ካን በከካን ና ጎዼ እረ፣ ከን በጋን ነማ ና ጎዼ፤ ጂeዼ ነምቻ በከካን እቲ ቡኤ ጂeዱ የመከማከን።
ነገሩ እንዲህ ነዉ፣ መብረቅ ከወረደብህ፣ ሰዉ አያዝንልህም፣ የኢግዚያብሔር ስራ ነዉ ስለምባል፣ ለተጎጂዉ ማዛን የእግዚያብሔርን ስራ እንደመቀወም ይሆናል ተብሎ ይቆጠራል ና። ስለዚህ ሰዉ ላይ መብረቅ ወረደ ይምል ወሬ ከሰመህ፣ እንኳን ሆነ እንጂ፣ ወይ ያሳዝናል፣ ለምን እግዚያብሔር አደረሰበት ተብሎ መልስ አይሰጥም። ይህን የሰማ ሁሉ እንደማዛን እንኳን (በአፋን ኦሮሞ በጋ) እያሉ ነዉ የምመልሱት። ታዲያ ሰዉዬዉ ይህን ከአስተዋለ ቦኋላ፣ ምን ጉድ መጣብኝ ብሎ ይገረም ና፣ መበረቁ ከጎዳኝ በላይ የሰዉ እንኳን ማለት ያደረገኝ ነዉ የባሰብኝ (ካን በከካን ና ጎዼ እረ፣ ከን በጋን ነማ ና ጎዼ) አለ ለማለት ነዉ።
ይህን አባባል ያስታወሰኝ ደግሞ የአቶ ዘለንስኪ ጉዳይ ነዉ። ያን የምያክል ጉድ ከወረደበት ቦኋላ ሁሉም ሰዉ፣ አሳዘንከን እንደማለት፣ ህድ ና ከ ፕረዚደንት ትራምፕ ጋር ግንኙነትህን ጠግን የምል ቀልድ የምመስል ጉዳይ ይመልሱለታል። ሰዉዬዉ ደግሞ በነጩ ቤተመንግስት ከደረሰብኝ ዉርጅብኝ በላይ፣ ሁሉም ይህን ጉዳይ ሰምቶ ህድ ና ከፕረዚደንት ትራምፕ ጋር ግኑኝነትህን ጠግን ማለቱ ይበልጥ ሳይጎደዉ አልቀረም የምል ግምት አለኝ።
ይህን ሁሉ የመጣበት በይደን የምባል ግለሰብ ይመስለኛል። ነብሱ ይማር ይሁን?
-
- Senior Member
- Posts: 11902
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32