Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Fiyameta
Senior Member
Posts: 19946
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር!

Post by Fiyameta » 01 Nov 2024, 18:17

አይ ኢትዮጵያዊ !
ኢትዮጵያዊና ልመና፦ አንድ


ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም



በዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር ኢትዮጵያዊ አንደኛ ከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለኢትዮጵያዊ፣ ልመና የኑሮ ዘዴ ነው፤ እንዲያውም ከልመና ውጭ የሆነ ኢትዮጵያዊ ኑሮ የለም ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ ስለዚህም ልመና ባህላዊ ጥበብ ሆኖአል፤ አንዳንድ አላዋቂዎች፣ አንዳንድ አዋቂዎችም አንዳንዴ እየተሳሳቱ ልመናን እንደነውር ይገልጹታል፤ ልመና ነውር አይደለም፤ ለጨዋ ልጆችማ አንዳንድ አጥንትን የሚያበላሽ ሥራ ከመሥራት ለምኖ መብላት ክብር ነው።

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቄሶቹ ምንም ይስበኩ በተግባር እንደሚታየው ጽድቅ የሚገኘው በልመና ነው እንጂ በሥራ አይደለም፤ ሥራኮ ለኢትዮጵያዊ ከእርግማን የመጣ ነው፤ ኢትዮጵያዊ አልተረገመ፤ ታዲያ ለምን ብሎ ይሥራ! አሁን እንደሚሰማውና እንደሚመስለኝ አገዛዙም እንደተቀበለው የቻይና ሰዎችም እንደመሰከሩለት ከሥራ ጋር ጠብ አለው፤ ደግሞስ ለምን ይሥራ! ለአንድ እንጀራ? ለተራበ አብልተው ለመጽደቅ የሚፈልጉ ስንትና ስንት ሰዎች አሉ፤ ስለዚህም ደግ ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ ለመጽደቅም መለመን ያስፈልጋል፤ ጸሎት ልመና መሆኑን አትርሱ፤ ስለዚህም ዋናውና ከፍተኛው ልመና ወደ እግዚአብሔር ነው፤ ብልጦቹ እግዚአብሔርን የሚለምኑት ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ነው፤ አንድ ቀን ተነሥተው እግዚአብሔር ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት እንደሰጣቸው ያውጃሉ፤ አውጀውም በሕዝብ ራስ ላይ ይወጣሉ፤ በራሱ ላይ ወጥተውም ይጨፍራሉ፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው መለየት ይሳናቸዋል፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው ያጣላሉ፤ እግዚአብሔር ለእናንተ ብቻ እንዴት ሰጣችሁ? እግዚአብሔር እኛን ለምን ነፈገን? ብሎ የሚጠይቃቸውን እየደበደቡና እያቃጠሉ፣ እየገረፉና እያራቆቱ በዝምታ እንዲገዛ ያደርጉታል፤ አልበቃው ካለም አካሉን ለውሻ ሰጥተው ነፍሱን ወደእግዚአብሔር ይወረውራሉ፤ እግዚአብሔር እየቆጠረ የማይመዘግብ ይመስላቸዋል፤ የጠጠረ ጉልበታቸው ዓይኖቻቸውን አውሮ፣ ኅሊናቸውን አፍኖ እግዚአብሔር በዕዳ እንደሚይዛቸውና በጥጋባቸው ያደሉትን መከራና ስቃይ፣ የወረደውን እንባና ደም ከነወለዱ እንደሚያስከፍላቸው መገንዘብ ያቅታቸዋል።

