Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6768
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 26 Mar 2025, 17:48

ይህ ጥያቄ ለረጅም ግዜ ከእኔ ጋር ሰንብቷል።

ቀላል መልሱ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ጠለቅ ስንል ነዉ መልሱ ከባድ የሚሆነዉ።

አንደበተ ርቱዕነት ባህሉ የሆነ ማህበረሰብ ሊኖር ይችላል?

መልሱ ኣዎ ከሆነ እንደዚህ ዐይነት ባህል ማካበት የሚቻለዉ እንዴት ነዉ? እንደዚህ ዐይነት ባህልን ማካበት ምን ያህል ዘመናትን ይወስዳል?

የኢትዮጵያን ስልጣኔ በጥልቅ እናዉቃለን የምትሉ ኢትዮጵያዊያን እስቲ ይህቺን አጭር ጥያቄ በትክክል መልሱ።

Horus
Senior Member+
Posts: 39871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Horus » 26 Mar 2025, 21:06

Naga Tuma wrote:
26 Mar 2025, 17:48
ይህ ጥያቄ ለረጅም ግዜ ከእኔ ጋር ሰንብቷል።

ቀላል መልሱ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ጠለቅ ስንል ነዉ መልሱ ከባድ የሚሆነዉ።

አንደበተ ርቱዕነት ባህሉ የሆነ ማህበረሰብ ሊኖር ይችላል?

መልሱ ኣዎ ከሆነ እንደዚህ ዐይነት ባህል ማካበት የሚቻለዉ እንዴት ነዉ? እንደዚህ ዐይነት ባህልን ማካበት ምን ያህል ዘመናትን ይወስዳል?

የኢትዮጵያን ስልጣኔ በጥልቅ እናዉቃለን የምትሉ ኢትዮጵያዊያን እስቲ ይህቺን አጭር ጥያቄ በትክክል መልሱ።
አንደበተ ርቱዕ ማለት ተናግሮ የሚያሳምን ማለት አይደለም ፤ አንደበተ እውነት ፣ እውነት ተናጋሪ genuine, authentic, truth speaker ማለት ነው። ለምሳሌ በግርዝና ሴራ (ጉርዝ ሽማግሌ) የሚተዳደሩት ጉራጌዎች በጎርደና፣ ጆካ፣ ጉርዳ የሚገዙት ሕዝቦች አንደበተ ርቱዕ በሆኑት ሽማግሎች (ባሊቆች) ቃል ነው የሚገዙት ምክኛቱም እነዚህ ባሊቆች አቀተኘ ስለሆኑ ። አቀተኘ አቅ (ሃቅ) ተናጋሪ ፣ አቅ ፈራጅ ማለት ነው። በፖለቲካ የሚገዙ ሕዝቦች ባብዛኛው በውሸት ነው የሚገዙትና የሚዳኙት ። አንድ ሰው ቃሉ ለምስክርነት ይበቃል ከተባለ አንደበተ ር ቱ ዕ ነው ። አንድ ቀን እንኳ ሲዋሽ የተገኘ ሰው በጉራጌ ባህል ለምስክርነት አይበቃል።

Abere
Senior Member
Posts: 14766
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Abere » 26 Mar 2025, 21:56

Naga Tuma
ጥያቄህን ሆረስ የመለሰልህ ይመስለኛል። ቀለል ባለ አማርኛ - ርቱዕ ማለት ቀጥ ያለ ትክክል ማለት ነው። ለምሳሌ አንድን ጽሁፍ ለማስተካከል እና ለማረም አርታዒ ይፈለጋል። ግድፈት ወይም ስህትተትን ማረም እንደ ማለት።

ፍትህ ወይም ርትዕ እንፈልጋለን ይባላል። ወይም አንድ ሰው በፍርድ ቤት ተከራክሮ ጉዳዩን [ረታ] ይባላል። ረታ (ረ'ተ'ዓ0 ማለት ሀቅኝነቱን አረጋገጠ ማለት።

በዚህ ዘመን ግን አንደበተ ርቱዕ ማለት ቱልቱላ ወሬ ውሸትም ቢሆን ተውሮ የሚሰራ ሊሆን ይችላል። ከአድርባይነት በመነጨ ምክንያት በአነጋገር ስህተትን እንደ እውነት ያሽሞነሙናል። It is called Political correctness. አፈ-ቅቤ ይባላል

Horus
Senior Member+
Posts: 39871
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Horus » 26 Mar 2025, 22:33

Abere wrote:
26 Mar 2025, 21:56
Naga Tuma
ጥያቄህን ሆረስ የመለሰልህ ይመስለኛል። ቀለል ባለ አማርኛ - ርቱዕ ማለት ቀጥ ያለ ትክክል ማለት ነው። ለምሳሌ አንድን ጽሁፍ ለማስተካከል እና ለማረም አርታዒ ይፈለጋል። ግድፈት ወይም ስህትተትን ማረም እንደ ማለት።

