ የሰበሰብኳቸው። በግምት ከረፋዱ 05:00 (11:00 AM) ሰዓት አከባቢ መሀል ከተማ ባለው ትልቁ ዋርካ ስር ህዝቡ ሰብስቤ ለማወያየት ሞኮርኩኝ። እዚህ ስብሰባ ከግምቴ በላይ ህዝብ ስለመጣ፣ በክፍት ቦታ (open air) የሚደረግ ስብሰባም ስለነበረ፣ የኤርትራ የስለላ ክንፍ ስብሰባ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ስለአወቅኩኝ፣ ለተሰብሳቢዎች አንድ ጥብቅ ማሳሰብያ ነገርኳቸው።

ስለ ጎረቤቶቻችን ( የኤርትራ ጉዳይ ማለቴ ነው) ሀሳብ መስጠት አይቻልም፣ የነሱ ጉዳይ (የኤርትራ ) ለእኔ ተዉት፣ የሰሩትን ዘር የማፅዳት ወንጀል(Genocide ) በአይኔ አይቸዋለሁ፣ ለሚመለከተው አከል ሪፖርት አድርጊያለሁ፣ እናንተ ስለተናገራቹ የሚመጣ ለውጥ የለም፣ አጋጥሞን ያለው የፖለቲካና ወታሃደራዊ ችግር በደንብ ተረዱት፣ ከቻላቹ ከኤርትራ ወታሃደራዊ ሀላፊዎች ጋር በሽማግሌ ለመወያየት ሞክሩ፣ የሚዘርፉት ጉዳይ፣ ተሸክሞው እየወሱዱት ያሉት ተሸክሞ ይመሉስታል፣ በዚህ ጉዳይ ጥርጣሬ አይግባቹህ እያልኩኝ ለማግባባት ሞኮርኩኝ። የኣክሱም ሰዎች ይህንን ጉዳይ ፍፁም አልተዋጠላቸውም ነበረ። በመሀል የሰዉ መብዛት ያየው ባሻይ (የደቡብ ልጅ ነው) በጆሮየ ጠጋ በሎ "ያለው ሁኔታ አደገኛ ነው፣ ስብሰባውን ማቆም አለብህ፣ እኛ ልንከላከልልህ አንልችልም፣ ሰው በዛ" አለኝ። እንግዳ(የጎጃም ልጅ) ስናይፐሩን እንዳቀባበለ ከሗላየ ሁኖ ለመከላከል ሙከራ እያደረገ ነበረ። ሁኔታው አደገኛና አስፈሪ ቢሆንም አማራጭ የለም። እንግዳና ባሻይ እጅግ ሲበዛ ጥሩና እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው። በውስጤ ምን አለ ሁሉም ወታደሮች እንደነሱ ቢሆኑ እያልኩኝ እሺ አሳጥረዋለሁኝ አልኩት። ለስብሰባ የመጡት ሰዎች ስለ ኤርትራ ሀሳብ መስጠት አይቻልም ስላልኩት ጉዳይ አልተቀበሉትም። አጉሮመረሙ። የኣክሱም ሰዎች ያንን ሁሉ ግፍና ጭፍጨፋ ተፈፅሞ እያዩም ትንሽ እንኳን አይፈሩም። ቅድስት ከተማቸው በአወሬና ጨካኝ፣ እምነትና ስርዐት በሌለው ሀይል ተወሮ እያዩ እንኳን የሚጠይቁት "ህግና ስርዐት የለም"? መንግስትና ስርዓት ይመጣል ይሄዳል፣ ግን ንፁሀንን እንዲህ መበደል ምን አመጣው"? ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወታሀደሮቹስ (የኢትዮጵያ ማለታቸው ነው) ቁሞ የሚያዩን ለምንድነው? እኛ የኢትዮጵያ ዜጎች አይደለንም?" ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች እኔ መልስ የለኝም። ጥያቄዎቹ የእኔም ጥያቄዎች ናቸው።

