Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39796
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የሰው ልጅ የሚኖረው በቦታውና በሃሳቡ ልክ ነው ፡ ሰውንም ባህልንም የሚፈጥረው ደሞ ቦታ ነው፡

Post by Horus » 04 Aug 2025, 16:32

ዛሬ ላይ ብዙ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች ግራ ተጋብተዋል ። ብዙ ያልጠበቁትና ያልለመዱት ነገር በማየታቸው ። ብዙ ብዙ ኢትዮጵያውያኖች ከችግር ፣ ከቆሻሻ፣ ከድህነት፣ ከጠብና ጦርነት ጋር በጣም በጣም የተላመዱ ሕዝብ ስለሆኑ ለውጥ ፣ጽዳት፣ ሃብት፣ ሰላምና መልካም ነገር አይፈጠርም ብለው ስለደመደሙ ይህን እምነታቸውን የሚሟገት ፣ የሚሽር ወይም የሚለወጥ ክስተት ሲከሰት የመጀመሪያ ምላሻቸው ጥርጣሬና ብሎም የሚያዩትን መካድ ነው። ይህ በሳይኮሎጂ ሳይንስ የተረጋገጠ ነው ።

ነገር ግን አንድ ለውጥ በተለይ የቦታ ለውጥ የሰው ልጅን ሳይወድ በግድ ይለውጠዋል ። የሰው ባህሪ የሚፈጠረውም ፣ በየቀኑ የሚከወነው፣ ብሎም የሚለወጠውም በቦታና ግዜ ውስጥ ነው ። ግዜ ያለ ቦታ ህልውና የለውም ። ከቦታ ውጭ የሚኖር ፣ የሚሰራ ምንም ነገር የለም ። የሰው ልጅ ሕይወት የቆመው በቦታ ላይ ነው ። ቦታ ሲለወጥ ሁሉም ነገር ይለወጣል ፣ አንዳንዱ በቅጽበት ፣ የቀረው በዝግመት።

ስለዚህ ዛሬ አዲስ አበባ እንደ ቦታ መለወጧ ያለ ምንም ጥርጥር የሕዝቦቿን ባህሪ ፣ ባህል፣ ሃሳብ፣ አኗኗር ፣ ራዕይ ፣ አላማና ፍላጎት ሁሉ ይለውጣል፤ አንዳንዱን በቅጽበት የቀረቱን በዝግመት ። ለምሳሌ ድህነትን እንውሰድ። ያዲስ አበባ መሰረተ ልማትና እቅድ ማበብ በቅጽበት የነዋሪዎቿን ድህነት አይለውጥም ። ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ በዉጫዊው እደገትና ዉበት ባንድ በኩልና በዉስጣዊው የዜጋዎች ኑሮ ዝቅተኘትና ድህነት በሌላ በኩል እጅግ ያገጠጠ ፣ እግጅ ያፈጠጠ ልዩነትና መጣረስ ይፈጥራል ፣ ፈጥሯልም።

ይህ ግዙፍ ቅራኔ ነው እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ስር ነቀል ግለሰባዊና ማህበረሰባዊ ንቃተ ሕሊናና ፍጭት የሚያስነሳው ። ቦታው ሃብታም ስለሆነ ድህነትን አልቀበልም ማለት ይጀምራል ። ድህነት የሚያብብበት ቦታ አጣ ማለት ነው። በዚህ በተለወጠው ቦታ እያንዳንዱ ግለሰብ እንዴት እንደ ሚኖር በግድ እጅግ በግድ ማሰብ ይጀምራል ። ማህበረሰብም ፣ መንግስትም በዚህ በተለወጠ ቦታ ውስጥ ድህነትን እያንቆላጰሰ መሸጥ የማችልበት ሁኔታ ይፈጠራል ፣ ተፈጥሯል ።

ስለዚህ እርግጥ አዲስ አበባ በጣም ሰፊና ከግማሹ የላቀው ሰሜን አዲሳባ ፣ ምራብ አዲሳባ ፣ ደቡብ ምራብ አዲሳና ገና የኮሪደር ልማት ወስጥ ለመግባት አመታት ቢወስዱም ከወዲሁ ያሁኑ የቦታ ለውጥ መላውን የከተማው ነዋሪ ሕይወት አሁን ባለበት እንደ ማይቀጥል እያረጋገጠ ነው። አንድ ምሳሌ ብቻ እንውሰድ፣ ልመና!