ፍትህ ወይም ርትዕ እንፈልጋለን ይባላል። ወይም አንድ ሰው በፍርድ ቤት ተከራክሮ ጉዳዩን [ረታ] ይባላል። ረታ (ረ'ተ'ዓ0 ማለት ሀቅኝነቱን አረጋገጠ ማለት።

በዚህ ዘመን ግን አንደበተ ርቱዕ ማለት ቱልቱላ ወሬ ውሸትም ቢሆን ተውሮ የሚሰራ ሊሆን ይችላል። ከአድርባይነት በመነጨ ምክንያት በአነጋገር ስህተትን እንደ እውነት ያሽሞነሙናል። It is called Political correctness. አፈ-ቅቤ ይባላል
አበረ፣
በትክክል፤ ቴክኒካል ሆንክ አትበለኝና ይህ ቃል ሳንስክሪት (በሂንዱ ቅዱስ ቋንቋ ወይን የህንዶች ግዕዝ) ተመሳሳይ ነው ። እነሱ ዕ አይከቱበትም 'ርት' ሲሉት በላቲን 'ራይት' (rith) ሲሆን ዛሬ right የሚባለው እንግሊዝኛ ነው ። Yes, justice & truth ፍትህና ርትዕ ይሏል። ሃቅ እንደ ወረደ ካረብኛው አንድ ነው። ለምሳሌ እምርታ ቆንጆ ቃል ነው ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6768
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 27 Mar 2025, 05:19

ሆረስ እና አበረ፥

ረታ በሚለዉ ቃል ተስማማን። እዉነት ሆነ ትክክል የሚረታ ነዉ።

ካልተሳሳትኩ አንደበት ስለ አነጋገር ነዉ። ስለ መርታት ችሎታ ነዉ። ስለ አነጋገር ዘዴ ነዉ።

ልጅ ሆኜ አከ ቦረናት ዱቢ ቤከ ሲባል ሰምቻለሁ።

እንደ ቦረና ሰዉ አነጋገር ይችላል ማለት ነዉ።

ከበርካታ ዓመታት በፊት የሚከተለዉ ቪድዮ ኣጋጥሞኝ ሰማሁት።



ሎሬት ፀጋዬ በአንደበተ ርቱዕነቱ ያስደነቀኝ ሰዉ ነዉ ያለዉን ስትሰሙ ምን ማለቱ ነዉ የገባችሁ?

እዚህ ዉስጥ ስለ ወል፣ ዉል (will) ያብራራል።

Abere
Senior Member
Posts: 14766
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Abere » 27 Mar 2025, 10:35

Naga Tuma,
I think you used the Poet Laureate, Tsegaye G/Medhin, in out of context. I am not sure poetic facts are in symmetry with broader facts, in history, geography, anthropology, etc. Poetry echoes more of rhetoric to rhythm with feeling of audience.
Establishing fact requires validating many historical findings and research.


Naga Tuma
Member+
Posts: 6768
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 02 Aug 2025, 16:21

ወደዚህ ርዕስ ኣሁን ተመለስኩኝ።

ኣንድ ግዜ ቦረና ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ባህል አዋቂ እና ጠባቂ የተባለ ሰዉ አሜሪካ መጣ ሲባል ሰምቼ ፈልጌ መሠረታዊ ስለሆኑ ባህላዊ አስተሳሰቦችን ጠየኩት።

ይህ ሰዉ አርገ ዸጌቲ የሚባል ባህላዊ ድርጅት ኣቋቁሞ ይመራ ነበር ሲባል ሰምቻለሁ። አርገ ዸጌቲ እንደ ባህል ሆኖ ሰዉ ማመን ያለበት መጀመርያ በዐይኖቹ ያየዉን፣ ቀጥሎ በጆሮዎቹ የሰማዉን መሆን ኣለበት ብሎ ማስተማር ነዉ። ከተሳሳትኩ የበለጠ የገባቸዉ ልያርሙኝ ይችላሉ።

አርከመኒቆ የተባለ የጥንት ግብጥ መሪ መልዕክት ተልኮልሃል ሲባል ለመጀመርያ ግዜ የተጠየቀዉን መፈጸም ትቶ መልዕክቱን የላከዉን በዐይኖቼ ልየዉ ብሎ የጠየቀ ነዉ ተብሎ ይታወቃል።

