Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4543
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ለቅኝት የተላከችው የኤርትራ ድሮን

Post by Meleket » 12 Mar 2025, 09:54

የኤርትራ የትምህርት ሚኒስትር ባልደረባ የሆነው ፍስሃየ ኪዳነ (ወዲ ፓሊስ) የተባለ ምርጥ ኤርትራዊ ዜጋ በጋዜጣም በድረ ገጽም በትግርኛ ለኤርትራውያን ያጋራዉን፡ ብሮፉርሸር ዘሜ ዘመሰሎም እዚህ የዶለውን viewtopic.php?f=2&t=358567 በኢትዮጵያዉያን ‘ልሒቓን’ ዙርያ ያጠነጠነውን ምርጥ ጽሑፍ ግርድፍ ትርጉም እንሆ። ኢትዮጵያዉያን ‘ልሒቃን’ ኮምኩሙ። :mrgreen:


ኢትዮጵያዉያን 'ልሒቓን' ግን ለምንድን ነው የኤርትራ ልዑላዊነት የማይዋጥላቸው?
ለምንድን'ስ ነው “ቀይ ባህር ” እያሉ ኣሁንም ኣሁንም በቀጣይ የሚያላዝኑት?


ፍስሃየ ኪዳነ (ወዲ ፖሊስ)
ሚኒስትሪ ትምህርቲ @shabait

በዓለማችን ያሉ ሃገሮች የፓለቲካ መስተጋብር ሂደት፡ እርስ በእርስ መተባበርና አንዱ ባንዱ ላያ ተጽዕኖ ማሳደሩ የግድ ነው። በመሆኑም በየትኛውም የዓለማችን ማእዘን የምትገኝ ኣንዲት ሃገር፡ በጋራ ጥቅም ላይ ተምርኩዛ፡ ከሌላ ልዑላዊት ሃገር ጋር፡ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረት መብቷ ነው። ከዚህ ባሻገር በተለይ በጎረቤታም ሃገሮች መካከል የሚኖር ግንኙነቶች፡ መልክኣምድርን፡ ባህልን፡ ቋንቋን፡ ኢኮኖሚን ወይም ቁጠባን እንዲሁም ታሪክን ጭምር ወዘተ ያማከሉ ስለሚሆኑ፡ ይበልጥ የግድ መቀራረብንና መደጋገፍን ይጠይቃሉ።

በማንኛውም የታሪክ ኣጋጣሚ፡ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሊኖር የሚገባው ፓለቲካዊ ዝምድና፡ ከዚህ ታሪካዊ ሓቅ ውጭ ሊሆን ኣይችልም። በሁለቱ ልዑላዉያን ሃገራት መካከል የሚገነባ ፖለቲካዊ ሆነ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትም፡ በአንዲት ቀኝ ገዢ የነበረች (Hegemonic State) እና ተገዢ የነበረች (Diasporic State) መካከል እንደሚደረግ ግንኙነት ሆኖ መመስረት ኣይገባውም። ይልቅስ፡ በዓለም ኣቀፋዊ የሃገራት የግንኙነት መርህ (International Relations) መመራት ይገባዋል። በሌላ ኣባባል፡ በሃገሮች የእርስበርስ ግንኙነት፡

የህዝቦች ዘለቄታዊ ወይም ቋሚ ጥቅም እንጂ፡ ቋሚ ወዳጅ ወይም ጠላት ብሎ ነገር የለም፡

የሚል ስትራቴጂካዊ መርህን ማክበር ይገባዋል።

በአጠቃላይ፡ የሃገሮችን የፖለቲካ ግንኙነት፡ በመንደፍና በመተግበር ረገድ፡ ስልጣን ላይ የተቆናጠጡ ልሂቃን፡ ጤነኛ ኣሊያም ጤነኛ ያልሆነ ግንኙነት ለመመስረት፡ ወሳኝ ሚናና ተጽዕኖ ኣላቸው። ከዚህ ኣኳያ ሲታይ፡ እስከዛሬ ድረስ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው ፖለቲካዊ ግንኙነት
“ቦግ-እልም” (on-off)

