Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40147
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!

Post by Horus » 04 Jan 2025, 13:34

ትፈነዳለች! ትንቀጠቀጣለች! እስከስታ ትረግዳለች! አዳዲስ ወንዞችን፣ ተራሮችን ትወልዳለች! አሮጌውን ሰባብራ አዲሶቹን ታመጣለች! ፍጥረት እጹብ ድንቅ! ኢትዮጵያዊያንም እንዲያከብሯት እንዲፈሯት ታስተምራለች!! ይህ ትውልድ እድለኛ ነን! መሬት ፍጥረት ስንት ሚሊዮን አመት በፊት የሰራችውን መልሳ እያሳየችን ነው!! በኃያሏ ምድር ፊት የሰው ልጅ አቅም ኢምንት እንደ ሆነም ዘላለማዊ ዊዝደም እየሰጠችን ነው !! አግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃት :idea: :!:

Abere
Senior Member
Posts: 14830
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!

Post by Abere » 04 Jan 2025, 13:42

ቀን በበቅሎ ሌት በቆሎ የአዲስ አበባ ነገር የግሪምቢጥ። ፒያሳ በባዶው ውሃ ሲባክን ሲንቦጫራቅ ሲያይ አምሽቶ ማታ ቤት ሲገባ ሽንት ቤት የሚያጸዳበት (የሚያወርድበት) ውሃ አጥቶ ቤቱ ሲገማው ያድራል። የመታጠቢያ እና የመጸዳጃ ቤቱ ድርቆ የበሽታ ቋት የሚጠጣ ውሃ እጥረት በሽበሽ። ቅድሚያ የግል ንጽህና

Selam/
Senior Member
Posts: 16994
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!

Post by Selam/ » 04 Jan 2025, 14:07

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ከምድራዊ ንዋይ አንቋላጮች፣ ከጣዖት አምላኪ ጭልፊቶች፣ ከግብዝ አረማውያኖች፣ ከስድ-አደግ ባለጌዎች፣ ከድሃ-ጠል ካድሬዎች፣ ከሆዳም ጎጠኞች፣ ከልበ-ደንዳና ጨካኞችና ከገዳዮች ይጠብቃት። የመዳን ክንፉን በተበደሉት፣ በተቸገሩትና በተጎዱት ላይ ይዘርጋ።

Horus
Senior Member+
Posts: 40147
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!

Post by Horus » 04 Jan 2025, 14:12

Abere wrote:
04 Jan 2025, 13:42

ቀን በበቅሎ ሌት በቆሎ የአዲስ አበባ ነገር የግሪምቢጥ። ፒያሳ በባዶው ውሃ ሲባክን ሲንቦጫራቅ ሲያይ አምሽቶ ማታ ቤት ሲገባ ሽንት ቤት የሚያጸዳበት (የሚያወርድበት) ውሃ አጥቶ ቤቱ ሲገማው ያድራል። የመታጠቢያ እና የመጸዳጃ ቤቱ ድርቆ የበሽታ ቋት የሚጠጣ ውሃ እጥረት በሽበሽ። ቅድሚያ የግል ንጽህና
አው ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው! አበሻ በአፉ ጤፍ ይቆላል ይባል የለ?!!

Abere
Senior Member
Posts: 14830
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!

Post by Abere » 04 Jan 2025, 14:18

የብልጽግናው ካህናት በፏፏቴው ዳርቻ ሲታዩ አንድ ነገር አስታወሰኝ። በዚህ በሰሜን አሜሪካ በርካታ ቤተክርስቲያን በብልጽግና ቀሳውስት እየተወረሩ ነው የሚል በርካታ ቅሬታ ስለሰማሁ። በኮንዶምንየም፤በአፓርትመንት፤ወዘተ ጥቅማጥቅም የተገዙ በዲያስፓራ የተላኩትን ምዕምን እገሌ እኮ ብልጽግና ቄስ ነው የሚል ሃሜት ይሰማል። የiPhone እና iPad ቄሶችም ይሏቸዋል - Addis Ababa የብልጽግናው ሲኖዶስ የሚልካቸው ( በስራ ላይ ታጠናላችሁ) የተባሉ ናቸው ይባላል :lol:
Selam/ wrote:
04 Jan 2025, 14:07
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ከምድራዊ ንዋይ አንቋላጮች፣ ከጣዖት አምላኪ ጭልፊቶች፣ ከግብዝ አረማውያኖች፣ ከስድ-አደግ ባለጌዎች፣ ከድሃ-ጠል ካድሬዎች፣ ከሆዳም ጎጠኞች፣ ከልበ-ደንዳና ጨካኞችና ከገዳዮች ይጠብቃት። የመዳን ክንፉን በተበደሉት፣ በተቸገሩትና በተጎዱት ላይ ይዘርጋ።

sesame
Member+
Posts: 7953
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!

Post by sesame » 04 Jan 2025, 14:21

Horsey,

They say 80% residents of Addis Ababa live from hand to mouth. Don't you think it is the duty of their government to try to improve their lives instead of wasting national resources for useless projects like parks and shining streets? The failed PP regime is trying to swindle its citizens by these useless projects. But what is your excuse?
:lol: :lol: :lol: :lol:

Selam/
Senior Member
Posts: 16994
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ምድርም እንደ ሕዝባችን ወጣት ነች!

Post by Selam/ » 04 Jan 2025, 14:38

ስለ ኢትዮጵያ መስሎኝ ርዕሱ!
sesame wrote:
04 Jan 2025, 14:21

Post Reply