Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4772
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

Post by Meleket » 09 Sep 2025, 10:24

ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

መለስ ወዲ ኣለማሽ ኣባይን ባይገድብ
ኢትዮጵያ ነበረች ዓይን-ዬሌላት ቅንድብ:mrgreen:

ኢንጅነር ስመኘዉ የዓባዩ መሃንዲስ
የጎንደሩ ቅዱስ፡
መስቀል አደባባይ በመንፈስ ሚቀደስ

ለኒህ ሁለት ፈርጦች የምድረ ኢጦብያ፡
ስላስመሰከሩ ያላቸውን ሙያ፡
ልዑል ክብር ኣላት ሃገረ ኤርትርያ!

በወዲ ዜናዊ "ተስሎ ተጠርቦ"፡
ሕወሓት ወያኔ "ቦተሊካ ጠግቦ"፡
ምድረ ኢትዮጵያዊን በጥበብ ሰብስቦ፡
በኢሕኣዴግ ዘመን አባይን ገድቦ፡
ግሩም ተግባር ሰርቷል "ለሃገሩ" አስቦ።


እኛ ኤርትራዉያን የመሃል እና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር፡ ለዓዲዃላዋ የእታችን ልጅና የሴራ ቦተሊካ ሰለባ ለሆነው ለጎንደሬው መሃንዲስ የቋጠርንላቸው ስንኝ መሆኑ ነው።

ግእዛዊው 2018 ዓ.ም. የሰላም የተመስገንና የጸጋ ዘመን ይሆን ዘንድ ተመኝተናል ለመላው የዓለም ህዝብ!

ተጣፈ "በዘመነ ጽምዶ" - በዘመነ ማርቆስ ዋዜማ





Axumezana
Senior Member
Posts: 18354
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

Post by Axumezana » 09 Sep 2025, 13:21

Meleket ዛሬ እውነት ተናገርክ!

almaze
Member+
Posts: 8341
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

Post by almaze » 09 Sep 2025, 15:19

ባባ ኢሱም አልሰነፉም ያቅሚቲን አስመርቀዋል give credit where credit is due


Zmeselo
Senior Member+
Posts: 36747
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

Re: ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

Post by Zmeselo » 09 Sep 2025, 15:53

ኣየ ናይ ሕርካም [ deleted ]!

Please wait, video is loading...
almaze wrote:
09 Sep 2025, 15:19
ባባ ኢሱም አልሰነፉም ያቅሚቲን አስመርቀዋል give credit where credit is due


Roha
Member
Posts: 2180
Joined: 17 Feb 2011, 00:38

Re: ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

Post by Roha » 09 Sep 2025, 19:43

ለተወዳጁ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ፡
ብኤርትራዊው ጨዋነት እንኳን ደስ ኣላቹህ ፡ ለኛም ለኣፍሪካውያን ሁሉ ኩራት ናቹህ።
በዚህ ኣጋጣሚ በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨሪሲቲ ከኔ ኣብሮ ተማሪ ለነበረው ለኢንጂኔር ስሜ በቀለ ፡ ለቤተሰቦቹ ፡ ለቅርብ የዩንቨሪሲቲ ጓደኞቹ ለኢንጂኔር ከዲር ፡ ለቴድሮስ እስታቲስቲክስና ሌሎች ሁሉ ፡ ወዳጃችን ጓደኛችን ስሜ በኣባይ ወንዝ ላስቀመጠው ዘልኣለማዊ ኣሸራ ያለኝን ኣድናቆት እገልጻለሁኝ።
በዛች ጠባብ የመኝታ ክፍላችን ኣለፍ ኣለፍ ብለን ስለ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብናወራም ፡ ኣንድ ግዜ ትምህርታችን ይህን ዘለቆ የኣፍሪካና የኣረቡ ዓለም ፖለቲካ ልያንጋ ይችላል ፡ የኛም ትውልድ ሚና ይኖርበታል ብየ ብሕልሜም ኣስቤውም ኣላቅም።
እርግጥ በመጀመርያ ኣመታችን ከስሜ ጋር ስናወራ ፡ ከኛ ከዩኒቨርሲቲ በፊት በኮተቤ በሚገኘው የመብራት ሃይል ኮሌጅ ምሩቅ መሆኑን ኣስታውሳለሁኝ።
ኣንዱ ከክላስሜታችን ከዛች ከታላቋና ገናናዋ ከጎንደር ከተማ ተነስቶ ፡ ይህን ያህል ሃላፊነት ተሽክሞ በዚህ ታሪካዊ ታላቅ የሕዳሴ ግድብ መሪ ቀያሽ መሃዲስ ሆኖ በታሪክ መዛግብት ሲታወስ የሚሰማኝ ከፍተኛ ኩራት ነው።።
ስራው ተጠናቅቀዋልና ፡ የኛው ስሜ በሰላም ዕረፍ።