በተቻለኝ መጠን ህዝቤን ለማረጋጋት እየሞኩርኩኝ ባለሁበት ሁኔታ ከሰሜን በኩል ከገዳም ፅዮን እድሚያቸው እጅግ የገፋ የገዳሙ አገልጋይ (መነኩሴ) በደከመ ጉልበታቸው ፈጠን ፈጠን እያሉ ወደ እኛ መጡ። "ልጄ! ልጄ! ልጄ! ድንግል ቅድስት ማርያም ትጠብቅህ፣ የኤርትራ ወታሃደሮች ወደ ገዳማችን ገብቷል፣ እኛ ሰላዕ (የቤተክርስያን ደወል) ልንደውል ነው፣ ሰላዕ ከተደወለ የሀይማኖት ጦርነት ታወጀ ማለት ነው፣ ህዝቡ የያዘውን ይዞ ገዳሚቱ ሊከላከል ይመጣል፣ እነሱም ጨካኞች ናቸው ህዝቡን አይምሩትም ይጨፈጩፍታል፣ስብሰባውን ይቆይልህ ና እነዚህ አራዊቶች አስወጣልን፣ አሉኝ ቁጣ በተሞላበትና በተቆራረጠ ድምፃቸውን"። ገዳም ፅዮን ማርያም ኣክሱም በኣፍሪካ ምድር የመጀመርያው ገዳምና ቤተክርስትያን እንዲሁም በገዳሙ ውስጥ "የፅላቴ ሙሴ" (Arc of the covenant) አቅፎ የያዘ ነው።
ስብሰባውን አቋርጠን፣ ህዝቡ ትተን እኔ፣ እንግዳና ባሻይ በምዕራብ በኩል ባለው የቤተክርስያን ደጃፍ በርግደን ገባን። ዙርያው በኤርትራ ወታሀደሮች ተከቧል።

ወታሃደሮቹ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ቁሟል። እንግዳ "ከዚህ ገዳም አንወጣም ካሉ እገጥማቸዋለሁኝ፣ የታጠቁት ክላሽ ነው በዚች ስናይፐር እጨርሳቸዋለሁ፣ ለእኔ እዚህ ገዳም ውስጥ ሞሞት ፅድቅም ክብርም ነው፣ አንተ ወጣት ነህ ሞሞት የለብህም፣ ይህንን ማየት አይገባህም ነበር፣ እምቢ ካሉ አንተ ማምለጫ መንገድህን አይትህ አምልጥ፣ አንላቀቅም! አብዝቶቷል!" አለ። እንግዳ እጅግ ተቆጥቷል። ይሁን እንጂ አለቆቹ ከላይ አልታዘዝንም በሚል ተልካሻ ምክንያት የኢትዮጵያ ውድመትና ውርዴት ቁሞ የሚያዩ ተንቀሳቃሽ ሬሳ ናቸው። ባሻይ በሬድዮ ግንኙነቱ እኔ እማላቀውን ወታሀደራዊ መልዕክት አስተላለፈ። ካልተሳሳትኩኝ ለአለቆቹ ተጨማሪ ሀይል እንዲልኩ ነው የጠየቃቸው። የኤርትራ ወታሃደሮች የቤተክርስትያኑ ደወል አልፎ፣ ለወንዶች ብቻ የተፈቀደውን መጀመርያ በንጉስ ኢዛና፣ በዮዲት ጉዲት ከፈረሰ በሗላ ድጋሚ በንጉስ ፋሲለደስ የታነፀውን ገዳም ፈትሾ ከጨረሱ በሗላ ደረስንባቸው። በቀጥታ ወደ ኤርትራ የጦር ሓላፊ (በግምት ኮለኔል ይመስለኛል) ተጠግቼ መታወቅያውን እንዲያሳየኝ እንዲሁም ገዳም ውስጥ ለምን እንደገባ ጠየቅኩት። ጦርነትም ህግ አለው፣ እናንተ ግን የጦርነት ህግም ስርዓትም አታውቁም፣ ይሀ በዓለም ያሉ ህዝበ- ክርስትያን በሙሉ ቤት ነው፣ ትንሽ አታፍሩም፣ እግዚአብሔር አትፈሩም ጨመርኩለት። ሁኔታየን አይቶ እንዲረጋጋ ከጠየቀኝ በሗላ "የከተማውን ህግና ስርዓት እያስከበሩ እንደሆነና ለሊት ከገዳሙ ውስጥ ሁኖ የህወሓት ወታደሮች (TPLF fighters) እንደሚተኩስባቸው" አይኑን በጨው አጥቦ በውሸት ሊያሳምነኝ ሞኮረ። እንግዳ "አትዋሽ ዛሬ ለሊት እዚህ ከተማ የተተኮሰ ጥይት የለም! ከተማውን ለመጠበቅ ስንዞር ነው ያደርነው፣ በቁጣ መለሰለት"። እንግዳ ጀግና ነው። የኤርትራ የጦር አዛኝ ለጊዜው ቢሆን ከገዳሙ ለመውጣት ተስማምቶ ሰራዊቱን ይዞ ወጣ።

