Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6842
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኢትዮጵያን ማዘመን እንደ ዘመናዊ ኮሪደር ልማቶቹ በዘመናዊ ፌደራሊዝም ነዉ

Post by Naga Tuma » 06 Dec 2024, 15:47

በዜና የምሰማዉ ዘመናዊ ልማት ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት መልካም መሠረቶችን የሚገነባ ከሆነ ተመሳሳይ የሆኑ ዘመናዊ ፌደራሊዝም መሠረቶችን መገንባት ኣይቻልም?

ኣዲሶቹ የሃገር ዩኒቨርዚቲዎች የዘመናዊ ፌደራሊዝም መሠረቶች መሆን ኣይችሉም?

አዲስ አበባ በኮሪደር ልማቶች መሃል ሃገር ዉስጥ ስትገዝፍ ኣዲሶቹ ዩኒቨርዚቲዎች ከፌደራል መንግስት ጋር በመተባበር የአከባቢዎቻቸዉ ኮሪደር ልማት መሠረት መሆን ኣይችሉም? የፌደራሊዝም ጥያቄ ይህ ኣልነበረም?

ለምሳሌ ሰላሌ አምቦን ሳይጠብቅ የፌደራል መዋቅር ዉስጥ ገብቶ አከባቢዉን ቀልጠፍ ብሎ ያሳድጋል። ቦረና ወለጋን ሳይጠብቅ ከፌደራል መንግስት ጋር እየሰራ አከባቢዉን ያሳድጋል።

ሀረርጌ ምቹ ባይኤን ቀበ ዘፈኑን ከማዳመጥ ተነስቶ አርሲን ሳይጠብቅ ከፌደራል መንግስት ጋር እየሰራ አከባቢዉን ያሳድጋል። ጭሮም ድሬደዋን ሳይጠብቅ።

ወለጋ ዉስጥም ነቀምቴም ደምቢ ዶሎን ሳይጠብቅ። ሻምቡም ነቀምቴን ሳይጠብ። ከፈለገ ከነቀምቴም ሆነ ከደብረ ማርቆስ ጋር በመተባበር።

ጎጃም ጎንደርን ሳይጠብቅ። ደብረማርቆስ ባህር ዳርን ሳይጠብቅ።

ወሎ ትግራይን ሳይጠብቅ። አክሱም አደዋን ሳይጠብቅ።

ጅማ ኢሉ አባ ቦራን ሳይጠብቅ። ወልቅጤ ወላይታን ሳይጠብቅ።

አርሲ የቀጥታ ፌደራል አስተዳደር ምሳሌ የሆነዉን ስዳማን ሳይጠብቅ።

ይህ ለዘመናዊ የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ጽንሰ ሀሳብ ነዉ። ኣዲስ ኣይዴለም። ስራ ላይ መዋል የሚችል መሆኑን ለማጥናት በቂ ዩኒቨርዚቲዎች ኣሉ።

ሃገርን ለማፍረስ የተዋቀሩ አስተዳደሮች ዘላቂ ሃገርን የምያስተዳድር አወቃቀር ነዉ ብሎ ማሰብ የፖለትካ መቃወስ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ኢትዮጵያ የስዳማን የፌደራል አስተዳደርን ዌልካም ካለች ሰነበተች። የአወቃቀሯ ሂደት ጥሩ ምሳሌ ኣልነበረም?

ጥሩ ምሳሌ የነበረ ከሆነ ይህ ጽንሰ ሀሳብ የኢትዮጵያን ፌደራሊዝም ዘመናዊ ኣያደርግም?

Naga Tuma
Member+
Posts: 6842
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ኢትዮጵያን ማዘመን እንደ ዘመናዊ ኮሪደር ልማቶቹ በዘመናዊ ፌደራሊዝም ነዉ

Post by Naga Tuma » 07 Jan 2025, 19:59

በርገርን የተዋወኩኝ አሜሪካ ደርሼ ኣይዴለም።

ከሁሉ ቦታ በላይ በስነ ስርዓት በርገር ተሰርቶ ያየሁኝ እና ጣፍጦኝ የበላሁኝ ለገሃር ሚኒት ዉስጥ ነበር። ጾምም ያስገደፍኩበት ቤት ነበር።