የልመና ሕገ ወጥ መደረግ አንድ ግዙፍ ያኗኗርና የባህል ለውጥ አምጥቷል ፣ ያመጣል ፣ በግድ። ሰዎች ስለ ቆሻሻ ያላቸው አመለካትንም እንዲሁ። ሌሎች አንድ ሺ የድህነት አይነቶችን መጥቀስ ይቻላል። ሁሉም አሁን ጥያቄ ላይ ይገባሉ። በሁሉም ላይ ሰው ሁሉ መፍትሄ መፈለግ ይጀምራል ።

በቃ አንድ ማህበረሰብ ስር ነቀል የግልና የማህበር ለወጥ የሚፈጥረው ይህን መሰል ውጥረት ሲጋፈጥ ነው ። የሰው ልጅ ለማንኛውም ችግር መፍትሄ የመፍጠር ችሎታ አለው ። ይህን ችሎታውን እንዲቀሰቅስ የሚያስነሳው አንዱ ትልቁ ገፊ ምክኛት የቦታ መለወጥ ነው።

sesame
Member+
Posts: 7894
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: የሰው ልጅ የሚኖረው በቦታውና በሃሳቡ ልክ ነው ፡ ሰውንም ባህልንም የሚፈጥረው ደሞ ቦታ ነው፡

Post by sesame » 04 Aug 2025, 18:11

Horsey,

I just found out that the population of Addis is 3.5million, less that 2.67% of people of Ethiopia. What an insult to the unfortunate people of that unfortunate nation that its idiotic leaders are not only wasting enornmous scarce resourseces on useless projects but that dumbitos like you expect them to be grateful!

https://en.wikipedia.org/wiki/List_of_c ... nhabitants

Selam/
Senior Member
Posts: 16864
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የሰው ልጅ የሚኖረው በቦታውና በሃሳቡ ልክ ነው ፡ ሰውንም ባህልንም የሚፈጥረው ደሞ ቦታ ነው፡

Post by Selam/ » 04 Aug 2025, 18:13

ቱስ ቱስ ጭልፊቱ aka ዲዲቲ

ለምን አንድ ፊቱን ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ስር እናደርጋለን ብለህ ወደ አሲምባ ዘመን አትመልሰንም?

አንተ ለሰላሳ ዓመት ሰሜን አሜሪካ ኖረህም፣ አስተሳሰብህ ዓብዮተኛነትና ጎጠኝነት ላይ ተቀርቅሮ ነው የቀረው። በአንተ አመለካከት፣ አንድ አውሮፓዊ ለሰላሳ አመት ወልቂጤ ከተማ ውስጥ አንተን ተክቶ ቢኖር፣ ሹካውንና መጫሚያውን ጥሎ በምላጭ ጥሬ ስጋ እየቀነጠበና ሊስትሮ እየጠረገ ይኖር ነበር።

Horus wrote:
04 Aug 2025, 16:32
ዛሬ ላይ ብዙ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች ግራ ተጋብተዋል ። ብዙ ያልጠበቁትና ያልለመዱት ነገር በማየታቸው ። ብዙ ብዙ ኢትዮጵያውያኖች ከችግር ፣ ከቆሻሻ፣ ከድህነት፣ ከጠብና ጦርነት ጋር በጣም በጣም የተላመዱ ሕዝብ ስለሆኑ ለውጥ ፣ጽዳት፣ ሃብት፣ ሰላምና መልካም ነገር አይፈጠርም ብለው ስለደመደሙ ይህን እምነታቸውን የሚሟገት ፣ የሚሽር ወይም የሚለወጥ ክስተት ሲከሰት የመጀመሪያ ምላሻቸው ጥርጣሬና ብሎም የሚያዩትን መካድ ነው። ይህ በሳይኮሎጂ ሳይንስ የተረጋገጠ ነው ።

ነገር ግን አንድ ለውጥ በተለይ የቦታ ለውጥ የሰው ልጅን ሳይወድ በግድ ይለውጠዋል ። የሰው ባህሪ የሚፈጠረውም ፣ በየቀኑ የሚከወነው፣ ብሎም የሚለወጠውም በቦታና ግዜ ውስጥ ነው ። ግዜ ያለ ቦታ ህልውና የለውም ። ከቦታ ውጭ የሚኖር ፣ የሚሰራ ምንም ነገር የለም ። የሰው ልጅ ሕይወት የቆመው በቦታ ላይ ነው ። ቦታ ሲለወጥ ሁሉም ነገር ይለወጣል ፣ አንዳንዱ በቅጽበት ፣ የቀረው በዝግመት።