ካንዱ የኣስመራው ክላስመይቲህ




Meleket wrote:
09 Sep 2025, 10:24
ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

መለስ ወዲ ኣለማሽ ኣባይን ባይገድብ
ኢትዮጵያ ነበረች ዓይን-ዬሌላት ቅንድብ:mrgreen:

ኢንጅነር ስመኘዉ የዓባዩ መሃንዲስ
የጎንደሩ ቅዱስ፡
መስቀል አደባባይ በመንፈስ ሚቀደስ

ለኒህ ሁለት ፈርጦች የምድረ ኢጦብያ፡
ስላስመሰከሩ ያላቸውን ሙያ፡
ልዑል ክብር ኣላት ሃገረ ኤርትርያ!

በወዲ ዜናዊ "ተስሎ ተጠርቦ"፡
ሕወሓት ወያኔ "ቦተሊካ ጠግቦ"፡
ምድረ ኢትዮጵያዊን በጥበብ ሰብስቦ፡
በኢሕኣዴግ ዘመን አባይን ገድቦ፡
ግሩም ተግባር ሰርቷል "ለሃገሩ" አስቦ።


እኛ ኤርትራዉያን የመሃል እና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር፡ ለዓዲዃላዋ የእታችን ልጅና የሴራ ቦተሊካ ሰለባ ለሆነው ለጎንደሬው መሃንዲስ የቋጠርንላቸው ስንኝ መሆኑ ነው።

ግእዛዊው 2018 ዓ.ም. የሰላም የተመስገንና የጸጋ ዘመን ይሆን ዘንድ ተመኝተናል ለመላው የዓለም ህዝብ!

ተጣፈ "በዘመነ ጽምዶ" - በዘመነ ማርቆስ ዋዜማ





Meleket
Member
Posts: 4772
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]

Post by Meleket » 10 Sep 2025, 03:35

ወዳጃችን Axumezana እንኳን ደስ ያለህ፡ ትናንት እዉነትን መስማት በመጀመርህ!

ኣብይ ኣሕመድ፡ ዳንኤል ክብረት፡
ያባይን ግድብ መቼ ጀመሩት?
ባለቀ ሰዓት ነው የደረሱት።

ቆርጦ ተነስቶ፡ በእናቱ ወኔ፡
የጀመረውስ ነበር ወያኔ!
ወዲ-ኣለማሽ ሲጀምር ያኔ!

የማክሰኝይቱ የፈላሻዋ የጎንደር ፈርጡ፡
የእሟሆዩዋ ልጅ ያ ልበ ንጡ፡
ለሃገሩ ሲል ደሙን አፍስሶ፡
ዘላለም ኗሪ ልብ ላይ ነግሶ።

ነጭ ባህሩ ሳለው ሓሸንጌ፡
ቀይባሕር ሚመኝ ሆኖ ባለጌ፡

ተመስገን አያውቅ ኣያ ብልጥጌ!

Axumezana wrote:
09 Sep 2025, 13:21
Meleket ዛሬ እውነት ተናገርክ!

Post Reply