Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

“የመደመር መንግሥት” በዋነኛነት የሚያስፈልገው የቱ ነው?

You may select 1 option

 
 
View results

Meleket
Member
Posts: 4773
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

“የመደመር መንግሥት” በዋነኛነት የሚያስፈልገው የቱ ነው?

Post by Meleket » 19 Sep 2025, 04:34

ሀ. ወደብ መከራዬት
ለ. ወደብ መውረር
ሐ. አደብ መግዛት
መ. ወደብ መግዛት

Meleket
Member
Posts: 4773
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “የመደመር መንግሥት” በዋነኛነት የሚያስፈልገው የቱ ነው?

Post by Meleket » 20 Sep 2025, 04:01

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ለማገዝ ያክል ነው!

viewtopic.php?f=2&t=287697
sarcasm wrote:
25 Jan 2022, 20:15
Please wait, video is loading...

Meleket
Member
Posts: 4773
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: “የመደመር መንግሥት” በዋነኛነት የሚያስፈልገው የቱ ነው?

Post by Meleket » 20 Sep 2025, 04:20

ድምጽ ሰጪዎች ታሪክን በወጉ አጢነው በእውቀት የታጀበ ድምጽ ይሰጡ ዘንድ ለማበረታታት ያህል ነው!
Meleket wrote:
13 Sep 2024, 11:33
Meleket wrote:
13 Sep 2024, 11:25
Meleket wrote:
11 May 2022, 09:25
ቤነገራችን ላይ ግጥሙ፡ ለ'ጋዜጠኛው ቴድሮስ ጸጋዬ" ወልጋዳ ምልከታ የተገጠመ ነበር፡ እስቲ ኣጣጥሙ፡ በኤርትራዊ ኣማርኛ የተጣፈ ነው! :mrgreen:
Meleket wrote:
11 May 2022, 04:23
'በአንከላኛ'ና በከበደ ሚካኤልኛ የገጠምነውን እናጋራ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። "ኣንከላኛ' ደግሞ ምንኛ ነው እንዳትሉ! :mrgreen:
Meleket wrote:
12 Aug 2018, 08:53
ርእዮት - ግርድፍ ግጥም

አንድ እናት ነበረች ልጆች የነበሯት፣
እጅግ ውብ የሆነች እንከን የማይወጣት።

ያለም ነገር ሆኖ እርጅና መጥቶ፣
ልጆች ስታሳድግ እንግልቷ በዝቶ፣
ብዙ ስቃይ አየች የማያልቅ ተወርቶ።
ግን አልሰነፈችም በማድረጓ ጥረት፣
አንድ ልጇን ዳረች መርቃ በክብረት።

ያለም ነገር ሆኖ የጤናዋ ጉዳይ፣
ለልጆቿ ስትል እሷ ስትሰቃይ፣
ከእለት ወደ እለት መሻሻል ሳያሳይ፣
ከእርጅናው ጋራ አባሰባት ስቃይ።

እንዲህ እንዲህም ሲል ያይኗን ብርሃን አጣች፣
ልጆቿ ሲያብቡ እሷ ግን ገረጣች።
ይህንን ታዝባ ባለ ትዳር ልጇ፣
እናቷን መርዳቷን አረገች ግዳጇ።

እናቷን ስትመራ በመንገዷ ሁሉ፣
ለመመረቅ ነበር እንዲያው በጥቅሉ።

እናትየዋ ግን የእናት ነገር ሆኖ፣
ልጆቿን ስትመግብ አንድ ልጇ ጨክኖ፣
አንድ ሃሳብ አመጣ አወላግዶ አጢኖ፣
ካወቅኩ ባይ ልጇ በቀረበ ‘መላ’፣
በሰላሙ ሰፈር ተንኮል እንዲያጠላ፣
እንዲህ እንዲህ አላት በነገር ፍተላ።

“ልጄ በመሆንሽ ራሴ የወለድኩሽ፣
የምልሽን ስሚ እንዲያው አትቅለስለሽ።

ይህ ያይኖችሽ ብርሃን ከኔ የወረስሽው፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ ቁርጥሽን እወቂው።

ይህን ሃቅ አጢነሽ ተንግዲህ በኋላ፣
ማንኛውም ስራሽ እኔን ማያጉላላ፣
እንዲሆን አድርጊ እኛ እንዳንጣላ!

