Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40050
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by Horus » 10 Mar 2025, 12:15

ትላንትና በመስቀል አደባባይ ትልቅ የኢቫንጀሊስቶች ትዕይንት ነበር ፤ በቢሊ ግራሃም ልጅ በፍራንክ ግራሃም የተሰበከ ። እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ፤ እናም ትርኢቱን ያየሁት በሓይማኖታዊ መልኩ ሳይሆን እንደ አዲስ አበባ ውበትና የሕዝቧ ሕይወት አገላለጽ ምንነት ነው። እኔ ይህን ትርኢት ያየሁን ልክ እንደ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት፣ እንደ ኦርቶዶክስ መስቀል ፣ እንደ ኃይሌ ገብረ ስላሴ ታላቁ ሩጫ ነው ። ይህን አዲስ ትውልድ በሰላም ብንተወውና ሕይወቱን ሲያሻው ፣ ሲያሻው በሩጫ፣ ሲያሻው በኮንሰርት ፣ ሲያሻው በመስቀል፣ ሲያሻው በፕሮቴስታንት፣ ሲያሻው በኦርቶዶክስ፣ ሲያሻው በኢድ እራሱን በዚህ መልክ ቢገልጽ ነው ኢትዮጵያ የምታምረው! ያ ይሆን ዘንድ የምታምር አዲስ አበባ የግድ ትላለች!!


Horus
Senior Member+
Posts: 40050
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by Horus » 10 Mar 2025, 12:19


Horus
Senior Member+
Posts: 40050
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by Horus » 10 Mar 2025, 12:24


Horus
Senior Member+
Posts: 40050
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by Horus » 10 Mar 2025, 12:30


Odie
Member+
Posts: 6109
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by Odie » 10 Mar 2025, 12:31


sesame
Member+
Posts: 7937
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by sesame » 10 Mar 2025, 12:39

Horse [deleted],

Feed your people. This is what the World Food Program (WFP) says in its front-page. It is what every visitor to the web-site sees first.

Ethiopia

15.8 million people needed food assistance in 2024

55% of all children under 5 years are malnourished

129.7 million population


But you dumbass persist in your idiotic attempt to paint a rosy picture of your country!

Abere
Senior Member
Posts: 14806
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by Abere » 10 Mar 2025, 14:11

የአዲስ አበባ ወጣት እዘጭ እዘጭ እና ጭፈራ ይወዳል። ዘረጦ ህዝብ ነው፤ የድጋፍ ሰልፍ አለ፤ የፓሊስ ቆመጥ የለም፤ ነጻ ምግብ አለ፤ ነጻ ከኔትራ አለ ከተባለ አiድስ አበባ መድር ቀውጢ ያደርጋል። የፈሪ መብቅያ አዲስ አበባ። በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሚመራ ንቃተ-ህሌናው ከአለም ዝቅተኛ የሆነ አዲስ አበባ ነው። እንደ የካ የፋሲካ ሰሞን የነጋዴዎች በግ በፓሊስ ቂጡ ላይ እየተገረፈ ተሰልፎ የሚጨፍር መብት አልባ - የ21ኛ ባለ ሁለት እግር በግ - አዲስ አበባ።

Horus
Senior Member+
Posts: 40050
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by Horus » 10 Mar 2025, 14:43

Abere wrote:
10 Mar 2025, 14:11
የአዲስ አበባ ወጣት እዘጭ እዘጭ እና ጭፈራ ይወዳል። ዘረጦ ህዝብ ነው፤ የድጋፍ ሰልፍ አለ፤ የፓሊስ ቆመጥ የለም፤ ነጻ ምግብ አለ፤ ነጻ ከኔትራ አለ ከተባለ አiድስ አበባ መድር ቀውጢ ያደርጋል። የፈሪ መብቅያ አዲስ አበባ። በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሚመራ ንቃተ-ህሌናው ከአለም ዝቅተኛ የሆነ አዲስ አበባ ነው። እንደ የካ የፋሲካ ሰሞን የነጋዴዎች በግ በፓሊስ ቂጡ ላይ እየተገረፈ ተሰልፎ የሚጨፍር መብት አልባ - የ21ኛ ባለ ሁለት እግር በግ - አዲስ አበባ።
አቶ አበረ፡
ያልኩትኮ ያ ነው! እኔና አንተ አዲስ አበባ ውስጥ አንኖርም! ስለዚህ ያሻህን መግለጽ መብትህ ነው! አዲስ አበባ የሚኖረው እራሱን በዚያ መልክ ይገልጻል። ገጠር ያለም እንደዚያው! ማ ይንገር የነበረ ነው ሁሉም ነገር! ምንም ለውጥ የማያመጣ የግል አስተያየት ያው ለባለቤቱ ነው ።

Abere
Senior Member
Posts: 14806
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: THE EVER DYNAMIC YOUTHFUL ETHIOPIA!

Post by Abere » 10 Mar 2025, 15:34

Horus,

አዲስ አበባ ማለት የተበከለ ውቅያኖስ እንደማለት ነው ( hazardous material polluted ocean)። ይህ ደግሞ ለአገር እና ለህዝብ ጠንቀኛ ነገር ነው። በኤድስ፤ በግብረ-ሰዶም፤ በጥገኝነት፤ በስራ ጠልነት፤ እርካሽ ባህል ተቀባይ እና አስተላላፊነት የሚያገልግል የአገር ክፍል ሊበረታታ አይገባውም። ነገ ደግሞ ግብረ-ሰዶማዊያን ምድር ቃጤ አድርገው ሲጨፉሩ ለማየት የጓጓህ ትመስላለህ።

ሌላው የአዲስ አበባ ህዝብ በሌሎች ጫንቃ ነጻ ሊወጣ፤ የኢኮኖሚ ጥገኛ በመሆን ብቻ በፍራት 1ኛ ደረጃ መሆኑ ሊያሳፍር እንጅ ሊመሰገን አይገባውም። የአዲስ አበባ ወጣት አይደለም ቄሮ መጣብህ ብለኸው ዐይጥ መጣችብህ ካልከው እግሩ እስኪሰባበር ሩጦ መኪና አደጋ የሚገጥመው ፈሪ ነው። ጫት፤ ድራፍት እና ስጋ አቅርብለት። ባለጉትቻ እና ባለሹሩባ ወንድ ቁጥር ከሴቶች በልጧል። ይህም የኮሪደር ልማት ይሆን hahaha

Post Reply