Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

BBC:-የደቡብ ትግራይ አስተዳዳሪ የነበሩት ሐፍቱ ኪሮስ ከሥልጣናቸው ከተነሱ በኋላ ወዴት ሄዱ?

Post by Za-Ilmaknun » 29 Aug 2025, 12:22

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞው የደቡብ ትግራይ ዞን አስተዳደርን በመቀየር ሁለት አዳዲስ አመራሮችን መሾሙን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ተፈጥሯል።
ከነሐሴ 18/2017 ዓ.ም. ጀምሮ አቶ ዝናቡ ገ/መድኅን የደቡብ ትግራይ ዞን አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ መሠራጨቱን ተከትሎ የአስተዳደሩን ቢሮ ሰብረው በመግባት ሥራ መጀመራቸው ይነገራል

አቶ ዝናቡ እንደ ጨርጨር እና ሌሎች አካባቢዎች የተካሄዱ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች ሲናገሩ ታይተዋል።

በመድረኮቹም ላይ ተሰብሳቢዎች "አሁንም እኛ አልመረጥንህም። በአፈ ሙዝ አንገዛም" ማለታቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህንን ያሉት በጨርጨር ከተማ በተካሄደው ሕዝባዊ መድረክ ላይ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።

በዚህ ሕዝባዊ መድረክ ላይ አቶ ዝናቡ "ህወሓት ቢቀየም ኖሮ አንድም የሚቀር ሰው አይኖርም ነበር" ሲሉ መናገራቸው በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል።

የቀድሞው የዞኑ አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ከሁለት ወራት በፊት እንዳደረጉት አሁንም "ሕዝባዊ ተቃውሞ" እያዘጋጁ መሆናቸውን ይናገራሉ።

"በሥራ ላይ ነበርን፣ ካቢኔው ሥራ ላይ ነበር፣ ሁሉም ወረዳ ሥራ ላይ ነበር፣ የዞኑ ፖሊስ አስተዳደር እና የሚሊሺያ አስተዳደሮች ከአንድ ቀን በፊት ተጠርተው እንደነበር እናውቃለን" ብለዋል።

በአካባቢው በነበሩበት ወቅት ቢሮውን በኃይል ሰብረው እንደገቡም ተናግረዋል።

"አሁንም አካባቢው ላይ ነን። ሥራ ላይ እያለን ነው ሰብረው የገቡት።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cz71xjj53p9o