Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4259
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ታሪካዊቷ “ኣብሪል 13” ተዘክራ ውላለች - ከ157 ኣመታት በፊት መቅደላ አጤ ቴዎድሮስና እንግሊዞች፡

Post by Meleket » 14 Apr 2025, 11:22

ታሪካዊቷ “ኣብሪል 13” ተዘክራ ውላለች - ከ157 ኣመታት በፊት መቅደላ ላይ ኣጤ ቴዎድሮስና እንግሊዞች ተርመስምሰው ነበር።
Battle of Magdala
Sir Robert Napier’s capture, on 13th April 1868, of the Fortress of Magdala, stronghold of the Emperor Theodore III of Abyssinia

Assault on the Kukitber Gate at the Battle of Magdala on 13th April 1868 in the Abyssinian War


ይህቺ ታሪካዊት ዕለት የኤርትራና ኢትዮጵያ የደንብር ብይን ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ የተወሰነባት ዕለትም ነች!
Last edited by Meleket on 15 Apr 2025, 03:10, edited 1 time in total.

Meleket
Member
Posts: 4259
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ታሪካዊዋ “ኣብሪል 13” ተዘክራ ውላለች - ከ157 ኣመታት በፊት መቅደላ አጤ ቴዎድሮስና እንግሊዞች፡

Post by Meleket » 15 Apr 2025, 03:00

ታሪካዊዋን "ኣብሪል 13" ፍጻሜ በግጥም ለማስታወስና ለመዝናናትና ለማዝናናት ያህል ነው!

ከህንድ ተነስቶ ገሰገሰ እንግሊዝ፣
ከዙላ ተነስቶ ገሰገሰ እንግሊዝ፣
በሰንዓፈ አድርጎ ገሰገሰ እንግሊዝ፣
ያጤ ቴዎድሮስን መንግሥት ሊገዘግዝ፣
እዬተላላከው የትግራዩ በዝብዝ!


ቴዎድሮስን ሊያጋድም ናፕዬር ገሰገሰ፡
ትግራይና ወሎን እያደፈረሰ፡
"የጦቢያን ሰራዊት" እዬገረሰሰ፡
የቋረኛውን ትዕቢት እያስተነፈሰ፡
መቅደላ ኣናቱ ላይ እንግሊዝ ነገሰ፡
ጦብያ ምን ትያለሽ መንግስትሽ ፈረሰ።


ቢያውቀውማ ኖሮ ቀይባህርን ቴዎድሮስ፡
ዙላ ላይ ነበረ እንግሊዝ ሚቃወስ፡
ባህሩ ዳር ነበር ናፒዬር ሚደመሰስ።

ቀይባህርን ቴዎድሮስ ቢያውቀውማ ኖሮ፡
ናፒየርና ጭፍራውን ባህሩ ውስጥ ነካክሮ፡
በደመሰሳቸው በክንዱ ደካክሮ።

ኣያውቀውም ነበር ቴዎድሮስ ቀይ ባህርን፡
ከጥንት ከጠዋቱ የኛ የሆነውን።


"ዝክረ ኣብሪል 13 1868 ወመቅደላ" ተጣፈ በእኛ በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Meleket
Member
Posts: 4259
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ታሪካዊቷ “ኣብሪል 13” ተዘክራ ውላለች - ከ157 ኣመታት በፊት መቅደላ አጤ ቴዎድሮስና እንግሊዞች፡

Post by Meleket » 15 Apr 2025, 08:18

ከአጤ ቴዎድሮስ ታሪክ ዙርያ እንዲህ ገጥመናል ለመዝናናትም ለማዝናናትም!

ወፈፌ ነበረ ቴዎድሮስ ዓቅሙን የማያውቅ፡
በሲቪል ሰዎች እጅ ሰንሰለት የሚያጠልቅ፡
መድፍ ስሩ ብሎ የሰው ልብ የሚያወልቅ።
በካህናት እጆች ሰንሰለት የሚያጠልቅ፡
እንደኔ ኣመኑ ብሎ የሰው ልብ የሚያደርቅ።


ወፈፍ ያደርገዋል ቴዎድሮስ ህመም ኣለው፡
በሃይማኖት ሽፋን ስንቱን የገደለው።

ትመስክር መቅደላ፡ ወሎም ትመስክር፡
የብጹዕ ገብረሚካኤልን ታሪክ ትናገር

ለእምነት ለኪዳኑ ሰው እኮ ይሞታል፡
እምነቱን መስክሮ ገነትን ይወርሳል።

ከአንባገነን ፊትም እውነትን ተናግሮ፡
ሰው እኮ ይኖራል ምድር ላይ ተቀብሮ፡
መንግስተሰማይ ላይ ተንፈላሶ ሰፍሮ።




ብጹዕ ገብረሚካኤል ኣኪሎ (1790 ዲቦ - 1855 ወሎ) እኒህ ነበሩ፡ የኣምባሳደራችን ኣጎት ዘርኣይ ደረስ፡ የገብረሚካኤላውያን ማህበር ብረዚደንት እንደነበሩ፡ ነፍስኄር ደራሲ ተስፋዬ ገብረኣብ ጭምር በመጸሓፋቸው ጠቁመውን አልፈዋል።

የቴዎድሮስ ታሪክ ጠሓፊ ደብተራ ዘነብም በቴዎድሮስ ታሪክ በሚልው መጠሓፋቸው ገጽ ፬ ላይ እንዲህ ኣስፍረውታል። ብዙ የሸዋና የኣዘዞ ካህናት ከኣቡነ ሰላማ ጋር እንደተከራከሩና፡ እምነታቸውን እንዲቀይሩ በማስገደድ በግርፋት እንደተቀጡም ይገልጹና እንዲህ ኣድርገው አንድ ጉዳይ ይጠቁሙናል። ኣስቀድመን ቴዎድሮስ በወሎ አድርጎ ወደ ሸዋ በዘመተበት ወቅት፡ ኣባ ገብረሚካኤል እጃቸውንና እግራቸውን በእግረሙቅ ታስረው ይጋዙ እንደነበሩ ስለምናውቅ፡ ታዲያ በገጽ ፬ “አንዱም ሰው አልገባም ብሎ ከወሎ ሲደርስ ሞተ።” በማለት ደራሲ ደብተራ ዘነበ የገለጿቸው ይህ ሰው ብጹዕ ገብረሚካኤል ኣኪሎ ናቸው ብለን መላ ምታችንን ሰጥተናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

https://en.wikipedia.org/wiki/Gh%C3%A9br%C4%93-Michael
ኦ ኣባታችን ብጹዕ ገብረሚካኤል ለምኑልን!

Post Reply