Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Post
by Za-Ilmaknun » 12 Aug 2025, 12:56

እየውልኽ ዛሬ የ ጅጅጋው ሙስጠፌ መሃመድ ቤተሰቡን ከ ሃገር አስወጣ የሚለውን ሰምተን ሳንጨርስ፣ በ እረፍት እና ህክምና ሰበብ የ ኦህዴድ ብልጥግና ሰዎች በብዛት እየኮበለሉ ስለመሆኑ በሰፊው ተዘገበ፣፣
የ ብአዴን ገልቱዎች ለ አየር ጉዞም ስለማይበቁ፣ ከየወረዳው ወደ ዞን ከተሞች ከ ዞን ከተሞች ወደ አዲስ አበባ በ እግርም በ ህዝብ መጓጓዣም እየተመሙ ይገኛሉ፣ አሊዶሮ ላይ በ ኦህዴድ ሸኔ ተይዘው ካልታረዱ፣፣
የመፍረሱ እና መደርመሱ ስንጥቃት እድሜ ከ ብልጥግና እድሜ እኩል ቢሆንም፣ አሁን ላይ የ ፋኖው ድለቃ ግን ኦህዴድን በድዱ እንዲገለፍጥ እያስገደደው ይመስላል፣፣ እነ ጭሎ አፋቸው ተከፍቶ እየጎረሱ ያሉትን ዳረጎት ሳያጣጥሙ፣ ነገሩ ሁሉ ፣ በ አናቱ መደፋቱ ቢያስቆዝምም፣ ነገ ደጋፊ ሆነው በመከሰት፣ ካንተ በላይ የለውጡ ሞተር ነን ብልው ሲውተረተሩ ብታይ እንዳትገረም፣፣
ለማንኛም ፣ አመለኛው ጎጄ ዛሬ ደሞ አንቶኖቩን ወደ አመድ ቀይሮልሃል! ሁለት በል እንግዲህ፣ ትህነግ ከ ሰማይ ካወረደው ፣ C-130 ጋር ሲደመር፣፣ እህሳ የጁላ እንበሶች ምን ትሉ?

♂️
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Post
by Za-Ilmaknun » 12 Aug 2025, 13:28
ሰበር የድል ዜና !!
ማርሸት ፀሃይ እንደዘገበው፣-
1/ የአማራ ፋኖ በጎጃም ከቀናት በፊት በከባድ ማጥቃት የአረመኔውን አገዛዝ ደምስሶ ተቆጣጥሯት የነበረችውን የጃዊ ወረዳ ዋና ከተማ ፈንድቃ ከተማን ተቆጣጥሯል ።
ከተማዋን ለቀናት ተቆጣጥሮ የነበረውን የአረመኔ አገዛዝ ሰራዊት ድባቅ በመምታት ፈንድቃን በቁጥጥር ስር አውሏል ።
2/ የአማራ ፋኖ በጎጃም ዘጠነኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድ በሁለት ግንባር ባደረገው ማጥቃት በርካታ ቁጥር ያለው የአረመኔው አገዛዝ ተደምስሷል ።
በዚህ ግንባር የእጅ በእጅ ውጊያ የተደረገ ሲሆን ክላሽንኮቭ መሳሪያዎች ተማርከዋል ።
ከቀናት በፊት ራሱን የወሎ ጠቅላይ ግዛት ብሎ የሚጠራውን ሐይል እስከ ደቡብ ወሎ ደንቆሮ ጫካ ድረስ ያባረረው ብርጌዱ በዛሬው ዕለት ታላቅ ጀብዱ ተፈጽሟል ።
3/ ሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር የየቦቅላ አባይ ብርጌድ ፣ የደጅ አዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ እንዲሁም የራሱ የፈጠራ ውጤት በሆነው የዘሪሁን 13 ምድብ የአረመኔውን ሰራዊት አፈር ድሜ አስገብተውታል።ነበልባሎቹ የቅጥረኛውን ሀይል እጅና እግሩን እየቆራረጡ በየሆስፒታሉ አስተኝተውታል።
በዚህ ከፍተኛ ትንቅንቅ በተደረገበት ውጊያ ክንደ ነበልባሎቹ በሚገርም መናበብ የአረመኔውን አገዛዝ ሰራዊት እግሬ አውጪኝ ያሯሯጡት ሲሆን የአድማ ብተና አመራሩ ጀርባውን ተነድሎ ህክምና ደ.ማ ሆስፒታል ገብቷል።
ይህ ውጊያ የተደረገው የቦቅላ መገንጠያ ላይ ሲሆን ከ25በላይ የጠላት ሀይል ሲደመሰስ ከ14 በላይ ቁስለኛ ሆኗል።ውጊያው በየቦቅላ አባይ ብርጌድ ጦር አዛዥና በተድላ ጓሉ ብርጌድ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ተመርቷል።
በሌላ ዜና በዚህ ውጊያ መሐል 2የአገዛዙ አሽከር የነበሩ የፖሊስ አባላት ተድላ ጓሉ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
4/ የጣናው መብረቅ ብርጌድ ተወርዋሪ ኮማንዶ በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ አንቶኖቭ አውሮፕላን በዱሽቃ በመምታት ከጥቅም ውጭ አድርጓል ።
የአማራ ፋኖ በጎጃም ወደ ባህርዳር ከተማ እና አካባቢው የሚያደርገው ማጥቃት ጨምሯል ።
የአረመኔውን አገዛዝ ሰራዊት እየደመሰሰ ይገኛል ።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Post
by Za-Ilmaknun » 12 Aug 2025, 13:46
ሽሽቱ ከ ኦህዴድ ብልፅግና : ቢላዋ ነው ይልኻል! የ ፋኖው ሙቀት እና ግለት እየናረ፣ የ ኦህዴድ መንጋ ሲሸበር፣ አቡጡጡም ጥለዛና ድለዛውን በራሱ ግሪሳ ላይ