Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum















MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: ዘመቻ አንድነት በመላው አማራ

Post by MINILIK SALSAWI » 09 Nov 2025, 03:46

አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጠ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሮሃ ሚዲያ ጋር ያደረገው ቆይታ ..... https://x.com/i/status/1987426128651284650


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በደሴ ዙሪያ ወረዳ በተደረገ ውጊያ የአገዛዙ ኃይል ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት ታወቀ!

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Nov 2025, 00:59

በደሴ ዙሪያ ወረዳ በተደረገ ውጊያ የአገዛዙ ኃይል ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት ታወቀ!

በደሴ ዙሪያ ወረዳ አጥንት መስበሪያ እና እሁዲት ተብለው በሚጠሩ አከባቢዎች ላይ በተደረገ ውጊያ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአድማ ብተናና የሚኒሻ አባላት ሲገደሉ፣ በርካቶች መቁሰላቸውን በአፋብኃ የምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

አፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃና ጥቅምት 27/2018 ዓ/ም የተመረቁት አዲሶቹ የልዩ ኮማንዶ አባላት በጋራ በመሆን ነው በጠላት ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድ ድሉን የተቀዳጁት ብሏል ዕዙ ለጣቢያችን በላከው መረጃ።

ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው ሙትና ቁስለኛ ከመሆን የተረፈው የጠላት ኃይል ወደ ኩታበርና ደሴ መፈርጠጡንም የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በላከው መረጃ ጨምሮ ገልጿል

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በምዕራብ አማራ ቀጠና ሕዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል!

Post by MINILIK SALSAWI » 10 Nov 2025, 01:05

በምዕራብ አማራ ቀጠና ሕዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል!

በምዕራብ አማራ ቀጠና በሰዴ ወረዳ አዲስአለምና ሂወተ ሰላም ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ጥልቅ ውይይት መደረጉን እንዲሁም አዳዲስ ሕዝብ ተኮር የሆኑ መዋቅሮችን መዘርጋቱን በአፋብኃ አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አሳውቋል።


Post Reply