በመጀመሪያ ደረጀ፣ ምን ሰርተህ ጉምቱ ለመባል እንደበቃህ፣ አላዉቅም፣ መሬት ላይ ፈልጌ አጣሁ፣ ምን ፈፀመ፣ ምን አቅዶ ከግብ አደረሰ ና ተሳክቶለት የጉምቱ ፖለቲከኛ ስመ ጥር አገኛ ብዬ ለራሴ መልስ አላገኘሁም። ሌላ ሰዉ ልያርመኝ ይችላል።
ይህ እንዳለ ሆኖ በጣም የሰለቸኝ ና እጅ እጅ ያለኝ ነገር፣ ሁሉም እንደመጣለት ይነሳ ና የኦሮሞ ጥያቄ ይህ የኦሮሞ ጥያቄ ያ ሚዲያ ላይ መስተጋባት ይወዳል። አንተ ከነዚህ ሰዎች አንዱ ነህ። ማንሳቱ በልከፋ፣ ነገሩ ግን ወዲህ ነዉ።
የኦሮሞ ጥያቄ ስትሉ፡ የሕዝብ ጥያቄ ማለት ነዉ፣ የሕዝብን ጥያቄ ደግሞ አንግቦ ለመነሳት ሁለት መሰረታዊ ጉዳዪች መሟላት ይገባቸዋል።
1- የሕዝብ ዉክልና ማግኘት፣ በአግባቡ።
2- የሕዝቡን ጥያቄ ከሕዝቡ ራሱ ላይ ማሰባሰብ ያስፈልጋል
የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የምባለዉ ጉዳይ ከነዚህ ሁለቱ መስፈርቶች ዉጪ ከሆነ እንዴት ሆኖ ነዉ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ልባል የምችለዉ?
የኦሮሞ ሕዝብ እንደማንኛዉም ሌላ ሕዝብ ጥያቄ ልኖረዉ ይችላል፣ ይገባልም። ጥያቄዉ እንድመለስ የፈለጋ ማንኛዉም አካል በትንሹ ከላይ የተቀመጡትን መሰረታዊ መስፍርቶችን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል። እኔን እንደምመስለኝ።
ይህን ሳያደርግ እንድሁ ተነስቶ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የምል መፈክር ያምያስተጋባ ማንኛዉም አካል ወይም ግለሰብ የተደበቀ አለማዉን በሕዝብ ስም ስር ከለላ እያደረገ የምጓዝ ተንኮል ከመሆን ሌላ ልሆን አይችልም።
በዛሬይቷ ኢትዮጵያ ሁለቱን መስፍርቶች መሟላት የምከብድ አይመስለኝም፣ በእኔ ግምት፣ ስንፍና ወይም ተንኮል ከሌለበት።
የፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ መንቀሳቀስ የታገደበት አገር አይደልችም ኢትዮጵያ ዛሬ፣ አይደለም?
የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት የምቻል ከሆነ ደግሞ ጥያቄዉ ምን እንደሆነ በትክክል ጥናት አካህዶ የሕዝብ ጥያቄ ምን እንደሆነ ማጣራት አይከብድም፣ በአሁኗ ኢትዮጵያ ዉስጥ። ዛሬ ላይ የአገር የምክክር ኮምሽን ተብሎ ትልቅ ባጀት ተመድቦለት የምንቀሳቀስ ትልቅ አካል አለ።
ታዲያ አቶ ሌንጮ ሚዲያ ላይ ወጥቶ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ አልተመለሰም ብሎ ከመለፍለፍ፣ ለምንድን ነዉ በዚህ ረገድ ወደ የአገር ምክክር ኮምሽኑ ጠጋ ብሎ ይህ ነዉ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ማለት የልደፈረዉ?? ከልቡ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ተቆርቁሮ ከሆነ፣ ይህን እድል ሳይጠቀም ቀርቶ እንዴት ነዉ ሚድያ ላይ ብቻ እየወጣ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄን ከአፉ እንዳይወርድ የምያደርገዉ? ይህ ጉዳይ ራሱ ብቻ ተንኮል እንደ ተሞላበት አያሳይም፣ ከጥያቄ ጀርባ ያለዉ አካሄድ?
ይህ ትልቅ የአገር ሀብት ፈሶበት፣ የጉዳዩ በላቤት ሆኖ ሕዝቡ ዉስጥ ያላዉን ጥያቄ አጣርቶ ወደ ፊት እልባት እንዲያገኝ ነዉ ስንቱ ሰዉ የምለፈባት፣ መድርክ ለሕዝቡ ክፍት አድርጎ። አንተ አንድ ግለሰብ ሆነህ ሳላህ፣ እንዴት ነዉ ና በምን አግባብ ነዉ ታዲያ ወደ ተፈጠረዉ መድረክም ጠጋ ማለትን ፈርተህ፣ አሁን ደግሞ ወደ ለመድከዉ ሚዲያ ብቅ ብለህ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ አልተመለሰም የምትለን? ይህ ተንኮል ብቻ ነዉ ልሆን የምችልዉ፣ በእኔ ግምት።
ተንኮል ከለበት ደግሞ፣ አንተ ሰዉ መቼ ነዉ ተንኮልህን የምታቆመዉ? ልመሞት እንኳ ታቃርበህ፣ እንድሁ ተንኮል እየሸበረክ ወደ ጉድጓድ ልታቀና ነዉ? ሰዉን በትፈራ፣ ለእግዚያብሔር ስም ብለህ እንኳ ትንሽ እፍረት አይሰማህም? ለነብስህ አታስብም?