ካልተሳሳትኩ የንግዱ ባለቤት አዲስ አበባ ዉስጥ በርካታ ኬክ ቤቶች የነበራት ባለ ሃብት ነበረች።

አሜሪካ ከደረስኩኝ በኋላ ባለ ሃብትዋ አምቦ ዉስጥ የመጀመርያዉን ከፍ ያለ ፎቅ ኣሰርታ ትንቀሳቀስ ነበር ኣሉ።

ሰንብቼም ንብረቷ በፖለትካ ረብሻ ምክንያት ተጎዳባት ኣሉ።

ለዚህ ርዕስ ጥሩ ምሳሌ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

የፖለትካ አስተዳደሯን ብታስተካክል አምቦ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ተቀምጣ፣ ባለ ሃብቶችን ኣስተባብራ እንደ ባህር ዳር እና አዋሳ መልማት የማትችል ነዉ?

መጫ እና ቱለማ ወደ ፖለትካ ንቅናቄ ተቀየረ እንጂ የተቋቋመዉ ለልማት ነበር ይባላል።

ስለዚህ ዘመናዊ ፌደራሊዝም ጽንሰ ሀሳብ ሳሰላስል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦን የፌደራላዊ አስተዳደር መዋቅር ማዕከል በማድረግ ለልማት በስነ ስርዓት መንቀሳቀስ ይችላል።

አስተዳደሩ ከክልል ቢሮክራሲ ወጥቶ የፌደራል መዋቅር ዉስጥ ገብቶ ለልማት በቀጥታ መንቀሳቀስ ማለት ከሌሎች የፌደራል አስተዳደሮች ጋር በቀጥታ ኣይተባበርም ማለት ኣይዴለም።

ዞኑን የዘመናዊ ፌደራል አስተዳደር ለማድረግ መጫ እና ቱለማ ወይም አምቦ ዩኒቨርዚቲ መምራት ኣይችሉም ወይ ብዬ ኣስባለሁ።

ለልማት ተቋቁሞ የፖለትካ አቅጣጫም ሀሳብ የነበረዉ መጫ እና ቱለማ ዘመናዊ የፌደራል አስተዳደር ማዋቀርን መርቶ ለልማት እንበርታ ማለት ኣይችልም?

ኢትዮጵያ እያለሁ ነበር የድርጅቱ መሪ የነበሩት ኮሎኔል አለሙ ቅጤሳ ቪ ኦ ኤ ላይ ተጠይቀዉ ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ ወደ የት ነዉ የሚገነጠለዉ ብለዉ ሲመልሱ የሰማሁኝ።

ኣጥጋቢ የዘመናዊ ፌደራሊዝም ተቋቋመ ማለት መጫ እና ቱለማ ወደ ተነሳለት ልማት መመላስ ይችላል ማለት ነዉ። ለቱለማም ዘመናዊ የፌደራል አስተዳደር ከተቋቋመ።

ኣልያም ልማቱን ለኣዲሱ የፌደራል አስተዳደሮች በመተዉ ጡረታ መዉጣት ይችላል። ዘመኑ ቻይና በኣጭር ግዜ ትልቅ ከተማ የምትገነባባት ነዉ ይባላል። የሌላ ኣፄ ምንሊክን መከታ መጠበቅ ኣያስፈልግም።

ዘመናዊ የፌደራል አስተዳደር በአስተዳደሩ ዉስጥ ያሉትን ማህበረስብ በሙሉ በማስተባበር ነዉ።

በእኔ ግምት አስተዳደሩ ዉስጥ የሚኖሩት በብዛት ገበሮዎች እና ቦረናዎች የሚባሉ ጎሳዎች ናቸዉ። የትኛዉ ጎሳ ብዛት እንደሚበልጥ መገመት ያስቸግረኛል። የአከባቢዉ የፖለትካ መሪዎች ያዉቁ ይሆናል።

በቦረናዎች ገበሮዎች የተባሉት ቀድመዉ በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ ገበሬዎች እንጂ እራሳቸዉን ኦርመ የማይሉ ነበሩ።

በእኔ ግምት ድምጻዊዉ ታደለ ሮባ ገበሮዎች ከሚባሉት ጎሳ ነዉ።

ሁለቱም ጎሳዎች ለዘመናት እንደ ኣንድ ማህበረሰብ በስምምነት ኣብረዉ ኖረዋል። ተባብረዉ ለልማት መነሳት የሚችሉ ናቸዉ።

ይህ ለዘመናዊ ፌደራሊዝም ጥሩ ምሳሌ መሆን ይችላል። ኣይችልም?

Post Reply