ሁለቱ፣ የጥንቱ እና የዚህ ዘመኑ፣ ማየት ማመን ነዉ የተባሉትን ምን እንደኣመሳሰላቸዉ ለታሪክ ተመራማሪዎች መተዉ ይቻላል።

እኔ ባህላዊ ንግግሮቹ ዉስጥ ሶስት ጥልቅ ጽንሰ ሀሳቦችን ኣስተዉያለሁ።

ኣንደኛዉ ስለ ፍትህ ያላቸዉ አስተሳሰብ ነዉ።

ከመገናኘታችን በፊት ጦር ኣጋድሞ ሴረ ወይም ሕግ ማርቀቅ የገዳ ስርዓት መነሻ ወይም ጀነስስ መሆኑን ግልጽ የምያደርግ ፎቶ በአጋጣሚ ኣይቼ ገና እንዳየሁት ጀምሮ ደንቆኛል።

ስለዚህ ከዛ በኋላ ያለዉን የፍትህ ስርዓት እንዴት እንደሆነ ማወቅ ፈለኩኝ።

ኣጭር ጥያቄ ጠየኩት። ሰዉ ወንጀለኛ ነዉ ወይም ዋን ጀላ ፈጸመ ከተባለ እንዴት ነዉ የሚዳኘዉ ብዬ ጠየኩት።

የተሰጠኝ ማብራርይ በጣም ደነቀኝ። ከአሜርካ የፍትህ ስርዓት ቢበልጥ እንጂ የምያንስ ኣይመስለኝም። ስርዓቱ ሀቁ ጋ መድረስ ነዉ። ለዚህ ደግሞ አሜርካ ዉስጥ ያለ መናገር መብት የሚል ዬለዉም። ሀቁ ማለት መፋቅ እንደማለት ነዉ። ምናልባትም ሀቅ የሚለዉ ቃል መሠረት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ኣለኝ።

የሰማሁኝን የፍትህ ሂደት ሆነ ብዬ ጽፌ ነበር። ከተቻለም ዶክመንታሪ ለማሰራት ይሆናል ብዬ ኣስቤ ነበር።

ሁለተኛዉ ስለ ሀይማኖት እና ፖለትካ ለየብቻ መሆንን ጠየኩት። ለዚህም የሰማሁኝ ግልጽ መልስ ሁሌ ይደንቀኛል።

የቃሉ ድርጅት እና የገዳ ድርጅት ለየብቻ መሆናቸዉን ነገረኝ።

ቃሉ አባ ገዳን የመምረጥ ሂደት ዉስጥ ፈጽሞ ኣይገባም፣ ለመሳተፍ ኣይጋበዝም ኣለኝ።

አባ ገዳ ከተመረጠ በኋላ ለሙደ ወይም የተባረከ ነዉ ለማለት ተጋብዞ የሹመቱ የመጨረሻ ኣጽዳቂ ይሆናል ኣለኝ።

ስለዚህም ጽንሰ ሀሳብ ከተሳሳትኩኝ እና የተሻለ የገባቸዉ ልያርሙኝ ይችላሉ።

ሶስተኛዉ ጠይቄ ሳይሆን ዉይይት ዉስጥ ሰምቼ ባልጠበኩት ደረጃ የደነቀኝ ለዉይይት እንደሁኔታዉ ቃላት መርጦ የመናገር ባህል ነዉ።

ምን ሁኔታ ላይ ምን ዐይነት ቃልን ኣለመናገርን ያስተምራል።

ለዚህ ደግሞ ስለ ግጭቶች መፍትሔ ሳይንስ ወይም ስለ ዲፕሎማሲ ትምህርት ኣለን የሚሉ ማጥናት ይችላሉ።

እኔ ባህል እንደዛ ያስተምራል የሚል ያልጠበኩትን ስሰማ ድሮ ፊደል መርጦ መጻፍ ብቻ ሳይሆን ቃልን መርጦ መናገርን የስተምር ነበር ኣስብሎኛል።

የቅኔ ባህልም የሚደነቅ ቢሆንም ምንጩ ምን እንደሆነ ወይም ምን እንደወለደዉ ማብራራት ኣልችልም።

የቅኔ ባህልም አንደበተ ርቱዕነትን ኣምቆ የሚገልጽ ባህላዊ ዘዴ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

እንደ እኔ አስተሳሰብ እነዚህ ሁሉ ሰፊ ጥናት የምያስፈልጋቸዉ የኢትዮጵያ ቅርሶች ናቸዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6768
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አንደበተ ርቱዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 02 Aug 2025, 16:28

Abere wrote:
27 Mar 2025, 10:35
Naga Tuma,
I think you used the Poet Laureate, Tsegaye G/Medhin, in out of context. I am not sure poetic facts are in symmetry with broader facts, in history, geography, anthropology, etc. Poetry echoes more of rhetoric to rhythm with feeling of audience.
Establishing fact requires validating many historical findings and research.

Abere:

I read your comments here today.

May be it is out of context or may be it is contextual. I don’t know for sure.

However, I think that it provides an opportunity for interested social science scholars to study it.

Post Reply