Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 13 Aug 2025, 11:16

አምቦይቱ ኪያ የአቢይ አህመድ መንግስትን ሊጥል የሚችለው አደጋ ምን እንደ ሆነ ቁልጭ አድርጋ እያስቀመጠቸው ነው ! በፊዳሉ ዘመን ይህን መሰል ጥጋበኞች ነበሩ! በደርግ ዘመን ይህን መሰል ጥጋበኞች ነበሩ! በወያኔ ዘመን ይህን መሰል የሚዘገንኑ ጥጋበኞች ነበሩ ! አሁን በኦሮሞ መንግስት ዘመን ደሞ ይህው ቆሻሻ ዳለቻዎች ተነስተዋል ። አዳምጧት !!!


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 13 Aug 2025, 21:45

የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ ምንጩ ግብጽ ፣ኤርትራ ሲሆኑ ወያኔ ኦነግ ፋኖ ተላላኪዎች ናቸው። አለቀ! ኢትዮጵያ የፕለቲካ ሆነ ኢኮኖሚ ችርግ መፍታት ያልቻልነው ላለፈው 100 አመት ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ የምትሸርበው ሴራ ነው።


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 14 Aug 2025, 21:59




Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 14 Aug 2025, 22:19

ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገር በአርብ ገንዘብ ተከብባ ማስተዳደር የራት ግብዣ አይደለም !! ጨዋታውን በችሎታ መጫወት ደሞ ትልቅ የፖለቲካ መሪነትን ይጠይቃል !


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 15 Aug 2025, 13:35

አቢይ አህመድ አሊ የባህር በር ጥያቄ ማንሳት ማንሳቱ ስህተት ነው ፤ ጥያቄው ትክክል ቢሆንም አቢይ መጥፎ ሰው ስለሆነ እሷ ስላነሳው ጥያቄውን እቃወማለሁ ለሚሉ ፋንዲያ የፖለቲካ ደንቆሮች ፣ ባንዳዎችና የኢትዮጵያ ጠላቶች እዚህ ቢዲዮ ውስጥ ጥቂት መልስ የሚያገኙ ይመስለኛል።


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 16 Aug 2025, 13:07

የቲክ ቶኩን ሆያ ሆዬ ወደ ጎን ትተን ቁም ነገሩ ላይ ስናተኩት ያለው ፖለቲከ ይህን መሰሉ ነው ። አንዱ ኢትዮጵያን ከውስጥ መከፋፈልና ሰላም ማሳጣት፤ በድምበሮቿ ዙሪያ ሁከት መፍጠር (ምሳሌ የሱዳን ትንኮሳ) እና የግብጽ በመላ ቀጠናው የምታቀናብረው ኢትዮጵያን ዴእስታቢልያዝ የማድረግ ዘመቻ ነው ።


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 16 Aug 2025, 16:12

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መፍትሄ ያጣው የመንጋና እረኛ ችግር ፡

በፖለቲካ ሳይንስ ውስጥ የፖለቲካ ልሂቃን የሚባል ሃሳብ አለ። ይህ ቡድን የፖለቲካ ሙያተኛ ሲሆን ገፊ ፍላጎቱ ፣ አላማውና የመኖሩ ም ክ ን ያ ት (1) ስልጣን፣ ሌሎችን መግዛት፤ (2) ገንዘብ ፣ ሃብት፤ (3) ዝና፣ እውቅና፣ ደረጃ፤ እና (4) ክብር ናቸው። ሌሎችን መግዛት ፣ መንግስትን መቆጣጠር፣ ወይም የፖለቲካ መሪነት ዝም ብሎ ማንም ልሂቅ የሚሰራው ሙያ አይደለም። ሕዝብን ፣ አገርን መንግስት የመግዛት ፣ የማስተዳደር ወይም የመምራት ብቃት የተለየ እራሱን የቻለ ክህሎት ነው ። ይህ ክህሎት ደሞ ዝም ብሎ የሚገኝ ሳይሆን እንደ ማንኛው ትልቅ ሙያ በትምህርትና በተሞክሮ ፣ በኤክስፔሪያንስ የሚገኝ ችሎታ ነው ።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቅ ሆኖ ሌሎች ለመግዛት የማይመኝ ጂል እረኛ የለም። ያልተማረ መሃይም ፣ የሁለተኛ ደረጃ ቀለም የቆጠረ ፣ ከፍ ካለም ኮሌጅ ተብዬ መታወቂያ የያዘ ፣ ከፍ ካለም ማንኛው የኢኮኖሚ ፣ የርሻ፣ የህክምና ፣ የድርሰት፣ የምህድስና ፣ የዘፈን፣ የቲያትር ሙያ ብጤ ያለው ሁሉ ሌሎችን ለመግዛት ፣ አገር ለመግዛት ፣ ሕዝብ ለመግዛት በምኞች ተቃጥሎ ልሂቅ የተባለ የፈረስ ስም ይሸለማል። ድሮ ድሮ አንድ ሰው የፖለቲካ ልሂቅ ተብሎ ሌሎችን ለመግዛት ፣ በዚያም ሳቢያ ሃብት ፣ ዝናና ክብር ለማካበት ከገዢ ቤተሰብ ፣ ከመሳፍንት ወገን መወለድ ነበረበት ። ሲቀጥል የዲክታተር ልጅ፣ የፕሬዚዳንት ልጅ፣ የከንቲባ ልጅ ወዘተርፈ መሆን ነበረበት፣ ሲቀጥል በሙያው በፖለቲካና አስተዳደር ሳይንስ የተካነ ፣ በሕግና የሕግ ገዥነት የጠበበ ፣ መብታቸውን በሚያውቁ የነቁ ሕዝብ የተመረጠ ገዢ ሳይሆን አንድን የፖለቲካ ማህበረሰብ የሚመራ የፖለቲካ ልሂቅና የፖለቲካ መሪ መሆን ነበረበት ።