የገዳሙ ፓፓስ ከቀናት በፊት ወደ ኣክሱም ፅዮን በዓል ከዓድዋ ሲመጡ የኤርትራ ወታሀደሮች ዓዲ ኣቡን ተብሎ በሚጠራ አከባቢ አቁሞ፣ የፓፓሱ መኪና ቀምቶ ወደ ኤርትራ ወስዷል። ፓፓሱም በእግራቸው 25ኪ.ሜ አከባቢ ተጉዞ ኣክሱም ከተማ ደርሷል። ፓፓሱ በሂወት ስላሉ ማንም እውነታውን ማወቅ የሚፈልግ ኣክሱም ሂዶ ሊጠይቃቸው ይችላል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በትግራይ ውስጥ ያሉት አገልጋይ ካህናቷ፣ ቄሳትና ፓፓሳቷ ክብራቸው ተዋርዶ፣ ሰብአዊ መብታቸው ተገፎ፣ በኤርትራ፣ በሶማልያ ወታደሮች እንዲሁም ኢትዮጵያዊነታቸው በካዱ የኢትዮጵያ ወታደሮች የግፍ መዓት ሲወርድባቸው እስካሁን ጉዳዩን አይመለከተኝም ብላ ትንፍሽ አላለችም። የቤተክርስትያን ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚሸኑ፣የሚፅዳዱ፣ መገራጀዋ የሚቀዱ አረሜነዎች ቁማ እያየች ነው። እጃቸው በደም በጨቀየ ወታሃደሮች ቄሶች፣ ካህናት፣ ዲያቁናት ሲዋረዱም ሲታረዱም አይታ እንዳላየች ዝም ብላለች። ይባስ ብሎ ሰላም እንዲወርድ እንደመለመን፣ ህዝበ ክርስትያኑ እንደማሳመን፣ የቤተክርስትያንዋ ክብር የሚያዋርዱ፣ የህፃናትና ሴቶቸች፣ እንዲሁም የመላ ስብአዊ ፍጡሮችና እንሰሳትን ሰላም የሚያውኩ፣ በመስቀል ሳይሆን በጠመንጃ የሚያምኑ ወታደሮች መርቃ ወደ ትግራይ እየላከች ነው። ህዝበ መስሊሙም እንደሆነ እንደዛ ነው።

በኣፍሪካ እንዲሁም በዓለም ቀዳሚ የሆነ ቅዱስ የነጋሺ መስጊድ በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታሀደሮች ተመትቶ እንደፈረሰ እያወቁ ዝም ብሏል። የጋዚጠኞች ቡድን ጨምሮ ነጋሽ መሰጊድ ላይ ስለተፈጠረው ጉዳይ የሚያጣራ ቡድን ከኣዲስ ኣበባ ሲላክ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር በመወከል ቦታውን ድረስ ይዧቸው የሄድኩት እኔ ነኝ። የቡድኑ ስራውም የመራሁት እኔ ነኝ። ከኢትዮጵያ እስላማዊ ጉዳዮች የተላከው ሰው ከመስጊዱ አስተዳዳሪ ሼኽ የተሰጠንን ምስክር ሰምቷል። ቅዱስ ስፍራው በከባድ መሳርያ ከተመታ በሗላ የኤርትራ ወታሃደሮች በጠራራ ፀሓይ፣ በሚልዮኖች ብር በቱርክ መንግስት ድጋፍ የተደራጀው መስጊድ ፣ አንድም ንብረት ሳይቀር እንደተዘረፈ በኣላህ ፊት የሚነግራቹ ይሄ ነው አላሉንም? ይህንንም ጉዳይ የኢትዮጵያ እስላማዊ ጉዳዮች ከሀይማኖታቸው ይልቅ ፖለቲካ በልጠቧቸው ዝም ብሏል። ጊዜ ደጉ ስንት ጉድ አሳየን።ኢትዮጰያውያን ትግራይ ቅድስት ስፍራቹ ናት፣ ጠብቋት፣ አክብሯት ስንል ሰሚ የለም። የትግራይ ጥቃት የመላ ኢትዮጵያውን ጥቃት ነው ፣ የትግራይ ህዝብ ጥቃት አብረን እንከላከለው ስንልም ሰሚ የለም። ስለዚህ ትግራይ ለኢትዮጵያ ምንዋ ነች? እናንተ ፍረዱ!!!