እንዲያውም ይህ ዓይንሽ ሁሉን ምታይበት፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ እንዳሻኝ ምሆንበት፣”
ብላ እንድታስብ ያቺ ምስኪን እናት፣
አወቅኩ ባይ ልጇ በአንክሮ መከራት።

ባለትዳር ልጇ የመላች በትዕግስት፣
መረጠች ለናቷ እውነቱን ልትነግራት።

“እማማ እናታለም ወላጄ ውቢቱ፣
ይህን ሃቅ ስሚኝ እንዲያው ባዛኝቱ።

ድሮ ዓይኖች ነበሩሽ ምን ምን የመሰሉ፣
“በፌደሬሽን” ወቅት ላንቺ የተተከሉ፣

ያያቸውን ሁሉ እንዲያው ሚያማልሉ፣
እኛን በማሳደግ ውለታን የዋሉ።

የአምላክ ስራ ሆኖ ስለጠፉ አሁን፣
እንዴት ታልሚያለሽ ጌታን ለመኮነን?

ባለም አደባባይ ክሶችን መስርተሽ፣
እንዴት ልትዘልቂው ነው ፈጣሪን ሞግተሽ?
ያይንሽንስ ብርሃን እንዴት ልትመልሽ?

የተጠቃሚነት መብቱ ይገባኛል፣
የራስ ባልሆነ ዓይን እንዴትስ ይቻላል?


ይልቅ ጠባይ አርገሽ ከኔ ከልጅሽ ጋር፣
በብርሃኔ ልምራሽ እንኑር በፍቅር።

አንቺም ዋዛ አይደለሽ ብዙ ሃብቶች አሉሽ፣
ይህ የዓይኔ ብርሃን አይቀርም ሳይጠቅምሽ።

እንዲህ እንዲህ አርገን እየተጠቃቀምን፣
በፍቅር መኖር ነው ለኛ የሚበጀን።

ያለሽ አንድ አማራጭ ዓይንሽ እንዲበራ፣
እሱ ራሱ መጥቶ ተዓምር ካልሰራ፣
ሌላ መላ የለም ሚሆን በፉከራ፣
ጭቃውን አብኩቶ አይንሽን ነካክቶ፣
እሱ ካልዳበሰሽ ተሰማይ መጥቶ፣
የትም አያደርስሽ ሽለላ ቀረርቶ።


ተከባብሮ መኖር እያለ አንድ መላ፣
ተጋግዞ መኖርም እያለ አንድ መላ፣
እስቲ ዕድል አንስጠው ተንኮል ለሚያሰላ፣
አዋቂ ነኝ ለሚል ለማንም ቱልቱላ፣
ሌተቀን ለሚያልም እኛኑ ሊያባላ።


እኔና አንቺ ሁሌም ከልብ ስንፋቀር፣
እምንሰራው ሁሉ እንደሚሆን ተአምር፣
መሰሪ ዲያብሎስን እንደሚያደርግ ኩምትር፣
በምን አማርኛ ለመግለጽ ልሞክር!!!!!!!
ፍንጭ፦ ይህ ጽሑፍ ዓላማው፣ የሰው ገንዘብ ሚመኝን ክፉ መካሪ መሰሪን ለመገሰጽ ነው።

Prisoners of war in Assab, Eritrea [Photo by Habtom Berhe, from the Greg Marinovich collection]

Digital Weyane
Member+
Posts: 9822
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: “የመደመር መንግሥት” በዋነኛነት የሚያስፈልገው የቱ ነው?

Post by Digital Weyane » 20 Sep 2025, 04:35

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የአሰብ ወደብ ባለቤት እንድትሆን ለማድረግ መከፈል የሚገባውን መስዋእትነት እንከፍላለን። ማን ይፈራል ሞት፣ ማን ይፈራል፣ ለኤምሬትስ ሲባል!! :roll: :roll:

Post Reply