ይህ ሁሉ በሌለበት ኢትዮጵያ የማንም ሥራ አልባ ፣ ቦዘኔ ፣ ጡረታ ወጥቶ ኑሮ የሰለቸው ፣ ኑሮ ከብዶት ገንዘብ የቸገረው ፣ ስኬት ርቆት እውቅና የራቀው ጃልና ጂል እዚም እዛም ሌሎችን ለመግዛት እዚም እዛም የራሱን መንጋ ለመሰብሰብ ሲጋጋጥ እንደማስተዋል የሚያስገርም ነገር የለም ። ለመሆኑ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቅ ማለት ምን ማለት ነው? ማነው የፖለቲካ ልሂቅ? ምን ስለሆነ ምን ስላደረገና ምን ስለ ሚያደርግ ነው የፖለቲካ ልሂቅ የተባለው? የሚባለው?

ወይስ የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ መንጋ ስለሆነ (ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ስላልሆነ) ማንኛውም የፖለቲካ እረኛ ተነስቶ ስልጣን ፈላጊ ልሂቅ ነኝ ፣ሌሎችን መግዛት አምሮኛ ብሎ ቲክ ቶክ ላይ ስለወጣ?
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 17 Aug 2025, 17:06

በአንድ ቃል መንግስት መገልበጥ የራት ግብዣ አይደለም!

Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 19 Aug 2025, 13:51

SO WHAT EVER HAPPENED TO JAWAR-OLF-FANO - TPLF - ERITREA- EGYPT ORGANIZED REGIME CHANGE IN ETHIOPIA?????? 3.3 MILLION MEMBERS OF ABIY REGIME ARE OUT IN THE STREET DEMANDING REGIME CHANGE!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 19 Aug 2025, 22:10

በኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ላይ መፈንቅለ መንግስት ማድረግ አይቻልም ። መንግስትን የማይፈልጉና የሚቃወሙ ወታደሮች እየከዱ መውጣት ይችላሉ ። ዛሬ እንዲያውም የመንግስት ደሞች በወር 6 ሺ እስከ 40 ሺ በደረሰበት ሰዓት ያበደ ወታደር ነው መፈንቅል ሞክሮ መሞት የሚመርጥ!!!


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 21 Aug 2025, 15:25


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 24 Aug 2025, 17:48

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 25 Aug 2025, 15:07

THE SAGA OF WISHFUL DIASPORA OR POLITICAL SOAP OPERA!

Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 31 Aug 2025, 14:35


Horus
Senior Member+
Posts: 39812
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: The ABC of Regime Change in Ethiopia

Post by Horus » 21 Sep 2025, 00:25

ከጥቂት ሳምንታት በፊት THE ABC OF REGIME CHANGE በሚለው ሃረጌ በፖለቲካ ሳይንስ ውስጥ 4 አይነት መፈንቅለ መንግስቶች እንዳሉ ጥቅሼ ነበር ። በዚያ ሃረድ ውስጥ ድርጅታዊ ፣ ማህበረሰባዊና ግለሰባዊ መፈንቅለ መንግስት ሊኖር የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ ጠቅሼ ነበር። አራተኛው መፈንቅል ኮርፖሬታዊ መፈንቅል ይባላል። ይህ የሚሆነው ወታደሩ በራሱ ውስጣዊ ብሶት ምክኛት የሚደረግ መፈንቅል ነው ። ማለትም ወታደሩ የሚያስፈልጉት ትጥቅና ስንቅ ሲያጣ ፣ የደሞዝ፣ የዝውውርና እረፍት ችግር ሲጠነክርበትና በየእርከኑ መኖር ያለበት ሹመትና እድገት ሲጓደልና ኢፍትሃዊ ሲሆን ወታደሩ ለራሱ ውስጣዊ ጥቅም ሲል የሚመታው መፈንቅል ነው። የአቢይ መንግስት ዛሬ ያደረገው የጄኔሪአሎች ሹመት ይህን የኮርፖሬት መፈንቅለ መንግስት እንዳይኖር የሚያደርግ እርምጃ ነው!

Post Reply