ስለዚህ ዛሬ አዲስ አበባ እንደ ቦታ መለወጧ ያለ ምንም ጥርጥር የሕዝቦቿን ባህሪ ፣ ባህል፣ ሃሳብ፣ አኗኗር ፣ ራዕይ ፣ አላማና ፍላጎት ሁሉ ይለውጣል፤ አንዳንዱን በቅጽበት የቀረቱን በዝግመት ። ለምሳሌ ድህነትን እንውሰድ። ያዲስ አበባ መሰረተ ልማትና እቅድ ማበብ በቅጽበት የነዋሪዎቿን ድህነት አይለውጥም ። ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ በዉጫዊው እደገትና ዉበት ባንድ በኩልና በዉስጣዊው የዜጋዎች ኑሮ ዝቅተኘትና ድህነት በሌላ በኩል እጅግ ያገጠጠ ፣ እግጅ ያፈጠጠ ልዩነትና መጣረስ ይፈጥራል ፣ ፈጥሯልም።

ይህ ግዙፍ ቅራኔ ነው እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ስር ነቀል ግለሰባዊና ማህበረሰባዊ ንቃተ ሕሊናና ፍጭት የሚያስነሳው ። ቦታው ሃብታም ስለሆነ ድህነትን አልቀበልም ማለት ይጀምራል ። ድህነት የሚያብብበት ቦታ አጣ ማለት ነው። በዚህ በተለወጠው ቦታ እያንዳንዱ ግለሰብ እንዴት እንደ ሚኖር በግድ እጅግ በግድ ማሰብ ይጀምራል ። ማህበረሰብም ፣ መንግስትም በዚህ በተለወጠ ቦታ ውስጥ ድህነትን እያንቆላጰሰ መሸጥ የማችልበት ሁኔታ ይፈጠራል ፣ ተፈጥሯል ።

ስለዚህ እርግጥ አዲስ አበባ በጣም ሰፊና ከግማሹ የላቀው ሰሜን አዲሳባ ፣ ምራብ አዲሳባ ፣ ደቡብ ምራብ አዲሳና ገና የኮሪደር ልማት ወስጥ ለመግባት አመታት ቢወስዱም ከወዲሁ ያሁኑ የቦታ ለውጥ መላውን የከተማው ነዋሪ ሕይወት አሁን ባለበት እንደ ማይቀጥል እያረጋገጠ ነው። አንድ ምሳሌ ብቻ እንውሰድ፣ ልመና!

የልመና ሕገ ወጥ መደረግ አንድ ግዙፍ ያኗኗርና የባህል ለውጥ አምጥቷል ፣ ያመጣል ፣ በግድ። ሰዎች ስለ ቆሻሻ ያላቸው አመለካትንም እንዲሁ። ሌሎች አንድ ሺ የድህነት አይነቶችን መጥቀስ ይቻላል። ሁሉም አሁን ጥያቄ ላይ ይገባሉ። በሁሉም ላይ ሰው ሁሉ መፍትሄ መፈለግ ይጀምራል ።

በቃ አንድ ማህበረሰብ ስር ነቀል የግልና የማህበር ለወጥ የሚፈጥረው ይህን መሰል ውጥረት ሲጋፈጥ ነው ። የሰው ልጅ ለማንኛውም ችግር መፍትሄ የመፍጠር ችሎታ አለው ። ይህን ችሎታውን እንዲቀሰቅስ የሚያስነሳው አንዱ ትልቁ ገፊ ምክኛት የቦታ መለወጥ ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 39796
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የሰው ልጅ የሚኖረው በቦታውና በሃሳቡ ልክ ነው ፡ ሰውንም ባህልንም የሚፈጥረው ደሞ ቦታ ነው፡

Post by Horus » 04 Aug 2025, 18:22

sesame wrote:
04 Aug 2025, 18:11
Horsey,

I just found out that the population of Addis is 3.5million, less that 2.67% of people of Ethiopia. What an insult to the unfortunate people of that unfortunate nation that its idiotic leaders are not only wasting enornmous scarce resourseces on useless projects but that dumbitos like you expect them to be grateful!

https://en.wikipedia.org/wiki/List_of_c ... nhabitants
Jimma;
አስመራን ይልቃል!

Post Reply