የሚል ቦለቲካዊ መርህ የተከተለ ነበር ለማለት ይቻላል።

በተለይም መላዋ ኤርትራ ነጻ ከሆነች ከ1991 ማግስት፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የስልጣኑን ኮረቻ የተቆናጠጡ የፓለቲካ ልሂቃን (Political Elites)፡ የሁለቱ ሃገራት ህዝቦች መልካም ግንኙነትን በማደፍረስና በኣፍራሽ ሚናቸው ተጠያቂዎች ናቸው። የዚህ ምክንያት ደግሞ እነዚህ ኣካላት ልባቸው ሆነ ህሊናቸውን ኣንጽተው ስለማያውቁ ብቻ ነው። ዋነኛው ምክንያት ግን በሁለት ነጥቦች ሊጠቃለል ይችላል።

ኣንደኛው ምክንያት የወያኔዎቹ የኢህኣዴግ ሆነ የብልጽግና መንግስት፡ ኤርትራ ውስጥ እያበበ ባለውና እየተኮሰኮሰ ባደገው

የኤርትራ ህዝብ የኣንድነት መንፈስ፡ የአመራር ኣካላት ውህደትና ችሎታ እንዲሁም፡ የሃገር ደህንነትና የመከላከያ ሃይሎች ብቃት

ሁሌም እንቅልፍ ስለሚነሳቸውና ስለሚያቓዣቸው ይመስላል።

ሁለተኛው ምክንያት ጥንትም ሆነ አሁን፡ የኢትዮጵያ ስርዓቶች፡ የባዕድ እና የምዕራብ ሃገሮችን ማለትም (አሜሪካ፡ እንግሊዝና፡ ሶቭዬት ህብረትን)እንዲሁም የመልህቆቻቸው ማለትም የነዚህ ኣካላት ወኪሎቻቸው እንደ (የኣረብ ኤምሬትስን የመሳሰሉ ሃገራት መሆኑ ነው)፡ ጉዳይ ኣስፈጻሚና ተላላኪ መሆንን ዋንኛ ተግባራቸው አድርገው በመውሰዳቸው ነው። በመሆኑም በኢትዮጵያ ስርዓቶች ከንፈርና ቅንድብ ላይ ፡ ሁሌም “ሻዕብያ ወይም ኤርትራ” የሚል ቃል ሰፍሮ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም፡ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን ሲደክሙና የሃገር ውስጥ የህዝባቸው ጉዳይና ችግር ሲወጥራቸው፡ “ባህር” የሚል ምክንያት (ሕመም) በመፍጠር፡ ከቀውሳቸው ማገገሚያ፡ በጉርብትና ሰበብ፡ ህዝብን በስሜት ለመቀስቀስና ለማወናበድ አሁንም አሁንም ደጋግመው “ባህር” የሚል ዜማቸውን ሊዘምሩለት መሞከራቸው ነው።



የኢትዮጵያው የብልጽግና መንግሥት፡ ኣስቀድመው ከተሸነፉት የኢትዮጵያ ስርዓቶች ለመማር ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳሳትና ለማወናበድ ሳያሰልስ ሲጥር ይታያል። ይበልጥ የሚገርመው፡ ኣንዳንዶችንም የሚያሰጋ የሚመልስላቸው፡ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ኣንደበት የሚነዛው፡

በኤርትራና ኢትዮጵያ ዝምድና መሻከር ምክንያት

የኣፍሪካ ቀንድ ላይ፡ በዋነኝነትም በነዚህ ሁለት ሃገራት መካከል፡ አሁንም ከባድ ጦርነት እንዳይነሳ የሚል ስጋት ነው።

ምናልባትም ዋነኛው ምክንያት፡ ኢትዮጵያ መላቅጡ ጠፍቶባትና መተንፈሻ ስታጣ፡ በዓሰብ በኩል የባህር በር ለመክፈት፡ ኤርትራን ጦርነት ውስጥ እንዳትጋብዛት የሚል ስጋት ይመስላል። ኤርትራ ከቀድሞ ገዥዋ ከኢትዮጵያ ቋሚ ስጋቷ ሙሉ በሙሉ ሊቀረፍላት ከፈለገች፡ አንዲት ወደብ (ምጽዋዕ) ስለምትበቃት፡ ዓሰብን ለኢትዮጵያ ልትተውላት ይገባል የሚል ስውር የስነ-ልቦናት ጦርነት (Psychological Warfare) ኣካል መሆኑ ኣሌ ኣይባልም።