እግዚአብሔር ፍርዱን እስቲሰጥ ድረስ ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ተረክበናል የሚሉት የተለያዩ ስሞችን እየለጠፉ በተዋረድ የለማኞችን ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ሕዝብ ሁሉ ከነዚህ የለማኞች ሠራዊት በአንዱ ውስጥ ለመግባት በፉክክር ይተላለቃል፤ ሠራዊቱ ውስጥ በመግባት የሚገኘው ጉርሻ ልጆቻቸውን እንኳን ከረሀብ የማያድን መሆኑን ሳይገነዘቡ መብታቸውን እያስረገጡ የሌሎችን መብት ለመርገጥ መሣሪያ ይሆናሉ፤ እነዚህ እንግዲህ ልመናን በማኅበረሰቡ ውስጥ ተክለው እየኮተኮቱ የሚያስፋፉት ናቸው፤ ልመናን ባህል የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው፤ ልመናን ታሪካችን ያደረጉት እነዚህና ከነሱ የቀደሙት ገዢዎቻችን ናቸው።

በእኛ ባህል የራበውን በማብላት ጽድቅ ይገኛል፤ ስለዚህም ለምኖ መብላት ይቻላል፤ ስለዚህም ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ እንግዲህ ለምነው እየበሉ መኖር ከተቻለና እግዚአብሔርን በመለመን ጽድቅ ከተገኘ፣ የመሬቱንና የሰማዩን ጣጣ በልመና መገላገል ከተቻለ ታዲያ ሥራ ለምን ያስፈልጋል! ለነገሩስ ሥራ በእርግማን የመጣ ነው፤ ስለዚህ የተረገሙት ሲሠሩ ያልተረገሙ የሚመስላቸው ይለምኑ፤ ለሌላው ዓለም ልመና የችግር ምልክት ነው፤ ለኢትዮጵያዊ ግን ልመና የጽድቅ ምልክት ነው፤ የጨዋ ልጅ፣ ማለት በልመና በሰዎች ላይ ሥልጣንን ከአግዚአብሔር አግኝቻለሁ ብሎ የሚያምን፣ አይሠራም፤ ቀን ቢጥለውም የጨዋ ልጅ በእጁ ሠርቶ ከሚበላ ለምኖ ቢበላ ይሻለዋል፤ ሆድ የተፈጥሮ ነው፤ ረሀብም የዕለት ከዕለት የተፈጥሮ ግዳጅ ነው፤ ስለዚህም ለአበሻ የተፈጥሮን ሆድና የተፈጥሮን ረሀብ በልመና መወጣት የተፈጥሮን ሥርዓት መከተል መስሎ ይታየዋል።

ሌላ ቀርቶ ተማሪ ለምኖ ካልበላ ትምህርት አይገባውም፤ ለተማሪ ሲሆን ልመና አይባልም፤ ቀፈፋ ነው፤ ኢትዮጵያዊ በልመና ምን ይህል እንደተራቀቀ የሚያመለክተው ለተለያዩ ልመናዎች የተለያዩ ስሞች ማውጣቱ ነው፤ እንደተባለው ተማሪ ሲለምን ቀፈፋ ነው፤ በዘመናዊ ቋንቋ የትምህርት ታክስ ነው፤ ምግብ የሚቀርብበትን ሰዓት እየጠበቀ ከተፍ የሚለው ቀላዋጭ ነው፤ አብዛኛውን ጊዜ ለቀላዋጭ ቀላል ሰበብ የሚሆነው ቀላውጦ የሚያገኘው ወሬ ነው፤ ሌላም የልመና ዓይነት አለ፤ እርጥባን ይባላል፤ — ደርቄአለሁና አርጥቡኝ ማለት ነው! ‹ላሊበላዎች› የሚባሉት ለምነን ካልበላን እንቆመጣለን በማለት ልመናን የኑሮ መሠረት አድርገውታል፤ ሌላም የልመና ዘር አለ፤ ደጅ መጥናት ይባላል፤ ደጅ መጥናት ማለት ብርዱን ችሎና እንቅልፉን አቋርጦ በሌሊት እየተነሡ በመኳንንቱና በመሳፍንቱ፣ በንጉሡ፣ በንጉሠ ነገሥቱ ደጃፍ ላይ አጥር ወይም ዛፍ እየተደገፉ የተፈለገውም ሰው ብቅ ሲል በመሬት ላይ በመነጠፍ እጅ በመንሣት ፊት ለማስወጋት ለመታወቅና ለሹመት ለመታጨት የሚጠቅም የልመና ዘዴ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሁሉም ነገር በልመና ነው፤ ምግብ በልመና፣ ትምህርት በልመና፣ መሬት በልመና፣ … በልመና፣ ግብር የሚከፈለው በልመና ነው፤ ሥልጣን የሚገኘው በልመና ነው፤ ንጉሥነትም የሚገኘው በልመና ነው፤ ባጭሩ ኑሮ ማለት ልመና ነው፤ ልመና ማለት ኑሮ ነው ።

ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog
https://mesfinwoldemariam.wordpress.com ... %E1%8B%B5/


Digital Weyane
Member+
Posts: 9838
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር!

Post by Digital Weyane » 01 Nov 2024, 19:17

ኢትዮጵያውያንን ልመና ያስተማርናቸው ኡኛ ወያኔ ነን። ልመና ስራ ነው። :roll:

Fiyameta
Senior Member
Posts: 19946
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር!

Post by Fiyameta » 01 Nov 2024, 20:00

ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር! 8) 8)


Fiyameta
Senior Member
Posts: 19946
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር!

Post by Fiyameta » 01 Nov 2024, 21:12

ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር! ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

  • ዳገት ላይ ሰው ጠፋ፤ አቀበት ከበደ፤
    ሁሉም በሸርተቴ ቁለቁለት ወረደ፤
    ሰው ተዋረደ፤
    ገንዘብ ተወደደ፤
    በምነቱ፣ ፍቅር፣ በክብሩ ነገደ፤
    በቁልቁለት ኃይል እየተገደደ፡፡


አንድ አገር ዜጎቹ በደሀነትና በለማኝነት በችጋርና በስደት ሲታወቅ በነእዚህ ከችጋር በተረፉ ለማኞችና ስደተኞች ላይ የበላይነት እየተሰማው የሚኮራና አገሩን የሚያኮራ ሰው አለ? የአገር ውርደት ለማን የኩራት ምንጭ ይሆናል? የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደአሜሪካ ወይም ወደአውሮፓ (የተሙዋላ ነፃነት ባሉባቸው አገሮች) ሲሄድ የሚያጋጥመው ዜጎች ተሰብስበው እንኳን ደህና መጣህ የኛ መሪ የሚል ጭብጨባ አይደለም፤ ይህ አያሳፍርም? አያስቀናም? ሰዎችን አዋርዶ መከበር አይገኝም፤ ጠመንጃና ጉልበት የውስጡ እውነት እንዳይወጣ ያፍናል እንጂ እውነቱን አያጠፋውም፤ ዞሮ ዞሮ ሰዎችን ማዋረድ ራስን ማዋረድ ነው፤ የተዋረዱ ሰዎች በውስጣቸው የሌለውን ክብር ለሌላ ሊሰጡ አይችሉም፤ የተዋረደ ሰውስ አከበረ ወይ አላከበረ ምን ፋይዳ አለው? ፋይዳ ያለው የሚያከብሩት ሰው ሲያከብር ነው፡፡

Fiyameta
Senior Member
Posts: 19946
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር!

Post by Fiyameta » 02 Nov 2024, 02:15

Young revolutionary Isaias Aewerki's quote below says, (Rough Translation)
  • "We are who we are, and we refuse to become political pawns of global powers. We aspire to become absolute masters of our fate and destiny. Therefore, we will never sell our soul for aid, nor do we surrender our human dignity and self-respect for short-term gain. We strive to be ourselves, not what others want us to be. We are determined to fight to the bitter end for what is right, because victory is guaranteed to those who never give up fighting."







Abdisa
Member+
Posts: 6263
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር!

Post by Abdisa » 02 Nov 2024, 13:36

It is a political suicide to speak against being a client state in Ethiopia. And it is almost a taboo for the educated class to entertain the noble ideas of sovereignty, self sufficiency and human dignity. The honorable professor chose to live one day as a fierce lion than 80 years as a sheep. RIP.
Fiyameta wrote:
01 Nov 2024, 20:00
ቀድመው የነቁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር! 8) 8)


Post Reply