Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Meleket
- Member
- Posts: 4535
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 20 May 2025, 05:58
ሰሞንኛዉ ኤርትራዊ ግጥም [ገብቶ ወጣ]
ፋሲል የኔዓለም ገብቶ ወጣ፡
መሳይ መኮንን ገብቶ ወጣ፡
ሲሳይ ኣጌና ገብቶ ወጣ፡
ኤልያስ ክፍሌ ገብቶ ወጣ፡
ሞላ ኣስገዶም ገብቶ ወጣ፡
ብርሃኑ ነጋ ገብቶ ወጣ፡
አንዳርጋቸው ገብቶ ወጣ፡
ኣብዪ ኣሕመድ ገብቶ ወጣ፡
ብርሃነ ዋጣ ገብቶ ወጣ፡
ስታሊን ገረላሰ ገብቶ ወጣ፡
ለኛ የገረመን የኤርትራዉያኖች ዕጣ፡
ሲጥፉ የነበሩት በጋዜጣ፡
ኣማኑኤል ኣስራት መቼ ይሆን ወደ መድረኽ የሚወጣ፡
ማቴዎስ ሃብተኣብስ መቼ ይሆን ወደ መድረኽ የሚወጣ፡
ስዩም ጸሃዬ መቼ ይሆን ወደ መድረኽ የሚወጣ፡
እስከ መቼ ያቺ እውነት ተደፍጥጣ፡
ትኖራለች እጉድጓድ ውስጥ ተቀምጣ?
ይህን ሳይገልጥ ምድረ ሞጥማጣ፡
እዚህ እዛ እየንተንጣጣ፡
ሊዘልብን ሲል “ኣያ ስንዝሮ” እንደ ጦጣ፡
'ወጅድ' ኣልነው የለን ጣጣ፡
ኤርትራኖች ያ ልባችን ስለነጣ!
[በኤርትራ የ34 ዓመት የነጻነት በዓል ምክንያት፡ ዝኽረ የተሰወሩ ኤርትራዉያን ወጣት ጋዜጠኞች!]

-
Meleket
- Member
- Posts: 4535
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 21 May 2025, 10:19
ኣንደኛው ‘ልሒቕ’፡
ኣንደኛው ግን ልቅ፡
ኣንዱ ላገሩ ህዝብ ኣስተባብሮ፡
ኣንዱ እንጣጥ እንጣጥ እንደ ስንዝሮ፡
ኣጥንት ቆጥሮ።
ኣንዱ ለመብቱ ላገሩ ዜጋ፡
ኣንዱ ለወሬ ዝና ፍለጋ፡
ኣንዱ ሲያወራ ኣንዱ ሲፈጋ፡
ኣንደኛው ብስል ኣንደኛው ቀጋ፡
"ስዉራኖቹን" ረስቶ እዚያ ጋ፡
ምላስ ኣሹሎ 'ዜጎቹን' ወጋ፡
ዲማርኼሽንን እያዘናጋ፡
ምላስ ኣሹሎ 'ወንድሙን' ወጋ።
tarik wrote: ↑21 May 2025, 09:02

. .....
-
Axumezana
- Senior Member
- Posts: 17241
- Joined: 27 Jan 2020, 23:15
Post
by Axumezana » 21 May 2025, 10:27
ሃተፍተፍ but I like you named አወል " ስንዝሮ"
-
Meleket
- Member
- Posts: 4535
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 21 May 2025, 10:57
ሃተፍተፍ ቢሆንም ሃተፍተፍ ባይሆንም፡
እዉነት መነገሩ በፍጹም ኣይቀርም፡
ስንዝሮም ስንዝሮ ስንዝሮም ስንዝሮ፡
ኣዅሱም ሃወልቱ ስር ነበር ተገትሮ፡
ዛሬ ጽምዶ ሊለን፡ ያኔ ተደምሮ፡
በሰው ኣምባጓሮ!
Axumezana wrote: ↑21 May 2025, 10:27
ሃተፍተፍ but I like you named አወል " ስንዝሮ"
-
Axumezana
- Senior Member
- Posts: 17241
- Joined: 27 Jan 2020, 23:15
Post
by Axumezana » 21 May 2025, 11:03
I like the above because you passed your message in a concise way ! The more you repeat and make your message longer, I loose interest to read! That is why I called it ሃተፍተፍ!