ይህ ኣጉልና ከንቱ ምጉት፡ ሁሌም ያለ አንዳች ጥርጥር የቀደሙ የኢትዮጵያ ስርዓቶችን ያከሰመ ፋይዳቢስ ምጉት ነው። በሌላ በኩል ሲታይ ደግሞ፡ ይህ ፋይዳቢስና ከንቱ ምጉት፡ የኤርትራዉያንን ሃገራዊ ማንነትና ምንነት ይበልጥ በማጉላትና በማጽናት፡ የኤርትራውያንን ሃገር የማዳንና የማቀብ ስትራቴጂካዊ ድልን ለማጎናጸፍ ካስቻሉት ምክንያቶችን ኣንዱ መሆኑ የተዘነጋ ይመስላል።

ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ልሂቃን በኩል የሚካሄደው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና የስነ ልቦና ጦርነት ማለቂያ ዬሌለው ቢሆንም፡ በኤርትራ በኩል ግን ምንም ዓይነት “የስጋት ምልክት” ይሁን የመልስ ምት ያዘለ ማብራሪያ ሲሰጥ ኣይታይም። ሻዕብያ፡ ከትጥቅ ትግል ግዜ ጀምሮ ካካበተውና እስከ ኣሁን ድረስ ኣቅቦ ከያዘው ባህርዩና ፖለቲካዊ መርሁ በመመርኮዝ፡ “እዩኝ እዩኝ ማለት፡ ደብቁኝ ያመጣል” እንዲሉ፡ ሻዕብያ ከመለፍለፍ ምንም ጠብ የሚል ነገር እንደሌለ ማወቁ ምስጢር ኣይደለም። እንዲያዉም በሆይሆይታና ጫጫታ የሚባባስ እንጂ የሚቀረፍ ጉዳይ እንደማይኖር ሊጤን ይገባዋል። የኤርትራ መንግሥትም፡ ጫጫታና ሆይሆይታ ምንም ፋይዳ ስለማይገኝበት፡ በኢትዮጵያ በኩል ማለዳ ማለዳ እንዳዲስ ኣሁንም ኣሁንም ለሚናፈስ ፋይዳቢስ ጉዳይ፡ መልስ ለመስጠት ሆነ ለማስተናገድ ሲል፡ የኢትዮ-ኤርትራን የፖለቲካ ትኩሳት ለማባባስ የመረጠ ኣይመስልም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከሃገሪቷ መሪ ጀምሮ ማንም የፖለቲካ ፓርቲ ወኪል ነኝ ባይ ተራና ተለማማጅ ፖለቲከኛ እንዲሁም ኣለሁ ኣለሁ ባይ ካድሬዎች ጭምር፡ ሻዕብያና ኤርትራ “የአፍ መፍቻ” ቃላቶቻቸው መሆናቸው ሊያስገርም የማይችል የየዕለቱ ትዕዝብት ሆኖ ይገኛል።

በአጠቃላይ ሲታይ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያገባህና በማያገባህ ጉዳይ ሁሉ “በመለፍለፍ ስሜትን መተንፈስ”፡ ባህል ሆኗል። ኤርትራ ውስጥ ግን፡ በሚያገባህና በማያገባህ፡ በምታደርገውና በማታደርገው ጉዳይ ሁሉ ኣፍህ እንዳመጣልህ መሞጣሞጥና መለፍለፍ፡ ኣሳፋሪና ኣስጠሊታ ኧረ እንዲያው ኣስነዋሪ ተግባር መሆኑ፡ ህጻናት እንኳ ሳይቀሩ የሚያውቁት ሃቅ ነው። ይህ ሲባል ግን ፍሬ ባለው ጉዳይና በቁምነገር ላይ ሃሳብን መግለጽ ኣይጠላም።



ለምሳሌ፡ ባለፈው ዓመት ሙሉ

ኢትዮጵያ፡ እያደገ ካለው የህዝብ ብዛቷና ኢኮኖሚዋ (ቁጠባዋ)፡ እንዲሁም ጂኦግራፊካዊ ኣቀማመጧ ኣኳያ፡ የባህር በርን በየትኛውም በኩል ቢሆን፡ ለማግኘት አጀንዳዋ አድርጋ ትንቀሳቀሳለች፡ ትገፋበታለችም። ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ(መልክዓምድር) እስረኛ ኣይደለችም።