እኔ ግን እላለሁ ከዚች ከፃፍኳት ፅሁፍ ትንሽየ ውሸት እንኳን ካለች፣ ሁሉንም የሚያይና የሚሰማ እግዚኣብሔር ይቅጣኝ! አሁንም ለሰላም ጊዜ አለ። አልመሸም፣ አልረፈደም!

ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ገብረመስቀል ካሳ ታፈረ
የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አሰፈፃሚ (ፕረዚዳንት) ፅ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ሓላፊ
10 ታህሳስ 2014 ዓ/ም


https://www.facebook.com/gerre.kassa/po ... 5416532505

https://www.facebook.com/gerre.kassa/po ... 7952698918

Meleket
Member
Posts: 4772
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኣክሱም ጭፍጨፋ: ትግራይ ውስጥ የተፈፀመው ምንድነው? ብረመስቀል ካሳ ታፈረ የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ሓላፊ

Post by Meleket » 28 Dec 2021, 11:08

ወዳጃችን ገብረመስቀል ካሳ ታፈረ፡ በየትኛው ስሌት ነው ገዳም ፅዮን ማርያም ኣክሱም በአፍሪካ ምድር የመጀመሪያው ገዳምና ቤተክርስትያን የተባለችው፧ :lol:

ኤርትራዊቷ ደብረሲና እንዳትሰማዎ። ደብረሲና ማለት ኢዛናን ሳይዛናን ያጠመቀችዋ፡ የመጀመሪያዎቹን የአኵሱም ክርስትያን ነገስታት ያጠመቀችዋን ማለታችን ነው።

እነ ግብጽ ኣልጀሪያና ቱኒዚያም እንዳይሰሙዎ፡ ጨዋታው በአፍሪካ ምድር የመጀመሪያው ገዳምና ቤተክርስትያን ማለትዎ ላይ ነው ያለው፡ በዚያ በኵል ያለውን ትርክትም መስማት ሳያስፈልግዎ አይቀርም

ከሣቴ ብርሃን አቡነ ሰላማም ከግብጽ ወደ ያሁኖቹ ኤርትራና ኢትዮጵያ ተልከው መምጣታቸውንም አይዘንጕ።
:mrgreen:
sarcasm wrote:
27 Dec 2021, 11:37
. . . ገዳም ፅዮን ማርያም ኣክሱም በኣፍሪካ ምድር የመጀመርያው ገዳምና ቤተክርስትያን . . .

እኔ ግን እላለሁ ከዚች ከፃፍኳት ፅሁፍ ትንሽየ ውሸት እንኳን ካለች፣ ሁሉንም የሚያይና የሚሰማ እግዚኣብሔር ይቅጣኝ! አሁንም ለሰላም ጊዜ አለ። አልመሸም፣ አልረፈደም!

ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ገብረመስቀል ካሳ ታፈረ
የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አሰፈፃሚ (ፕረዚዳንት) ፅ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ሓላፊ
10 ታህሳስ 2014 ዓ/ም

Meleket
Member
Posts: 4772
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኣክሱም ጭፍጨፋ: ትግራይ ውስጥ የተፈፀመው ምንድነው? ብረመስቀል ካሳ ታፈረ የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ሓላፊ

Post by Meleket » 30 Dec 2021, 04:44

የትግራዮቹ ወንድሞቻችን እነ sarcasm , Axumezana, Thomas H, Halafi Mengedi, ተባብራችሁም ቢሆን እስቲ ያያ ካሳን ልጅ ጠይቁልንና ማብራሪያ ቢጤ ኣቅርቡልን። . . . ኢየሱስ በስቅላት እንዲሞት ተፈርዶበት ወደ ጐልጐልታ የመስቀያዉ ስፍራ ሲጓዝ እንግልቱ በዝቶበት ሁለት ሶስቴ መንገድ ላይ እንደወደቀ የምዕራቡ ትውፊት ይገልጻል። መንገድ ላይ ስምዖን የተባለ የሲሪናይካ [ስምዖን ቀሬናዊ] ማለትም የሊቢያ ሰው የኢየሱስን መስቀል እንዲሸከምና ኢየሱስን እንዲረዳው በወታደሮቹ ጭፍራ ታዞ እንደነበርም ወንጌል ላይ ቁልጭ ተደርጎ ተገልጿል [ማርቆስ 15፡21 ]።

