Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

IMF:-በሥራ ላይ የሚገኙ የመንግሥት ባሥልጣናት (ሚኒስትሮችን ጨምሮ)፣ በብሔራዊ ባንክ ቦርድ ውስጥ እንዳይካተቱ ሲል አስጠነቀቀ

Post by Za-Ilmaknun » 05 Feb 2025, 13:32

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በቅርቡ በሕዝብ በተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ውስጥ ሊካተቱ ይገባሉ ያላቸው መሠረታዊ ማሻሻያዎች ሳይካተቱ መቅረታቸውን በመግለጽ ጥያቄ አነሳ፡፡

አይኤምኤፍ ከመፅደቁ በፊት የተመለከተውና በኋላም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ የብሔራዊ ባንክን ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት የሚያዘምን ቢሆንም፣ ብሔራዊ ባንክ ከመንግሥት ተፅዕኖ ውጪ ሆኖ በራሱ ለመወሰን የሚያስችለውን ተቋማዊ ነፃነት ከመስጠትና ባንኩን ከሚመለከቱ ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች አኳያ ጉድለቶች አሉበት።በአዋጁ መካተት የነበረባቸው ነገር ግን ሳይካተቱ የቀሩ ቁልፍ ጉዳዮች ብሎ ካነሳቸው መካከል፣ በሥራ ላይ የሚገኙ የመንግሥት ባለሥልጣናት (ሚኒስትሮችን ጨምሮ)፣ በብሔራዊ ባንክ ቦርድ ውስጥ እንዳይካተቱ የሚከለክል አንቀጽ አለመኖሩ አንዱና ዋናው ነጥብ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ የሥራ አስፈጻሚው መንግሥት ባለሥልጣናት ያልሆኑ ሌሎች የመንግሥት ኃላፊዎችም በብሔራዊ ባንክ ቦርድ ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ መያዝ እንደሌለባቸው የሚከለክል ድንጋጌ በአዋጁ ውስጥ አለመካተቱ፣ ሌላው ክፍተት መሆኑን አይኤምኤፍ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ አመልክቷል።

የገንዘብ ተቋሙ መሠረታዊ ክፍተት ብሎ ያነሳው ሌላው ነጥብ የብሔራዊ ባንክ ገዥ፣ ምክትል ገዥዎችና የቦርድ አባላት የሚሾሙበት ባለሁለት ድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት (double veto procedure) በአዋጁ መካተት ነበረበት የሚል ነው።

https://www.ethiopianreporter.com/138047/

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10454
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: IMF:-በሥራ ላይ የሚገኙ የመንግሥት ባሥልጣናት (ሚኒስትሮችን ጨምሮ)፣ በብሔራዊ ባንክ ቦርድ ውስጥ እንዳይካተቱ ሲል አስጠነቀቀ

Post by ethiopianunity » 07 Feb 2025, 11:27

As long as Ethiopia thinks it has to develop like West erecting will be demolished buildings, etc in stead of following its natural way of living hence you don’t have to be suit dresser, nothing good will come out of imf or what or who etc, these are instruments of one world government

Post Reply