የሚል ቅንቀሳ በይፋ ሲለፈፍና ሲደነፋ ቆይቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ቃሉን ለዓለም ይፋ ካደረገበት ግዜ አንስቶ፡ የገዛ ሃገሩን በጎረቤት ሃገሮች ኣስከብቦ (ከበባ ውስጥ አስገብቶ)፡ ኢትዮጵያን ትልቅ ዋጋ እያስከፈላት ነው ሊባል ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪም፡ ይህ ነው ወደ ማይባል ትልቅ ተነጽሎ ወይም መገለል እያስመራትም ይመስላል። በዚህ በያዝነው ወር፡ አንድ የኢትዮጵያ ጀነራል

ኢትዮጵያ፡ የባህር በር አስፈላጊነትን ለዓለም በአዋጅ መልክ መግለጧ ብቻ ትልቅ ድል ነው፡

በማለት፡ የአለቃውን ቃል ሊደግም ሞክሯል።

በማንኛውም ሚዛን ሲታይ፡ ይህን መሰሉ ህልም፡ የብልጽግናውን መንግሥት ፖለቲከኞች
ከህጋዊነት ቀውስ (Legitimmacy Crisis)

ለማውጣትና ለማዳን የተፈበረከ መላ ነው።

በሌላ አባባል፡ የወያኔዋ ኢሕኣዲግ (ኢትዮጵያ) መንግሥት መሪ ነፍስኄር መለስ ዜናዊየኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅጥ ማስተዳደር ከቁጥጥሩ ውጭ ሲሆንበት ግዜ፡ የድንበር ሰበብን በመፍጠር፡ የኢትዮጵያ ህዝብን ከኤርትራ ጋር ዲል ባለ ጦርነት በማናከስ፡ የህዝቡን ትኩረት ለመቀየርና ለመጠምዘዝ እንደሞከረው ማለት ነው። የሚገርመው የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች፡ የአፍሪካ ሃገሮች ህጋዊ ድንበሮች ወዳልነበሩበት ግዜ፡ ማለትም ቅድመ ጣልያንና ቀኚ ገዢዎች ወደ ነበሩ ግዜዎች በመመለስ፡

ራስ ኣሉላ ኣባ ነጋ ሳይቀር፡ ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ግዛት ኣካል መሆኑን ኣውቆ ይጠቀምበትም ነበር

የሚል ንጽጽርን ሊያቀርቡ በመሞከራቸው፡ ታሪክን መካድና በሁለቱ ህዝቦች ስነ ልቦና ላይ መሳለቅና የሁለቱ ህዝቦችን ንቃተ ህሊና ከመናቅና ከመድፈር ባሻገር፡ በኤርትራ ህዝብ ላይ ጥይት እንደመተዀስ ሊቆጠር ይችላል።

ባጭሩ፡ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን፡ ኤርትራን በሰበብ አስባቡና በረባ ባልረባው ወደ ጦርነት ሊጋብዙ የሚሞክሩት ለምንድን እንደሆነ፡ ይህ ነው የሚባል መልስም ኣይገኝለትም!

በአሁኑ ወቅት፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በብልጽግናው መንግሥት አጓጉል የፖለቲካ ኣካሄድ ምክንያት፡በተለይ የአማራና የትግራይ ክልሎች ቅልጥ ባለ ስርዓት ኣልበኝነት ውስጥ ተዘፍዝፈው ይገኛሉ። በመሃል ኢትዮጵያ ይሁን በሁለቱ ክልሎች ያሉ ባለሥልጣኖች ግን፡ ኤርትራን፡ የውስጥ የፖለቲካዊና ወታደራዊ “ችግሮቻቸው መፍቻና መቋመርያ” ለማድረግ፡ ሳያነሷትና ስሟን ሳይጠሯት ኣይውሉም። ኣንዳንድ የኢትዮጵያ ልሂቃንና ባለሥልጣኖች

ኤርትራ፡ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተዋጊ የፋኖ ሃይሎችን የትጥቅና ስንቅ ድጋፍ በመስጠት ትመራቸዋለች