በተጨማሪም በሃዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2:10 እና ምዕራፍ 6:9 እንዲሁም ምዕራፍ 11፡20 አካባቢ፡ የሊቢያዋ “ቀሬና” ተጠቅሳለች። ይህ ማለት የሊቢያና የሰሜን አፍሪካ ሰዎች ‘የምሥራቅም ጭምር’ በሃዋርያት እጅ መጠመቅ ብቻ ሳይሆን፡ ከዚያም ኣልፎ ራሱ ወንጌልን ከወንጌላዉያንና ከሓዋርያት ኣፍ ብቻ ሳይሆን፡ ከራሱ ከእምዬ ማርያም ልጅ ከኢየሱስ አፍም በቀጥታ እንደሰሙና እነሱም በበኩላቸው ለግሪኮች ሳይቀር ወንጌልን እንደሰበኩ ይጠቁመናል። ታዲያ ይህን አባባል ከአያ ካሳ ልጅ ኣባባል ጋር ኣጣጥሞ ኣዅሱምን ለማግዘፍ ያዳግታል። ገዳማዊና የምንኵስና ህይወት አጀማመርም ወደነ ግብጽ ያደላ ይሆን እንደሁ እንጂ . . . ወደ ኣኵሱም ኣይጠቁመንም። ነው ወይስ እነ ግብጽና ሊቢያ ቱኒዝያና ኣልጀሪያ ከአፍሪካ ጋር ኣይቆጠሩም፧ እስራኤል ኣገር የነበሩት አንዳንድ ክርስትናን በማለዳ የተቀበሉ የቀሬናና የሰሜን አፍሪካ ሰዎች ወደ አፍሪካ መጥተው ቤተክርስትያን ሆነ ገዳም የማይመሰርቱበት ምን ምክንያትስ ኖሯል፧ ብለንም እንጠይቃለን፡ አዋቂዎች እስኪመልሱልን።

ግራም ነፈሰ ቀኝ፡ ኣክሱም ማርያም ጥዮን በምንኛው ስሌት ነው ያፍሪካ የመጀመሪያ ገዳምና ቤተክርስትያን የተባለችው ግልጥ ኣይደለም። አንባቢ እኛም ጭምር ማብራሪያ በጭዋ መልክ እንጠይቃለን። አጥጋቢ ማብራሪያና መልስ ካልተሰጠ ደግሞ ኣባባሉን በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ እንደ ተራ ራስን ለማስዋብና ገጽታን ለመገንባት የሚደረግ የካድሬዎች መፍጨርጨርና ከንቱ ልፈፋ ቆጥረን እናልፈዋለን፤ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች።
:mrgreen:
Meleket wrote:
28 Dec 2021, 11:08
ወዳጃችን ገብረመስቀል ካሳ ታፈረ፡ በየትኛው ስሌት ነው ገዳም ፅዮን ማርያም ኣክሱም በአፍሪካ ምድር የመጀመሪያው ገዳምና ቤተክርስትያን የተባለችው፧ :lol:

ኤርትራዊቷ ደብረሲና እንዳትሰማዎ። ደብረሲና ማለት ኢዛናን ሳይዛናን ያጠመቀችዋ፡ የመጀመሪያዎቹን የአኵሱም ክርስትያን ነገስታት ያጠመቀችዋን ማለታችን ነው።

እነ ግብጽ ኣልጀሪያና ቱኒዚያም እንዳይሰሙዎ፡ ጨዋታው በአፍሪካ ምድር የመጀመሪያው ገዳምና ቤተክርስትያን ማለትዎ ላይ ነው ያለው፡ በዚያ በኵል ያለውን ትርክትም መስማት ሳያስፈልግዎ አይቀርም

ከሣቴ ብርሃን አቡነ ሰላማም ከግብጽ ወደ ያሁኖቹ ኤርትራና ኢትዮጵያ ተልከው መምጣታቸውንም አይዘንጕ።
:mrgreen:
sarcasm wrote:
27 Dec 2021, 11:37
. . . ገዳም ፅዮን ማርያም ኣክሱም በኣፍሪካ ምድር የመጀመርያው ገዳምና ቤተክርስትያን . . .

እኔ ግን እላለሁ ከዚች ከፃፍኳት ፅሁፍ ትንሽየ ውሸት እንኳን ካለች፣ ሁሉንም የሚያይና የሚሰማ እግዚኣብሔር ይቅጣኝ! አሁንም ለሰላም ጊዜ አለ። አልመሸም፣ አልረፈደም!

ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ገብረመስቀል ካሳ ታፈረ
የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አሰፈፃሚ (ፕረዚዳንት) ፅ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ሓላፊ
10 ታህሳስ 2014 ዓ/ም


Post Reply