Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት

Post by Za-Ilmaknun » 19 Dec 2024, 19:27

የዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢቲሀድ ኤርዌይስ ሕግ በመጣሳቸው በገንዘብ እንዲቀጡ ወስኗል።

ሚኒስቴሩ ባለፈው ሐሙስ ባወጣው መግለጫ መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካው ዩናይትድ ኤርላይንስ መለያ (ኮድ) በመብረሩ 425 ሺህ ዶላር እንዲቀጣ ተወስኗል። :mrgreen:

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ኤቲሀድ አየር መንገድ ደግሞ ጄትብሉ በተባለው የአሜሪካ አየር መንገድ መለያ ቁጥር በመብረሩ 400 ሺህ ዶላር ተቀጥቷል።

ሚኒስቴሩ በድረ-ገፁ ባወጣው መረጃ እንዳለው ሁለቱ አየር መንገዶች፤ በፌዴራል አቪዬሽን ባለሥልጣን (ኤፍኤኤ) የአሜሪካ አየር መንገዶች እንዳይበሩ በተከለከሉባቸው የአየር ክልሎች በመብረራቸው ነው ሕግ የጣሱት።

ሁለቱ አየር መንገዶች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ተዘግቧል።

አቪዬሽን ኮንሲዩመር ፕሮቴክሽን የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ቢሮ ባደረገው ምርመራ ከአውሮፓውያኑ የካቲት 2020 እስካ ታኅሣሥ 2022 ባለው ጊዜ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥፋቱን ፈፅሟል የተባለው።

በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዩናይትድ ኤርላይንስን ኮድ ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ ጂቡቲ በርካታ በረራዎችን አድርጓል፤ ይህ የአየር ክልል ደግሞ የአሜሪካ አየር መንገዶች እንዳይበሩበት በፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ክልከላ የተደረገበት ነው ይላል።

የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ ይህንን ድርጊት የፈፀመው ከዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ፈቃድ ውጭ መሆኑን መግለጫው ያትታል።

ቅጣቱን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢቢሲ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cq8qzgn19ylo

Union
Senior Member
Posts: 12062
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት

Post by Union » 19 Dec 2024, 23:42

:lol:

The US is now telling you it owns Ethiopia and eventually they are working to own everything in Ethiopia. Why do you think they are spending billions for the corridor limat :lol:

ባሪያ ሁላ አብይን ይደግፋል። ባንኩንም ገንዘቡንም ስራዎችንም፣ መከላከያ ተብዬውንም ከወረሱ ቦሀላ እያንዳድሽ አንገትሽ ይታነቃል :lol: :lol:

Union
Senior Member
Posts: 12062
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት

Post by Union » 19 Dec 2024, 23:49

አብይን የሚደግፍ ባሪያ ነው የምንለው ለዛ ነው

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት

Post by Za-Ilmaknun » 20 Dec 2024, 14:25

Ethiopian Airlines downward spiral. Purchasing of scrap planes from China.

Educator
Member
Posts: 2370
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት

Post by Educator » 20 Dec 2024, 15:49

Omg. Con artist satan Mamo Killo is ordering the airline to commit stupid crimes thinking he can get away with it just like all the mischief he got away with.

On the job training.
Za-Ilmaknun wrote:
19 Dec 2024, 19:27

Post Reply