በማለት ለማማት ይሞክራሉ

በተመሳሳይ መልኩ፡ ትግራይ ክልል ውስጥም፡ ህወሓትን (ወያኔን) እና ትግራይን ከሁለት ገምሰውና ከፍለው የሚገኙ ባለስሥልጣኖች፡ ኤርትራን አሁንም አሁንም ከመወንጀል ኣላባሩም። ለምሳሌ፡ የትግራይ ክልል ግዝያዊ ፕረዚደንት፡ ተቀናቃኙን

ከሻዕብያ ጋር ግንኙነት ስለጀመረ፡ የባዕድ ሃይሎችን ያመነ አንጃ ነው

በማለት፡ ኣፉ እንዳመጣለት ሲወነጅል ተሰምቷል።

ከዚህ ባልተለዬ መልኩ፡ አውርቶ አደር የሆኑ ልጓም-ኣልባ የማህበራዊ መገናኛ ኣውታሮችም

ሻዕብያ፡ ፋኖንና ኣንዱን የህወሓት አንጃ በማስተባበር፡ ስሉስ ኪዳን በመፍጠር፡የብልጽግናን መንግሥት ከስልጣን ለማባረር ተነስቷል

በማለት 'ይተነትናሉ'።

ታዲያ ከዚህ ሁሉ ዝባዝንኬና ቡራከረዩ በኋላ፡ ኤርትራ፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉረሮ ላይ እንደተሰነቀረች አጥንት፡ ተጽዕኖዋና ሚናዋ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ፡ ራሳቸው ኢትዮጵያዉያን ሳይቀሩ እንደሚያምኑባት ፍንትው ብሎ ይታይሃል ትገነዘባለህም።

እርግጥ ነው፡ የኢትዮጵያ ልሂቃን፡ የኤርትራን ፖለቲካዊ ተጽዕኖና ሚና ወሳኝነት አይክዱም። ነገር ግን በተዛባው ፖለቲካዊ አመለካከታቸውና በተዛነፈው የባህር በር ከንቱ ምኞታቸው ምክንያት፡ የኤርትራን መልካም ጉርብትና፡ ገንቢ ሚናና ኣቋሟን በተገቢው መልኩ ሲጠቀሙበት ኣይታዩም። ትልቁ ድክመታቸው ደግሞ፡ እስከ አሁን ኢትዮጵያን የመሩ ባለሥልጣኖች፡ ለባዕድ ርእሰ ሃያሎች ጥገኛ መሆንን በመምረጣቸው ምክንያት፡ በውድ ይሁን በግድ፡ ከኤርትራ ህዝብ ኣንጻር የወሰዱት ፖለቲካዊ ኣቋምና እርምጃ፡ በሚገባ በምክንያታዊነት ሊቀምሩት ወይም ሊያሰሉት ባለመብቃታቸው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነግሱ መንግሥቶች፡ ቢያምኑበትም ባያምኑበትም፡ አንዴም ወይ ሊለሙ ኣሊያም ሊጠፉ፡ በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ፡ እጣቸው ከኤርትራ መንግሥት እጅ የማይወጣ መሆኑ፡ የትናንት ታሪክ ህያዉ ምስክር ነው።



በእርግጥ፡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የትላንትና የዛሬን የቅርብና የሩቁን ታሪክ በመመርመርና በመፈተሽ፡ ከታሪክ ሊማሩ ይገባል። ለምን ቢባል፡ ትላንት፡ የዘመናውያን የኢትዮጵያ ስርዓቶች (ሃይለስላሴ፡ ደርግና፡ ኢህአዴግና ወያኔ) ከኤርትራ ኣኳያ የነበራቸው ፖለቲካዊ ኣመለካከት ባለመጥራቱ (የኢትዮጵያ ስርዓቶች በኤርትራ ላይ ያካሄዱት አመጽና ሸፈጥ በመባባሱ) ምክንያት፡ በተከታታታይ የኢትዮጵያ ሥርዓቶች ውድቀት ዕጣ ፈንታቸውን፡ የወሰነውና የፈረደው፡ ሻዕብያና የሻዕብያ መንግሥት ከሆነ፤ ዛሬ ሆነ ነገ ከነገ በስቲያም ሻዕብያ ይህንን ለማድረግ ኣያቅተውም።

