የጥንት ታሪክን ማጥናት ቀላል ኣይዴለም። ቀልድም ኣይዴለም።
የጥንት ታሪክ ግልጽ ያልሆነላቸዉ ኣዙሪት ዉስጥ ገብተዉ እዛዉ ዉስጥ መልሰዉ መላልሰዉ ይዞራሉ። ኣዙሪት የያዘዉ በእንግልዘኛ ትንክ ኣዉትሳይድ ዘ ቦክስ የሚባለዉን ኣያዉቅም።
እኔ ሠፈራችን የምለዉ ምስራቅ ኣፍሪካ ከቦረና እስከ ጥንት ግብጥ ነዉ።
ካልተሳሳትኩ ከየትኛዉም የዐለም ክፍል ጋር ሲነጻጻር ከጥንት ግዜ ጀምሮ የሰዉ ጎሳዎች የኖሩባት ሠፈር ነዉ።
ዘመናዊ ትምህርት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከተጀመረ ወዲህ ለዚህ ትንሽ ሠፈር ለሁሉም ምን ይበጃል ሳይሆን ኣንዳንዶቹ ኣዙሪት ዉስጥ ይኖራሉ።
የሠፈሩን የጥንት ታሪክ የተመራመሩት ያደመደሙትን ወይ ኣልሰሙም፣ ወይም በግድዬለሽነት ያልፉት እና ኣዙሪታቸዉ ዉስጥ መኖርን ይቀጥላሉ።
ኣንድ በጣም ቀላል ፈዋሽ መድሃኒት በቅርብ ግዜ እዚሁ ፎረም ላይ ፅፌ የነበረዉ የሚከተለዉ ነዉ።
ኩት (ኦሮምኛ)
ኩረት (ቁረጥ) (አማርኛ)
ከት (እንግልዘኛ)
ይህ ማንም ሊክደዉ የማይችል ሳይንስ ነዉ። ይህ ሳይንስ ከባድ ኣለመሆኑንም የምያሳይ ነዉ።
የእነዚህን ቃላት በሶስት ቋምቋዎች ዉስጥ መመሳሰል ከኣሁን በፊት ያስተዋለ መኖሩን ኣላዉቅም። መኖሩን ሳላዉቅ ያስተዋልኩኝ ቢሆንም ካለ የማስተዋሉን ባለቤትነት በደስታ እሰጠዋለሁ።
ያቃላቱን በኦሮምኛ እና በእንግልዘኛ ዉስጥ መመሳሰልን ካስተዋልኩ ብዙ ዓመታት ቢሆንም አማርኛ ዉስጥ ኣለመኖሩ እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ እንቆቅልሽ ሆኖብኝ ነበር።
እንቆቅልሹን በቅርብ ግዜ የፈታሁኝ ቁረጥ በኩረት መተካት የሚችል መሆኑን ያስተዋልኩኝ ቀን ነበር።
ይህ ለሠፈራችን ሶስት ኣዙሪቶች ፈዋሽ መድሃኒት ከሆነ ኣዙሪቶቹ ምንድናቸዉ?
የመጀመሪያዉ ለኦሮሞ መብት ትግል ከእኔ በላይ አዋቂ ዬለም ብሎ ተከራካሪ ነዉ። ይህ ሀይለኛ ኣዙሪት ነዉ። ምክንያቱም ኦሮሞ ኩት የሚለዉ ነዉ ወይስ ኩረት የሚለዉ ነዉ ወይስ ከት የሚለዉ ነዉ ብለህ ብትጠይቀዉ ወደየት እንደሚዞር ኣይታወቅም። ጥንታዊት ሃገር ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጋ ሆኖ።
ሁለተኛዉ ኣዙሪት ቦረና ዉስጥ የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ሸዋ ደርሰዉ ኣያዉቁም ብሎ አፍ ሞልቶ መናገር ነዉ። ይህ አፍ ሞልቶ መናገር ትክክል ከሆነ ኩት አማርኛ እና እንግልዘኛ ዉስጥ የተከሰተዉ እንዴት ነዉ ቢባል መልስ ዬለም።
ሶስተኛዉ ጥንታዊ ለዘመናዊ ምን ፋይዳ ኣለዉ በማለት ዘመናዊ ጋ ለመድረስ ሩጫ ነዉ።
እንግልዛዊዉ ዊንስተን ቸርችል “The farther back you can look, the farther forward you are likely to see” ያለዉን ያላስተዋለ ነዉ።
ኣዉሮፓ ዉስጥ የሬይነሳንስ ንቅናቄ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረን የግሪክ ስልጣኔ እንደገና እንዲወለድ ነበር። ጥንታዊን መሠረት ኣድርገዉ ነበር ዘመናዊን ያዋለዱት።
የኢትዮጵያም ሬይነሳንስ መሠረት የሚሆነዉ ከጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪክ መጀመር ነዉ።
ኣንድ ፈዋሽ መድሃኒት ያልኩኝ በጣም ጥሩ ምሳሌ ነዉ።
የአዉሮፓ ሬይነሳንስ ንቅናቄ ላይ ብዙዎች ተረባርበዉ ነበር። የኢትዮጵያ ሬይነሳንስም ብዙ መረባረብን የሚጠይቅ ነዉ።
መንገድ ይዟል ለማለት ይህ ምሳሌ ብቻ በቂ ነዉ። በጥልቅ ማንበብ ለሚችሉ።
ዘ ጂኒ ኢዝ ኣዉት ኦፍ ዘ ቦትል ያላችሁ ዘ ኢትዮጵያን ዋይን ኤጅስ ቬሪ ዌል ማለት ትችላላችሁ?
Re: ለሠፈራችን ሶስት ኣዙሪቶች ኣንድ ፈዋሽ መድሃኒት
ይህ ቃል በትግርኛ እና በጉራግኛ ቋንቋዎች ምን እንደሆነ የምታዉቁ ልትነግሩን ትችላላችሁ?
በሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ቃሉ ምን እንደሆነ ማወቅ ቢቻል ጥልቅ ዕዉቀት ይሆናል።
በሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ቃሉ ምን እንደሆነ ማወቅ ቢቻል ጥልቅ ዕዉቀት ይሆናል።