በአይኔ አይቼ መፍረድ ብከብደኝም ብዙ ሰዎች ስወነጅሉህ እድሜህን ሙሉ ተንኮል በመሸረብ ነዉ የጨረስከዉ ይላሉ፣ መካድ ትችላለህ?
የጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ መንግስት በስተእርጅነዉ አገሩ ገብቶ ይረፍ ብሎ ይቅርታ አድርጎልህ፡ እጁን ዘርግቶ ተቀብሎህ፣ አደር እንኳን ሳትል፣ ወዲያዉ ተነስተህ፣ ወደ መፈንቅለ መንግስት፣ አብይን ከስልጣን ለማዉረድ ብለህ ጋቻና ኦጋንሳ የምል ቡድን ጠፍጥፍህ፣ አስጠፍጥፍህ ብቅ አልክ፣ ለማ መገርሳን ጉድ አደርግከዉ፣ በአካሄዱ ላይ። ይህ ዉሸት ነዉ?
እኔ በቦታዉ ስላልነበርኩኝ መወሰን ይከብደኛል እንጂ፣ በቅርብ የምያዉቁህ ሰዎች እንደምሉት በአንተ የተንኮል መንገድ ላይ ብዙ ሰዎች የሕይወት ዋጋ ከፍሎዋል፣ አይደልም ኦቦ ሌንጮ?
ሕልናህ ይህን ሀቅ ይክዳል? በደረስክበት ቦታ ሁሉ ክደት አይደለም እንዴ የአንተ እስከ ዛሬ ተላይቶህ የማያዉቀዉ?
አንተን በይሰለችህ እኛን እኮ ሰለቸን፣ የአንተ ሴራ ና ተንኮል፣ የሕዝብን ስም ከለላ በመድረግ።
አሁን ደግሞ ጫካ ግቡ ብላችዉ ወደ ጫካ የላክችዉት ወጣት ተዉ ና ተብሎ ተለምኖ እምቢ በማለት እዛ ቁጭ ብሎ ሕዝቡን መከራዉን እያበላ የላዉን ውንብድና መንግስት እርምጃ መዉሰድ ስጀምር፣ ነገሩ እንደሳባችሁት እልህድ ስላችዉ፣ ለዚህች ደግሞ ኢሳት ለመቆስቆስ ዛሬም በአንዴ ተነስተህ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ አልተመለሳም ማለትን እንግብህ ወደዚይዉ ወደ ለመድከዉ ሚዲያ ብቅ አልክ። መንጋዉ ወጣት ደግሞ ይህን ይሰማ ና አይ ኦቦ ሌንጮ እንደዚህ ብሎዋል ና ጨካ መግባት አልብኝ ብሎ ዘፍ ብሎ እንድወጣልህ እየጎተጎትክ መሆኑ ግልፅ ነዉ።
የመንጋዉ ስብስብ ደግሞ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ ሳይሆን፣ ሕዝቡ ራሱን ስቃይ ለማሳያት ነዉ፣ ከዚያ ሌንጮ ና ግበረ አባሮቹ አይ እኝ ወደ ስልጣን ከልመጣን አገሪቷ ላይ ሰላም መምጣት አይችልም የምል አጉል ብልጣብልጥነትን አንግቦ ለመነሳት፣ አልያም ደግሞ ከምዘረፈዉ የሕዝብ ሃብት ተካፍሎ የግፍ ሃብት ማካበትን አንግባችዉ እየሮጣችዉ ነዉ።
የምሳካላችዉ ግን አይመስለኝም። ሕዝቡ መሮታል፣ እንጥፍ አድርጎ ተፍቶዋችዋል።
ከዚህ ዉጪ የምትመልሰዉ ምንም አይነት የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እንደሌላ አንተም ታዉቃለህ፣ ብትችል ኖሮ የለፉት 50 አመታት ይህንኑን ነበር እንግበህ የኦሮሞን ሕዝብ ደም ስታፈስ ና ስታስፈስስ የኖርከዉ። አሁን ግን ያም ሆነ ይህ የምትቀባጥረዉን ነገር ማንም ቁም ነገር አድርጎ አያዳምጥህም፣ ግፉ የሕዝቡ አፍንጫ ላይ ደርሶዋል።
ዉርደ ከጫንቃችን ላይ እየለ ነዉ ሕዝቡ።