ስለሆነም፡ ኣንድ ማስተዋልን የሚጠይቅ ብርቱ ጉዳይ ኣለ። እሱም፡ የተወራ ቢወራ፡ የተናፈሰ ቢናፈስ፡ ሻዕብያ ቃል ማውጣት በጭራሽ ባህሉ ኣይደለም። ከመድፍ ድምጽ በላይ የሆኑ ቃላቶች ቢተኰሱም፡ ለሻዕብያ በምንም መልኩና በምንም ተኣምር ስጋት ሆነ ፍራቻ ሊያሳድሩበት ኣይችሉም። ሻዕብያ ባንድ በኩል ዔሊ በሌላ በኩል ደግሞ ኣዞ ነው። በመሆኑም ሻዕብያ በምንም መልኩ ኣዝኖና ልቡ ቅሮ ኣያድርም። የማታ ማታ እንደ ዔሊ “በትዕግስትና በጥሞና” ቀስ ብሎ በመጓዝ፡ እንደ ዓዞም ኣድፍጦ በመቆየት፡ ደመኛ ጠላቶቹን ኣይምሬ መሆኑን ታሪክ በተደጋጋሚ መስክሮታል። ስለሆነም፡ ምላሳሞቹ የኢትዮጵያ ‘ልሒቃን’፡ የኢትዮጵያን የውስጥ ፖለቲካዊ ችግር ለማለዘብና ለማስተንፈስ በሚል ሰበብ የጦስ ዶሮ (scapegoat) ለማግኘት፡ ሁሌም የኤርትራን ስም ከማንሳት ሊቆጠቡና ኣደብ ሊገዙ ይገባል።

ኤርትራ፡ በፖለቲካዊ ልዑላዊነቷና በውስጣዊ ጉዳዩዋ ራሷን የቻለች ሃገር ስለሆነች፡ የጸጥታና ደህንነታዊ ጉዳያዋ ሆነ የኢኖሚያዊ ጉዳዩዋን በተመለከተ ‘ክተት’ ማለት ኣያስፈልጋትም፡ እንደዘበትም ኣታያቸውም።


ሲጠቃለል፡ ይህን ምርጥ ጽሑፍ ኢትዮጵያዉያን ‘ልሂቃን’ ሕሊናቸውን ይመረምሩ ዘንድ በማለም ላካፈለን ለፍስሃየ ኪዳነ ‘ሞቅ ደመቅ ሸብረቅ’ ያለ ምስጋናችንን ኣቅርበንለታል፡ ፕሮፉርሸር ዘሜ ዘመሰሎም የ ፍስሃየን ጥሑፍ እዚህ viewtopic.php?f=2&t=358567 ስለዶለው ኣመስግነነዋል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና እንዲሁም ልበምሉነት ጭምር!

Meleket
Member
Posts: 4543
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ለቅኝት የተላከችው የኤርትራ ድሮን

Post by Meleket » 12 Mar 2025, 11:47

Meleket wrote:
23 Dec 2024, 10:45
ምንኛ ተሞኙ

የወሎ “ልሒቓን” ምንኛ ተሞኙ፡
የትግራይ “ልሒቓን” ምንኛ ተሞኙ፡
የጉራጌ “ሊቆች” ምንኛ ተሞኙ፡
የጦብያ “ልሒቓን” ግምኛ ተሞኙ፡
በስራ እንደ መትጋት በህልም ሲናኙ፡
የኤርትራን በዅር ዓሰብን ሲመኙ፡

የጦርነት ዜማ በተንኮል ሲቀኙ፡
ከረሓብ በስተቀር እኮ ምን ኣገኙ?

መታሰቢያነቱ “ዓሰብ ዓሰብ” እያሉ በቁም ለሚቓዡት ለመረጃዎቹ “የወሎ ልሒቕ” Abere፣ “የትግራይ ልሒቅ” Axumezana እንዲሁም ለጉራጌው “ሊቅ” Horus! ድንቄም ልሒቃን!

ተጻፈ በኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

sarcasm wrote:
21 Dec 2024, 11:45
'ሕዝቡን በረሓብና siege ልጨርሰው ነው' እያለ ነው ያለው
viewtopic.php?f=2&t=356565

Post Reply